እየሱስ (ኢሳ ዐሰ) አምላክ ነው ወይስ መልዕክተኛ???


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ጥንቃቄ አድርጋችሁ ተከታተሉ አረጋግጡ
17:36 ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል። አንብብ ዲንህን እወቅ""!

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች
~
ኢትዮጵያ በምትከተለው ክርስቲያናዊው የዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ አመት ሊገባ የያዝነው አመት እየተጠናቀቀ ነው። ታዲያ ይህን ክስተት ተከትሎ የሚፈፀሙ ከሃይማኖትችን ጋር የማይሄዱ በርካታ ጥፋቶች አሉ። ከነዚህም ውስጥ
1. ቀዳሚው ድግምትና ጥንቆላ ነው፡፡ በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ነሀሴ ሊጠናቀቅ ሲል በየጠንቋዩ ቤት የሚልከሰከሱት እጅግ ብዙ ናቸው። ከዚያም አምስቱ ወይም ስድስቱ የጳጉሜ ቀናት መንገዶች በድግምት ስራዎች ይሞላሉ። በነዚህ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ። በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ-ጌጦች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ። ጥንቆላና ድግምት:-

* ከኢስላም የሚያስወጡ ከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡
وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ
“በሱለይማን ዘመነ-መንግስት ሸይጧኖች የሚያነቡትንም (ድግምት) ተከተሉ። ሱለይማን ግን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረምና።) ግና ሸይጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ።” [በቀራህ፡ 102]
ነብዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ፣ በሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል።} [አሶሒሐህ፡ 3387]

* ደጋሚዎችና ከነሱ ዘንድ የሚመላለሱ ሰዎች መቼም ቢሆን ስኬት የላቸውም። ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም።” [ጦሃ፡ 69]

* ደጋሚዎች የሰዎችን ገንዘብ በማታለል የሚበዘብዙ መዥገሮች ናቸው። ገንዘቡን ለነሱ የሚሰጥ አካልም አላህ ፊት ተጠያቂ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {የኣደም ልጅ በቂያማህ ቀን አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንደጨረሰው፤ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው፤ እንዲሁም በምን እንዳወጣው፤ ባወቀው ምን እንደሰራ።} [አሶሒሐህ፡ 946]

* ደጋሚዎች የነገር ቋቶች የማህበራዊ ህይወት ጠንቆች ናቸው። የተቸገረ ደንበኛቸው መፍተሄ ፈልጎ ሲመጣባቸው በብዛት የችግሩ መንስኤ የሆነው ወይ ጎረቤቱ፣ ወይ ዘመዱ ወይ ደግሞ የቤተሰቡ አባል እንደሆነ በመጠቆም ሰዎች ውስጣቸው እንዲሻክር አለመተማመን እንዲነግስ ያደርጋሉ። በድግምቶቹ ምክንያት የጤና መጓደል፣ የትዳር መፍረስ፣ የዝምድና መቆራረጥ፣ የጎረቤቶች በጎሪጥ መተያየት አልፎም ደም የሚያቃባ ግጭት እንዲከሰት ሁሉ ሰበብ ሊሆኑ ይችላሉ።

* ጠንቋይና ደጋሚ ዘንድ የሚሄድ ሰው የተነገረውን ባያምን እንኳን ከባድ ቅጣት ይከተለዋል። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።} [ሙስሊም፡ 5957]

