Citizens Journal ኢትዮጵያ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


አዳዲስ ወቅታዊ ትክክለኛ መረጃዎችን ማድረስ። ሰላም፣ ፍቅር አንድነትን እና ኢትዮጵያዊነትን መርህ መከተል።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: Ethio Job Vacancy
Vacancy Announcement – SITT
SITT would like to invite qualified and interested job seekers to apply for the following vacant position.
Position 1: Junior Mechanical Engineering
Position 2: Foreign procurement specialist
Position 3: Junior Sourcing Officer
Position 4: Junior Marketing officer
Position 5: Sourcing Division Officer
Position 6: Junior Accountant
Position 7: Bid Document Facilitator
Position 9: Import document officer
Position 10: Import Manger
Position 11: Sourcing Division Manger
Position 12: Secretary
Position 13: Senior Marketing Officer
Position 14: Logistics and Distribution Head
Position 15: Senior Accountant
Position 16: Sales Division Head
Position 17: Finance Manager
How to Apply: (ይመልከቱ፤ ፈጥነው ያመልክቱ!)
For details use the link below and apply: 👇👇👇
https://sewaseweth.com/sitt-job/
Deadline: February 12, 2025
🔗መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ እባክዎ ለወዳጅ-ጓደኛዎ ያጋሩት
Don’t forget to share for your friends
For more join via Telegram: @Ethiojob1Vacancy


የፌዴራል መንግስት የዘንድሮ አጠቃላይ በጀት 1.5 ትሪሊዮን መደረሱ ህዝቡን ለተጨማሪ ግብር የሚዳርግ እና የሚያማርር ሊሆን ይችላል ሲሉ የፓርላማ አባላት ተናገሩ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ይህን ያሉት የፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ በጀትን ለማጽደቅ በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ባደረጉት ወይይት ነው፡፡የ2017 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት መደበኛ በጀት ከዚህ ቀደም 971.2 ቢሊዮን ሆኖ መጽደቁ ይታወቃል፡፡

ይሁንና ከ2017 አስከ 2021 ድረስ የተነደፈውን የማክሮ ኢኮኖሚ እና የፊስካል ፖሊሲ ማዕቀፍ ማሻሽያ ተከትሎ ከታክስና ከወጪ ፋይናንስ የሚገኘውን ገቢ በመጨመሩ ለመደበኛ ስራዎች እና የወጪ አሽፋፋን ለማስተካከል ተጨማሪ በጀት ማጽደቅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ተብሏል፡፡

ተጨማሪ በጀቱ ለዕዳ ክፍያ፣  ለማህበራዊ ድጋፍ፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስተካከያ እንዲሆን መታሰቡን  በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መንግስት ተጠሪ ሚኒስትሩ ተስፋዬ ቤልጂጌ ተናግረዋል፡፡በዚህም ለበጀት ዓመቱ ያስፈለገው ተጨማሪ በጀት 582 ቢሊዮን ብር ነው ብለዋል፡፡

ለመደበኛ ወጪ 393 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪ 70 ቢሊዮን እና ለወጪ አሸፋፈን 119 ቢሊዮን ብር ሆኖ ቀርበዋል፡፡የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው ተጨማሪ በጀቱ የተጋነነ ነው የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡

ህዝቡንም  ለተጨማሪ የግብር  የሚዳርግ እና የሚያማርር ሊሆን ይችላል ሲሉ የፓርላማ አባላት ሃሳባቸውን እያቀረቡ ነው፡፡ምክር ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ 582 ቢሊየን ብር በጀትን አጽድቋል፡፡

Via Sheger FM


የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች "ፋይዳ" መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ መሆኑን አስታወቀ

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ በሚገኙት 16 ቅርንጫፎች ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ደንበኞች "ፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ ዓለምእሸት መሸሻ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት ለማግኘት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ መሆኑ እንደታመነበት እና መወሰኑን  ተጠቁሟል።

በመሆኑም ከህዳር 1 ቀን 2017 ጀምሮ ተቋሙ ለሚሰጠው አገልግሎት ደንበኞች ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው ተገልጿል።


