የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ለሁሉ የብድርና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር በጋር ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ ።
***
ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ወጋየው ገ/ማርያም እና የለሁሉ የብድር እና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር የቦርድ ሊቀመንበር አቶ መስፍን ዲባባ አማካኝነት ነው።
ስምምነቱ በዝቅተኛ የስራ እንቅስቃሴ ላይ ያሉ የአክሲዮን ማህበር ደንበኞች ገንዘብ እንዲቆጥቡ፣ እንዲያስተላልፉና እንዲበደሩ የሚያስችል የስራ አጋርነት የፈጠረ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ለሁሉ የብድርና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር በአሁኑ ሰዓት 20ሺ ደንበኞች ያሉት ሲሆን በስምምነቱም የደንበኞች ቁጥር 100 ሺ ለማደረስ እና ቅርንጫፎችንም ማስፋፋት እንዲሚያስችል የቦርድ ሰብሳቢው ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ወጋየው ገ/ማርያምአቶ በበኩላቸው ሌሎች የክፍያና የብድር ቁጠባ ተቋሞች ከባንኩ ጋር ተቀራርበው ቢስሩ እንደ አገር የፋይናንስ አካታችነትን እውን ለማድረግ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል ፡፡