2. ሌላው በ “ዘመን መለወጫ” አካባቢ የሚፈፀመው ጥፋት በአንዳንድ አካባቢ ያለው ጳጉሜን ተከትሎ ለዱዓህ መሰባሰብ ነው። እነዚህ አካላት የጳጉሜ ዱዓህ “መቅቡል ነው” (ተቀባይነት ያለው ነው) በማለት ነው ወቅቱን በዱዓእ የሚያሳልፏት። በጣም የሚገርመው ለዱዓህ የሚጥጠሩት እስልምናን ያውቃሉ ሰዎችን ያስተምራሉ የሚባሉት ሰዎች መሆናቸው ነው። ነብዩ ﷺ “አላህ እውቀትን ከባሪያዎቹ መንጠቅን አይነጥቅም። ይልቁንም ዑለማዎችን በመውሰድ (በመግደል) እውቀትን ይወስዳል። ከዚያም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ። በዚያኔ ሰዎች መሀይማንን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ። ሲጠየቁም ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ። በዚህም ይጠማሉ፣ ያጠማሉም” ማለታቸው ምንኛ የሚደንቅ ሐቅ ነው?! ዲን ያስተምራሉ ተብለው የሚታሰቡት አካላት ክርስቲያናዊ አቆጣጠርን መሰረት ያደረገ ዒባዳህ እየፈፀሙ ሰዎችን ወደ ጥፋት ሲወስዱ በገሃድ ይታያሉ።

3. ሌላኛው የ “ዘመን መለወጫን” ተከትሎ የሚፈፀመው ጥፋት መስከረም አንድን ወይም እንቁጣጣሽን ማክበር ነው። አቆጣጠሩ ሀገራዊ እንጂ እምነታዊ መሰረት እንደሌለው ሊያሳምኑ በከንቱ የሚዳክሩ ሰዎች አሉ። ነገሩ ሲበዛ ግልፅ ከመሆኑ ጋር በዚህ ላይ የሚሸወድ መኖሩ እጅጉን የሚደንቅ ነው። ብቻ ለማንም እንደማይሰወር ባስብም ለማስታወስ ያክል:-

* አቆጣጠሩ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው በሚሲዮናውያን መሆኑ፣
* አመቱ ሲፃፍ መጨረሻ ላይ “ዓመተ ምህረት” መባሉ፣
* የነብዩ ዒሳን (ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) መወለድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ መሞገታቸው
* እንዲሁም ይበልጥ ለማረጋገጥ የ “ዘመን መለወጫ” ወቅት ላይ ለምሳሌ “እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ፣ ... አደረሳችሁ” ማለታቸው አቆጣጠሩና በአሉ ሃይማኖታዊ መሆናቸውን አጉልተው የሚያሳዩ ነጥቦች ናቸው፡፡ ይህንን ስንል የሚደብራቸው ክርስቲያኖች አሉ። እኛኮ ዒድን አብራችሁን ካላከበራችሁ አላልንም። ሰው እንዴት የኔን እምነት ካልተከተላችሁ ብሎ ሌሎችን በአክራሪነት ይፈርጃል?!
የእምነታችንን ጉዳይ ለኛ ብትተውልን። እምነታችን ሌሎች ህዝቦች በሚልለዩባቸው እምነቶች፣ ባህሎችና ልማዶች መመሳሰልን አይፈቅድም። ነብያችን ﷺ “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 26/2007)
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor


📢 ይህ ነው መንሃጃችን።

ኢማሙ በርበሃሪይ በ4ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ(በሂጅራ) የነበሩ ታላቅ ዓሊም ናቸው። እኚህ ዓሊም ሸርሁ ሱና በተሰኘው ኪታባቸው፤ የአህሉ ሱና ወልጀመዓ ዓቂዳን በደንብ አብራርተዋል። እኚህ ታላቅ ዓሊም የኢማም አልመርወዚ ተማሪ ናቸው፣ኢማሙ አል–መርወዚ ደግሞ የኢማሙ አህመድ ኢብኑ ሃንበል ተማሪ ናቸው። ኢማሙ አህመድ ደግሞ የኢማሙ ሻፊዕይ ተማሪ ናቸው። ኢማሙ ሻፍዕይ ደግሞ የኢማሙ ማሊክ ተማሪ ናቸው። ኢማሙ ማሊክ ደግሞ የናፊዕ መውላ ዓብዱራህማን ኢብኑ ዑመር ተማሪ ናቸው። ናፊዕ ዓብዱራህማን ኢብኑ ዑመር ደግሞ የዓብደላህ ኢብኑ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ተማሪ ናቸው። ዓብደላህ ኢብኑ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ደግሞ የነብዩﷺ ተማሪ ናቸው። ነብዩﷺ ደግሞ ወህይን ከአላህ የሚቀበሉ የአላህ መፅእክተኛ ናቸው። ይህ ነው ዛሬ ዓቂዳችን እና መንሃጃችን ብለን የምንከተለው እንጂ፤ የዛሬ 200 እና 300 አመት የተፈበረከ አካሄድን አይደለም። በዚህ መንሃጃችን ችግር አለ የሚለን ካለ ቁርአን፣የነብዩﷺ ሀዲስ የቀደምቶቻችን ኪታቦች በመሃከላችን አሉ መነጋገር፣መወያየት እንችላለን።


