💎 እንቁ የሴቶች ምሳሌ 🌹
በኢማኗ የተራራን ያክል ጠንክራ ከፊርአውን እና ከጭፍሮቹ ፊት በሃቅ የቆመች በምድር ላይ ያለ የቅጣት አይነት ሲፈራረቅባት ምንም ያልተበገረች፣ በፊርአውን ቤተመንግስት ውስጥ ያለው የተትረፈረ ድሎት አኸይራን ያላስረሳት እመቤት አስያ አላህ ሱብሃነሁ ወተአላ እስከ ቂያማ ቀን ድረስ ስትዘከር እንድትኖር እና የጀግንነት ውሎዋ መብራት ነጸብራቁ ለወንዱም ለሴቱም ያበራ እና ምሳሌም ትሆን ዘንድ በሚያምረው የቁርአን ዘይቤ እንዲህ ሲል ይነግረናል።
وَضَرَبَ اللَّهُ مَثَلاً لِلَّذِينَ آمَنُوا امْرَأَتَ فِرْعَوْنَ إِذْ قَالَتْ رَبِّ ابْنِ لِي عِنْدَكَ بَيْتاً فِي الْجَنَّةِ وَنَجِّنِي مِنْ
فِرْعَوْنَ وَعَمَلِهِ وَنَجِّنِي مِنَ الْقَوْمِ الظَّالِمِينَ
✍ትርጉም፦
ለእነዚያ ለአመኑትም የፈሮንን ሴት አላህ ምሳሌ አደረገ፤ ጌታየ ሆይ አንተ ዘንድ በገነት ውስጥ ለኔ ቤትን ገንባልኝ፡ ከፈርኦን እና ከስራውም አድነኝ፡ ከበደለኞቹ ህዝቦችም አድነኝ ባለች ጊዜ።
አስያ አላህን የለመነችው ጸጋ በጀነት ቤት እንዲገነባላት ነበር እንጅ ዱንያዊ ጥቅም እና ብልጭልጩን አለም ከዚያ ከፊርአውን ቤተመንግስትም ቢሆን አላጣችውም ነበር።
በፊርአውን ትዝዛዝ እንደዚያ ስትቀጠቀጥ ሁሉን ነገር በትዕግስት ችላ እና ተቋቁማ የተቀደሰች ነፍስዋ ከሥጋዋ ተለይታ ወደ ተዘጋጀላት የክብር ማረፊያ በሄደበት ወቅት ከፊቷ ላይ ፈገግታ አልተለያትም ነበርና የሚያሰቃዩዋት ሰዎች ህይወቷ ማለፉን በቀላሉ አልተገነዘቡም ነበር።
አስያ ይህም ብቻ አልነበረም አስገራሚ ታሪኳ እና የኢስላም ባለውለታዋነቷ። ነብዩላህ ሙሳ ከቤታቸው ሲያድጉ በወቅቱ ፊርአውን ወንድ ልጅ የሚባል ሲወለድ በሚገድልበት ጊዜ እሷ ግን በዚያ አረመኔ ባሏ ቤት ነብዩላህ ሙሳ በእንክብካቤ እንዲያድጉ የተቻላትን ማድረጓን አሁንም ቁርአን እንዲህ በማለት ይገልጽልናል
وَقَالَتِ امْرَأَتُ فِرْعَوْنَ قُرَّتُ عَيْنٍ لِّي وَلَكَ لَا تَقْتُلُوهُ عَسَى أَن يَنفَعَنَاأَوْ نَتَّخِذَهُ وَلَداً وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ
የፈርኦን ሚስት ለኔ የአይኔ መርጊያ ነው ለአንተም። አትግደሉት ሊጠቅመን ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው የከጀላልና፡ አለች እነሱም (ፍጻሜውን) የማያውቁ ኾነው (አነሱት)
https://t.me/Quran_Yelb_Brhan