BALLON D'OR DAY

የፍራንስ ፉትቦል ጋዜጣ የሚዘጋጀው ስልሳ ስምንተኛው  ተጠባቂው የ2024 የባሎን ዶር ሽልማት ስነ ስርዓት ዛሬ ምሽት ይካሄዳል።

አንድ የእግርኳስ ተጫዋቾች በእግርኳስ ህይወቱ ሊያሸንፈው የሚፈልገው ትልቁ የግል ሽልማት ነው ።

የሽልማት ስነስርአቱ ዛሬ ምሽት በፈረንሳይ ርዕሰ ፓሪስ ይከናወናል ።

የዘንድሮው የ2024 የባሎን ዶር ሽልማት ያለፈውን የውድድር ዘመን ብቻ ያከተተ መሆኑ ተውቆዋል።

ሽልማት የሚበረከትባቸዉ ዘርፎች ፦

• ምርጥ ወንድ ተጨዋች
• ምርጥ ሴት ተጨዋች
• ምርጥ የወንዶች ክለብ
• ምርጥ የሴቶች ክለብ
• የኮፓ ሽልማት (ምርጥ ወጣት ተጨዋች)
• የያሺን ሽልማት (ምርጥ ግብ ጠባቂ)
• የሙለር ሽልማት (ምርጥ ግብ አስቆጣሪ)
• የሶቅራጥስ ሽልማት (ምርጥ የሰብአዊ ስራ)
• ምርጥ የሴቶች አሰልጣኝ
• ምርጥ የወንዶች አሰልጣኝ

ፕሮግራሙን  ዲዲየ ድሮግባ ይመራል ።


#BRICS+

በሩስያ፣ ካዛን ሲካሄድ የቆየው የBRICS+ አባል ሀገራት መሪዎች ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል።

ስብስቡ 13 ሀገራትን በአጋር (ፓርትነር) አድርጎ ተቀብሏል።

ሀገራቱን የBRICS አጋር (ፓርትነር) አድርጎ የተቀበለው በ2024 ምንም አይነት አዲስ ሙሉ አባል ሀገር ላለመቀበል በመወሰኑ ነው።

13ቱ ሀገራት ወደፊት የስብሰቡ ሙሉ አባል ሀገር ለመሆን እንደሚሰሩ ነው የተነገረው።

የBRICS+ ሙሉ አባል ሀገራት እነማን ናቸው ?

🇧🇷 ብራዚል
🇷🇺 ሩስያ
🇮🇳 ሕንድ
🇨🇳 ቻይና
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇪🇹 ኢትዮጵያ
🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ
🇮🇷 ኢራን
🇪🇬 ግብፅ ናቸው።

አሁን BRICS+ን በአጋርነት (ፓርትነር) ሆነው የተቀላቀሉት እነማን ናቸው ?

🇩🇿 አልጄሪያ
🇧🇾 ቤላሩስ
🇧🇴 ቦሊቪያ
🇨🇺 ኩባ
🇮🇩 ኢንዶኔዥያ
🇰🇿 ካዛኪስታን
🇲🇾 ማሌዢያ
🇳🇬 ናይጄሪያ
🇹🇭 ታይላንድ
🇹🇷 ቱርክ
🇺🇬 ዩጋንዳ
🇺🇿 ኡዝቤኪስታን
🇻🇳 ቬዬትናም ናቸው።

በካዛኑ የBRICS+ የመሪዎች ጉባኤ የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ፣ የቬንዝዌላው ፕሬዜዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ተገኝተው ነበር።

የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ካዛን ተገኝተው ነበር። ሳዑዲ ምንም እንኳን በይፋ የBRICS ስብስብን ባትቀላቀልም በተጋባዥ ሀገርነት ትሳተፋለች።

የሌሎች ሀገራት መሪዎችና ተወካዮችም በካዛን ተገኝተው ነበር።

#BRICSSummit #Russia


የአለልኝ አዘነ ግድያ ተጠርጣሪዎች ፍርድቤት ቀርበዋል።

በቀን 5/2/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት እንደተገለጸው (የገዛ ባለቤቱ) ሆን ብላ እቤት ውስጥ ያለውን ንብረት በመሰባበር ስልክ ደውላ በቅጽል ስሙ (ሉንጎ ) የተባለውን ተጠርጣሪ መጥራቷን  ችሎቱ  አስረድቷል ። (የቀድሞ የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ ቦዲ ጋርድ እና የእህቱ  ባልም ጭምር  ነው ) ።

ተጠርጣሪው ግለሰብ ከመጣ በኋላ ስልኩን ቀምቶ ወስዶ እቃ ለምን ሰበርክ ብሎ በመጠየቅ  መደብደብ ሲጀምር  ሟች ሮጦ በአጥር በመውጣት ከቤት ቢያመልጥም የገዛ ባለቤቱ ተከተለው ብላ በነገረችው መሠረት ተከትሎት ሄዶ የአንገት አጥንቱን በመምታት ከገደለ በኋላ ለማስመሰል በአቅራቢያ ባለው ስልክ እንጨት ላይ መስቀላቸውን የሚገልጽ በቂ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ማግኘቱን ፍርድቤቱ በዋለው ችሎት አሳውቋል።

ፍርድ ቤቱ ቀጣይ በቀን 21/02/207 ዓ/ም የሰው ማስረጃ ለመስማት  ቀጠሮ መያዙንም አሳውቋል።

በምርመራው ሂደት የምርመራው ቡድን አባላት ጠንካራ ፣ ፍታዊ እና  ከፍተኛ ኃላፍነት የተሞላ  የምርመራ ሂደት ማድረጋቸው ለዚህ ውጤት መገኘት መነሻ እንደሆነም ተጠቁሟል ።