♦️♦️♦️ትዳራዊ መርሆ

📌قال أبو الدرداء لأم الدرداء رضي الله عنهم: —

 ((إذا غضبت فَـرَضيِّني، وإذا غضبت رضيتك، فإذا لم نكن هكذا ما أسرع ما نفترق))

"ከተናደድኩ ደስ አሰኚኝ፣ ከተቆጣሽ ደስ አሰኚሻለሁ ይህ ካልሆነ ምንኛ አቻኮለው መለያየታችንን"

📚روضة العقلاء ١٠٦

ይህ መርሆ ተደርጎ ቢያዝ ኖሮ ትዳር ባልፈረሰ ነበር ሆኖም ግን ከሰው ብዙሃኑ የራሱን ጥፋት ሌሎች ላይ መለጠፍ ያስደሰተዋል ጥፋተኛ እሱ ቢሆንም እንኳ

📌እስኪ ነገረኝ ወንድሜ ባለቤትህ ጥፋት ስታጠፋ ታግሰህ መክራሀት ነው የምታሳልፈው ወይስ እሷ ላይ በመጮህና በመማታት ነው የምታሳልፍው⁉️

አብዛሃኛው ሚስቱ ላይ መጮህ ለመማታት መሞከር የተለያዩ ፀያፍ ቃላቶችን በመናገር ነው የሚያሳልፈው ግን ለምን ⁉️

ከዚህ ሁሉ የሚገርመው ብሯን ቅርጥም አድርጎ ከበላ ቡሃላ, ወጣትነቷን ከተጠቀመባት ቡሃላ,በጤንነቷ ግዜ አብሮ ከቧረቀ ቡሃላ እሷ ላይ አቃቂር ይጀምራል
ይሰድባታል ,ይዘልፋታል, ያወርዳታል… ግን ለምን ስትለው እፈታሻለሁ በማለት ያስፈራራታል ‼

ያረህማን አላህን ፍራ ወንድሜ

📌አላህ ያዘነላቸው ሲቀሩ አብዛሃኛው ሴቶች ባሎቻቸዉን መሳደብ, ማወራድ, ተስፋ እንዲቆርጥ ከዚህም የከፋው ለመማታት የሚሞክሩ አሉ ወላሂ ይህ አስነዋሪና በጣም ከባድ የሆነ ፀያፍ ድርጊት ነው ይህ ‼


♦️♦️♦️በጥቅሉ ወንድሜ አንቺም እህቴ ሚድያ ላይ ወጥቶ የሆነ ነገር ጫጭሮ የሰዉን ውዳሴ ማግኘት እወነተኛ ማንነታችንን አይገልፅም ።

ስለዚህ ሚድያ ላይ እየወጡ ሴቶች እያልክ ከምትሳለቅ ካጠገብህ ያለቺዉን ባለቤትህን ግዜ ሰጥታሃት ቁጭ ብለህ ብታቀራት

አንቺም የሚታመን ወንድ የለም እያለሽ ሮሮ ከማሰማት ቆም ብለሽ ማንነትሽን በታሰተካክይ መላስን ከማስረዘም ብትቆጠቢ መልካም ነው

ትዳር ላይ አሸናፊና ተሸናፊ የሚባል ነገር የለም የበታችና የበላይ የለም ባል በሚስቱ ላይ ሀቅ እንዳለዉ ሁሉ ሚስትም በባሏ ላይ ሀቅ አላት ስለዚህ አንዱ ያንዱን ሀቅ ሊወጣ ይገባል በዚህም ትደራቸዉን ይጠብቃሉ