የምርመራው ውጤት👇


በኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ ላይ የተደረገው ማስተካከያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰኔ 13/2016 ዓ.ም መጽደቁ ይታወሳል።

ይህ ተከትሎ  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት የታሪፍ ማሻሻያው ከመስከረም 1/2017 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሽፈራው ተሊላ የታሪፍ ጭማሪው የደንበኞችን የኃይል የአጠቃቀም መሰረት ያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም፦

የቤት ደንበኞች፤ የንግድ ተቋማት፤ ዝቅተኛ ኢንዱስትሪ፤ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ እንዲሁም የመንገድ መብራት ተጠቃሚዎች በሚል መከፋፈሉን አስታውቀዋል።

የቤት መብራት ተጠቃሚዎችን በተመለከተ " እንደ አጠቃቀማቸው አሁን ከሚከፍሉት እና ጭማሪ ከተደረገበት መካከል ያለውን ልዩነት ሲከፍሉ እንደ አጠቃቀማቸው ድጎማ ተደርጓል " ሲሉ አስረድተዋል።

ድጎማው ምን ይመስላል ?

➡️ 50kW በታች ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 75 በመቶ የሚሆነውን ይደጎማሉ፤

➡️ ከ50kW - 100KW ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 40 በመቶ የሚሆነውን ይደጎማሉ፤

➡️ 200kW - 300 Kw ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 4 በመቶ የሚሆነውን ይደጎማሉ፤

➡️ 400kW - 500 KW የሚሆነውን ማሻሻያውን ያለምንም ድጎማ ይከፍላሉ

➡️ ከ500kW በላይ የሚሆነውን ደግሞ ሌላውን ተጠቃሚ የሚደግፉበት የጎንዮሽ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ ይደረጋል።

የአከፋፈሉ ሁኔታ ምን ይመስላል ?

እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ ይህ የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያው (የተጨመረው 6 ብር) የሚከፈለው በአንድ ጊዜ ሳይሆን በ16 ዙር በሚደረግ የሂሳብ ማስተካከያ [ከመስከረም 1 /2017 ጀምሮ] በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

ኢንጂነር ሽፈራው ይሄንን ሲያስረዱ 50KW የሚጠቀሙ ደንበኞች አሁን የሚከፍሉት 27 ሳንቲም እንደሆነ ገልጸው ከመስከረም ጀምሮ የሚከፍሉት 35 ሳንቲም ይሆናል ብለዋል።

ከአራት ዓመታት በኋላ ደግሞ [በ16 ዙሮች በሚደረግ ማስተካከያ] 1.56 ብር መክፈል ይጀምራሉ ሲሉ አስረድተዋል።

ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ያለው ጫና ተጠንቷል ወይ ?

ይህ ጥያቄ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው ሲሆን በሰጡት ምላሽ በዚህ ላይ ጥናት መደረጉን ጠቅሰው ይህም #ከአራት_ዓመት በኋላ የሚኖረው ተጽዕኖ 2 በመቶ እንደሆነ አንስተዋል።

" ከአከራይ ተከራይ ጋር ያለው ተጽዕኖም በጣም አነስተኛ ነው፤ የሚያጣላቸው ነገር አይኖርም " ሲሉ አስረድተዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለው ይህ የታሪፍ ማሻሻያው በዋነኛነት የወጣበትን ወጪ ለመሸፈን (A cost reflective tariff) መሰረት ያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

#ማብራሪያ: ከላይ የተያያዘው ሰንጠረዥ ድጎማ የተደረገበት የሂሳብ ታሪፍ ሲሆን። በዓመት 4 ጊዜ በ4 ዓመት ደግሞ 16 ጊዜ የሚተገበር የሂሳብ ማስተካከያ የያዘ ነው።








Updated EEP Payment tariff


#GERD🇪🇹

ፕ/ር አታላይ አየለ ምን ነበር ያሉት ?