የአላህን ሀቅና የፉጥሮችን ሃቅ ከሚወጡ ባሮች አላህ ያርገን

አሚን


አቡ አዒሻ ሙሀመድ ሰይድ ሙሀመድ

https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba


💎 እንቁ የሴቶች ምሳሌ 🌹

በኢማኗ የተራራን ያክል ጠንክራ ከፊርአውን እና ከጭፍሮቹ ፊት በሃቅ የቆመች በምድር ላይ ያለ የቅጣት አይነት ሲፈራረቅባት ምንም ያልተበገረች፣ በፊርአውን ቤተመንግስት ውስጥ ያለው የተትረፈረ ድሎት አኸይራን ያላስረሳት እመቤት አስያ አላህ ሱብሃነሁ ወተአላ እስከ ቂያማ ቀን ድረስ ስትዘከር እንድትኖር እና የጀግንነት ውሎዋ መብራት ነጸብራቁ ለወንዱም ለሴቱም ያበራ እና ምሳሌም ትሆን ዘንድ በሚያምረው የቁርአን ዘይቤ እንዲህ ሲል ይነግረናል።


وَضَرَبَ اللَّهُ مَثَلاً لِلَّذِينَ آمَنُوا امْرَأَتَ فِرْعَوْنَ إِذْ قَالَتْ رَبِّ ابْنِ لِي عِنْدَكَ بَيْتاً فِي الْجَنَّةِ وَنَجِّنِي مِنْ

فِرْعَوْنَ وَعَمَلِهِ وَنَجِّنِي مِنَ الْقَوْمِ الظَّالِمِينَ

✍ትርጉም፦
ለእነዚያ ለአመኑትም የፈሮንን ሴት አላህ ምሳሌ አደረገ፤ ጌታየ ሆይ አንተ ዘንድ በገነት ውስጥ ለኔ ቤትን ገንባልኝ፡ ከፈርኦን እና ከስራውም አድነኝ፡ ከበደለኞቹ ህዝቦችም አድነኝ ባለች ጊዜ።

አስያ አላህን የለመነችው ጸጋ በጀነት ቤት እንዲገነባላት ነበር እንጅ ዱንያዊ ጥቅም እና ብልጭልጩን አለም ከዚያ ከፊርአውን ቤተመንግስትም ቢሆን አላጣችውም ነበር።
በፊርአውን ትዝዛዝ እንደዚያ ስትቀጠቀጥ ሁሉን ነገር በትዕግስት ችላ እና ተቋቁማ የተቀደሰች ነፍስዋ ከሥጋዋ ተለይታ ወደ ተዘጋጀላት የክብር ማረፊያ በሄደበት ወቅት ከፊቷ ላይ ፈገግታ አልተለያትም ነበርና የሚያሰቃዩዋት ሰዎች ህይወቷ ማለፉን በቀላሉ አልተገነዘቡም ነበር።

አስያ ይህም ብቻ አልነበረም አስገራሚ ታሪኳ እና የኢስላም ባለውለታዋነቷ። ነብዩላህ ሙሳ ከቤታቸው ሲያድጉ በወቅቱ ፊርአውን ወንድ ልጅ የሚባል ሲወለድ በሚገድልበት ጊዜ እሷ ግን በዚያ አረመኔ ባሏ ቤት ነብዩላህ ሙሳ በእንክብካቤ እንዲያድጉ የተቻላትን ማድረጓን አሁንም ቁርአን እንዲህ በማለት ይገልጽልናል

وَقَالَتِ امْرَأَتُ فِرْعَوْنَ قُرَّتُ عَيْنٍ لِّي وَلَكَ لَا تَقْتُلُوهُ عَسَى أَن يَنفَعَنَاأَوْ نَتَّخِذَهُ وَلَداً وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

የፈርኦን ሚስት ለኔ የአይኔ መርጊያ ነው ለአንተም። አትግደሉት ሊጠቅመን ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው የከጀላልና፡ አለች እነሱም (ፍጻሜውን) የማያውቁ ኾነው (አነሱት)

https://t.me/Quran_Yelb_Brhan


ጥቂት ወሳኝ ነጥቦች በለይለተል ቀድር ዙሪያ
~
ለይለቱል ቀድር ማለት ትልቅ ደረጃ ያላት ለሊት ማለት ነው። ከፊል ዓሊሞች ዘንድ ደግሞ ፍጡራንን የሚመለከቱ የአመቱ ውሳኔዎች የሚተላለፍባት ለሊት ማለት ነው።
የለይለተል ቀድር ደረጃዎች፦
1. ቁርኣን የወረደባት ለሊት ነች። ጌታችን “እኛ (ቁርኣኑን) በለይለተል ቀድር አወረድነው”ብሏል። [አልቀድር፡ 1]
2. በሷ ውስጥ የተፈፀመ ዒባዳ ከሌሎች ለሊቶች ምንዳው የበለጠ ነው። አላህ “ለይለተል ቀድር ከሺህ ወር በላጭ ናት” ይላል። [አልቀድር፡ 3]
3. በሷ ውስጥ መላእክት ኸይርን ይዘው ወደ ምድር ይወርዳሉ። ጌታችን “በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ (ጂብሪል) በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ” ብሏል። [አልቀድር፡ 4]
4. ለሊቷ ዒባዳ የሚበዛባት፣ ሰላም የሚሰፍንባት ለሊት ናት። ጌታችን “እርሷ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት” ብሏል። [አልቀድር፡ 5]
5. የተባረከች ለሊት ናት። ጌታችን “እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ለሊት ውስጥ አወረድነው” ብሏል። [ዱኻን፡ 3]
6. በዚች ለሊት አላህ በአመቱ ውስጥ ያሉ የፍጡራኑን የእድሜና የሲሳይ ልኬታዎችን ይፅፋል። “በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል” ብሏል አላህ። [ዱኻን፡ 4]
7. በዚያች ለሊት ምድር ላይ የሚኖሩት የመላእክት ብዛት ከጠጠሮች ብዛት የበዛ ነው። [አልባኒ ሐሰን ብለውታል]
8. ለተጠቀመባትና አጅሩን ከአላህ ላሰበ ሰው ከወንጀል መማርያ ለሊት ነች። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “ለይለተል ቀድር አምኖና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል።” [ቡኻሪና ሙስሊም]
ስለዚህ ይህቺን ወሳኝና እጅግ የላቀ ዋጋ ያላት ለሊት ለማገኘት የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ሌሎችንም ልናበረታታ ይገባል። ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ለይለተል ቀድር በአመት ውስጥ የምትገኝ አንዲት ቀን ብትሆን እሷን ለማገኘት ስል አመቱን ሁሉ እቆም ነበር። በ(ረመዳን) አስር ለሊቶች ውስጥ ከሆነችማ ምን ነካህ? (እንዴት እዘናጋለሁ?!)” [በዳኢዑል ፈዋኢድ፡ 1/55]
ለይለቱል ቀድር የምትገኘው በየትኛው ጊዜ ነው?