ኢትዮጵያ የሁለተኛውን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ሙሌት ባከናወነችበት ወቅት በግብፅ ጉዳይ አንድ አስተያየት ሰጥተው ነበር።

ፕ/ር አታላይ አየለ ፦

" ግብፆች ' ግድቡን እንመታለን ' ምናምን የሚሉት ፣ የሚያስፈራሩት ነገር አለ።

የግድቡ ግዝፈት እንዲሁም ሚሰራበት ጥራት እውነት ለመናገር መቼውንም ቢሆን ተመቶ ይፈርሳል ተብሎ የሚታሰብ አይደለም።

እንደው ተሳክቶላቸው እንኳ ቢሆን የውሃ ሙሌቱ ልክ እንደ #ኒውኩሌር_ቦምብ ማለት ነው ለራሳቸው የሚሆነው ፤ ጠራርጎ ሜዴትራንያን ባህር ውስጥ ነው የሚጨምራቸው።

የቀድሞ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ' ግድቡን እኛ ሳንሆን እነሱ ናቸው የሚጠብቁት ' ብለዋል።

ስለዚህ ከዚህ አንፃር ኢትዮጵያ ብዙ የሚያስጨንቃት አይደለም።

ቢፈልጉ ይደራደሩ በአካሄድ በሌሎች ጉዳዮች ፣ የውሃ ፣ አካባቢ ጥበቃና በሌሎች የመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ። "

#ETHIOPIA
#GERD


#ETHIOPIA🇪🇹

የቀን ቅዠት ነው !!!

" እንደ አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምንም ዓይነት የፀጥታ ሥጋት እንዲኖር አልፈልግም ነገር ግን በኢትዮጵያ አቅም በተለይም በሕዝቦቿ ስለምተማመን እንቅልፍ አልባ ሌሊት የለኝም፡፡ #ግብፅ በሶማሊያ በኩል መጥታ ኢትዮጵያን አጣቢቂኝ ውስጥ መክተት ትችላለች ማለት የቀን ቅዠት ነው። " - አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ (የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር)


በቁጥጥር ሥር ዋሉ‼️
የፐርፐዝ ብላክ ሥራ አስፈጻሚዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️
የፐርፐዝ ብላክ ኢ ቲ ኤች ትሬዲንግ አክሲዮን ማኅበር ሥራ አስፈጻሚዎች ስልጣንን አለአግባብ በመገልገል እና ከባድ አታላይነት የሙስና ወንጀሎች ተጠርጥረው ዛሬ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በማኅበሩ ተጭበርብረናል ያሉ ባለአክሲዮኖች ለፖሊስ ባቀረቡት አቤቱታ መነሻነት ምርመራ ተጀምሮ የአክሲዮን ማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚዎች ከላይ በተገለጹት ምክንያቶች በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ማኅበሩ መሀል ሜክሲኮ ላይ ገና በእጁ ባላስገባው መሬት እና ይዞታ ቤት ገንብቶ ባለ ሦስት መኝታ አፓርትመንት በ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚሸጥ መሆኑን በሚዲያ እና በራሪ ወረቀቶች በማስተዋወቅ ከሕዝቡ ገንዘብ ሲሰበስብ መቆየቱን በተለያየ መንገድ ከሕብረተሰቡ ሲቀርቡ የነበሩ ቅሬታዎች ያመላክታሉ፡፡

በዚህ መነሻም ሥራ አስፈጻሚዎቹ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፍትሕ ሚኒስቴር አስታውቋል።
==================


ይህ ዛሬ ጠዋት ገርባ የተከናወነ ነው‼
ነሐሴ 23/2016 ዓ.ም
ደቡብ ወሎ ቃሉ ወረዳ ገርባ ከተማ ቀጨማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ አሁነ ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለች አንድ እናት ነሐሴ 17/2016 የወለደችውን ህፃን ልጅ ሽንት ቤት ጥላ ዛሬ ነሐሴ 23/2016 ተገኝቷል።

የአካባቢው ፖሊሶችና የገርባ ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች ከማህበረሰቡ ጋር  የህፃኑን አስክሬን ከሽንት ቤት ወጥቶ በክብር እንዳሳረፉት ገልፀዋል።
ሴቶች ወልዳችሁ የማታሳድጉትን አትፀንሱ:ተከላከሉ።
==========================
©ዋሱ መሐመድ


የአሜን ሆስፒታል ህክምና ማስረጃ

👉 ህፃን ሄቨን ን አስመልክቶ


ለባህርዳር ከተማ ፓሊስ መምሪያ
8ኛ ዋና ፓሊስ ጣቢያ

ህፃን አሜን አወት ግርማ የተባለች ግለሰብ ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ህክምና ማዐከላችን ስትደርስ ምንም አይነት የህይወት እስትንፋስ አልነበራትም::

1. በወቅቱ ሙሉ ሰውነቷና ልብሷ በውሀ የራስ ነበር

2. አንገቷ ላይ የእጅ ምልክት ( strangulation marks) ነበራት

3. እንዲሁም

ድንግልናዋም ያልነበረ መሆኑን ስናረጋግጥ ለበለጠ የአስክሬን ምርመራ ወደ ፈለገ-ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል የላክናት መሆኑን እንገልፃለን::

ከሰላምታ ጋር
ግልባጭ :- ለሜዲካል ዳሬክተር

አሜን የህክምና አገልግሎት ኃ/የተ/የግል/ማህበር
Amen Medical Services PLC



Показано 18 последних публикаций.