የምትገኘው በረመዳን ብቻ ነው። ከረመዳንም በመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ። ነብዩ ﷺ “ይቺን ለሊት እየፈለግኩ የመጀመሪያውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ። ከዚያም መካከለኛውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ። ከዚያም (የሆነ አካል) መጥቶኝ ‘እሷ በርግጥም የመጨረሻው አስር ላይ ናት’ አለኝ” ማለታቸው ይህን ያስረግጣል።
ይቺ ታላቅ ለሊት እንዳታልፈን የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ይገባል። ነብዩ ﷺ በሐዲሣቸው እንዲህ ብለዋል፡- “በሱ ውስጥ ከአንድ ሺ ወር የምትበልጥ ለሊት አለች። የሷን ኸይር የተነፈገ በእርግጥም (ትልቅ ነገር) ተነፍጓል።” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2247]
መቼ እንፈልጋት?
ይበልጥ የሚገመተው ጊዜ 27ኛዋ ለሊት ናት። ይሁን እንጂ “ለይለተል ቀድርን በ23ኛዋ ለሊት ፈልጓት” ማለታቸው እንዲሁም “ለይለተል ቀድርን በመጨረሻዎቹ አስሩ (ለሊቶች) ፈልጓት። ከተረታችሁ በመጨረሻዎቹ 7 ላይ አትረቱ” ማለታቸው ለይለተል ቀድር ሁሌ በአንድ ለሊት ላይ እንደማትገደብ ያስረዳል። በተለይ ደግሞ በዊትሮቹ (21፣ 23፣ 25፣ 27፣ 29) የመሆን እድሏ ሰፊ ነው። ይህን አስመልክተው ነብዩ ﷺ “ለይለተል ቀድርን ከረመዳን በመጨረሻዎቹ አስሩ (ለሊቶች) በዊትሮቹ ፈልጓት” ብለዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
ይህ ማለት ግን ከነጭራሹ በሸፍዕ ለሊቶችም (22፣ 24፣ 26፣ 28፣ 30) አትሆንም ማለት አይደለም። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ “ከረመዷን የመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ፈልጓት። ዘጠኝ ሲቀረው፣ ሰባት ሲቀረው፣ አምስት ሲቀረው” ብለዋልና። ወሩ 29 ቀን ከሆነ 9፣ 7፣ 5 ሲቀር ዊትር የሚሆኑት ከመጨረሻ ወደ ኋላ ሲቆጠር ነው። ከመጀመሪያ ለሚቆጥር ግን ዊትር ሳይሆን ሸፍዕ ቁጥር ነው የሚሆኑት። ይህም ሸፍዕ ለሊቶችም ላይ የመሆን እድል እንዳለ ያስረዳናል። ቢሆንም ግን “ከ(መጨረሻው አስር) በዊትሩ ፈልጓት” ስላሉ ዊትሩ ላይ ይበልጥ ማተኮር ይገባል።
በለይለተል ቀድር ምን ይጠበቅብናል?
ዒባዳ ማብዛት። ነብዩ ﷺ “ለይለተል ቀድር አምኖና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል” ይላሉ። [ቡኻሪና ሙስሊም] እናም በዚች ለሊት ታላቅነትና መደንገግ አምኖ፣ ከዚያም ለመታየት ለጉራና መሰል አላፊ ኒያ ሳይሆን አጅሩን ከአላህ በማሰብ እንደሶላት፣ ዱዓእ፣ ቁርኣን መቅራት፣.. የፈፀመ ሰው ወንጀሉ ይታበስለታል ማለት ነው።
ምልክቶቿ
1. “በዚያን ቀን ማለዳ ፀሀይዋ ነጭ ሆና ጨረር ሳይኖራት ትወጣለች።” [ሙስሊም]
2. በዚያን ለሊት ዝናብ ሊዘንብ ይችላል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
3. ቀጣዩ ቀን አየሩ ሞቃትም ብርዳማም ሳይሆን የተስተካከለ ይሆናል። ፀሀይዋም ደካማና ቀይ ትሆናለች። [ሶሒሑል ጃሚዕ]
እነዚህ ምልክቶች ግን አንፃራዊ ናቸው ይላሉ ሸይኹል አልባኒ ረሒመሁላህ። በአካባቢው ባለው የአየር ሁኔታ ሊወሰን ይችላል። ስለሆነም በትክክል ለይለተል ቀድር በተከሰተበት ጊዜም እነዚህን ምልክቶች ብዙ የማያያቸው ሊኖር ይችላል።
ለይለተል ቀድር ለሰጋጆች ብቻ አይደለችም!
የወር አበባ ላይ፣ የወሊድ ደም ላይ ያሉ፣ መንገደኞች… የዚች ለሊት ትሩፋት አያልፋቸውም። ማስረጃው ጠቅላይ ነውና። ባይሆን ከሶላት ውጭ ባሉ ዒባዳዎች ላይ ሊበራቱ ይገባል። በዚያች ለሊት ዱዓእ ማብዛት ጥሩ ነው። እንዲያውም ሱፍያኑ ሠውሪ ረሒመሁላህ “በለሊቷ ከሶላት ይልቅ ዱዓእ እኔ ዘንድ የተወደደ ነው” ይላሉ።
ለይለተል ቀድር በአይን ትታያለች?
አንዳንዶች እግራቸውን ዘርግተው፣ እያወሩ ሰማይ ሰማይ ያንጋጥጣሉ። የሚጠባበቁት ተወርዋሪ ኮከብ ነው። እሱን ሲያዩ “አኑረን አክብረን” ብለው ይንጫጫሉ። ይሄ ባዶ እምነት ነው። ለይለተል ቀድር አላህ በአንዳንድ ባሮቹ ቀልብ ላይ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የመረጋጋት ወይም የመለየት ስሜት ከማሳደሩ ውጭ በአይን የሚታይ ነገር አይደለም። የሚታየው ምልክቶቿ እንጂ እራሷ አይደለችም። ሰዎች የሚጠበቅባቸውን ከተወጡ ለሊቱ ለይለተል ቀድር መሆኑን ባያውቁ እንኳን ትሩፋቷን አያጡም።
ለይለተል ቀድር እንደሆነ ውስጡ ያደረ ሰው ምን ያድርግ?
በተለይ ደግሞ ለሊቱ ለይለተል ቀድር እንደሚሆን ውስጣችንን ከተሰማን ይበልጥ ልናተኩርበት የሚገባን ዱዓእ “አሏሁመ ኢነከ ዐፉውዉን ቱሒቡል ዐፍወ ፈዕፉ ዐኒ” (“ጌታዬ ሆይ! አንተ በርግጥም ይቅር ባይ ነህ። ይቅር ማለትን ትወዳለህ። ስለሆነም ከኔ ይቅር በለኝ” የሚለው ነው። [አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል] ስለዚህ ዋናው ትኩረታችን የአላህን ይቅርታ ለማግኘት ይሁን።
ግን ለምን አላህ ለይለተል ቀድርን ስውር አደረጋት?
ዑለማዎች እንደሚሉት ታላላቅ ትሩፋቶች በሚገኝባቸው የረመዳን የመጨረሻ ለሊቶች ሙስሊሞች በዒባዳ ይበራቱና ይጠናከሩ ዘንድ ነው አላህ ይቺን ለሊት ስውር ያደረጋት። እናም ለይለተል ቀድርን እንዳታመልጣቸው ሲጣጣሩ ለይተው ቢያውቋት ሊኖራቸው ከሚገባው በበለጠ ለዒባዳ ይተጋሉ። በዚህም ይበልጥ ይጠቀማሉ። ለይተው ቢያውቋት ግን እሷ ብቻ ላይ አነጣጥረው ሌሎቹ ለሊቶች ላይ ይዘናጉ ነበር። እናም መሰወሯ ነብዩ ﷺ እንዳሉት ለኛ ኸይር ነው። [ቡኻሪ]
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሰኔ 29/2007)
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: አቡ ሙዓዝ (Abu muaz)
የቻት ሱሰኞች ሆይ! እውነት ይሆን⁉️


ቡዙዎቻችን ረመዳን ተጋመሰ ሄደብን ጓዙን ጠቀለለብን እንላለን ግን እውነት ይሆን⁉️

ሐቂቃ እኔ አፍራለሁ አዎ በጣም ነው የሚያሳፍረው እውነትም ያሳፍራል

ከስልካችን ተለያይተን ለአንድ ሰአት ያህል እንኳን ታግሰን ቁርኣን መቅራት ኪታብ መመልከት የማንችል ሰዎች ረመዳን ተጋመስብን ኡኡ ስንል ያሳፍራል‼️

እስኪ ወሏሂ አሏህን ምስክር አድርገን በኢንሷፍ እናውራ በነዚህ ባለፉት ቀናቶች ውስጥ በቀን ቁርኣን ስንቴ ገልፀናል? ስንቴ ኪታብ ተመልክተናል⁉️

ውይ ውይ ምን በሽታ መጣብን ሀቂቃ⁉️ሁሌም ቻት ቻት ቻት‼️

ደሞኮ ሞባይሉን የምናነሳው ኩቱቦቹን ለማየት ለመፈየድ ለመጠቀም ቢሆን መልካም ነበር ግን ነገሩ ልብ ወለድ ለመፃፍ ሆነብን እንጂ ገና ምን ልፃፍ ነው ሚያስጨንቀን

እናስተውል‼️

ቁርኣን ከመቅራት ኪታብ ከማፅናት ያገደኝ ለሰዎች የሚጠቅም ነገር እየፃፍኩ ሆኜ ነው ልትሉ ወይም ልንል እንችላለን ግን ይሄ መልስ የባሰ ጉድ ነው።

ከዚህ በታች ያለው የቁርኣን አንቀፅ ይመለከተናል


۞ أَتَأْمُرُونَ النَّاسَ بِالْبِرِّ وَتَنسَوْنَ أَنفُسَكُمْ وَأَنتُمْ تَتْلُونَ الْكِتَابَ ۚ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

እናንተ መጽሐፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በበጎ ሥራ ታዛላችሁን? ነፍሶቻችሁንም ትረሳላችሁን? (የሥራችሁን መጥፎነት) አታውቁምን?

ደረሶች ሆይ!!

እባካቹህ ባይሆን እቤታቹህ ስትቀመጡ እንኳ ኪታቦቻቹህን አገላብጧቸው እውነት ሚስቶቻችን ቃለ መጠይቅ ቢደረጉ የኔ ባል ጧትና ማራ ምሳም ሲበላ ኪታብ ያገላብጣል ይሉ ይሆን⁉️እኔ አልገምትም አሏህና ቤትሰብ ይፈረድ


ውይ ቻት!! ውይ ሶሻል ሚዲያ ወሏሂ አከሰረን አከሰረን አከሰረን!! እኔ ወሏሂ በጣም ነው የደበረኝ እንዴት ሂወታችንን እንዳበላሸው

በዚህ እድሚያችን ማንበብ መቅራት ኪታብ አገላብጠን ምልክት ማድረግ ስንችል ኪታቡ ተገዝቶ ቁጭ አለ ያአሏህ ያአሏህ ያአሏህ አሏህ ያስተካክለን

ቡዙ ኪታቦች ከቡዙዎቻችን ቤት ሊገኙ ይችላሉ ግን የመግቢያውን አንዱን ጥራዝ አንብቤ ጨርሸዋለሁ የሚል ወንድም አሏህ ካዘነለት ውጭ ይገኝ አይመስለኝም።

ቡዙ ወንድሞችኮ ቀን ላይ ከቻት ተላቀው መተኛት አቅቷቸው ተራዊህ መስገድ ተስኗቸው የሙተኙ አሉ

እየነገደ ውሎ ነው አትለው እያረሰ ውሎ ነው አትለው እየሸቀለ ውሎ ነው አትለው እንግዳሳ ቻት ብቻ‼️

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡

ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፡፡

አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡

t.me/abumuazhusenedris
t.me/abumuazhusenedris


Репост из: Sheik Abuzar Hassen Abu tolha
ስለ ፆም 7⃣0⃣ ጠቃሚ ነጥቦች.pdf
481.5Кб
ስለ ፆም 70 ጠቃሚ ነጥቦች

ትርጉም፦ ሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ ሀፊዘሁሏህ


➽ አንብቡት ትጠቀሙበታላችሁ!!!


https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha/5213

https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha/5213


Репост из: ᴀʜʟᴜ sᴜɴᴀ ᴡᴇʟ ᴊᴇᴍᴀ
50 ጾምን የሚመለከቱ ፈትዋዎች.pdf
4.9Мб
"50 ፆምን የሚመለከቱ ፈትዋዎች"

ፈትዋዎቹ ተመርጠው የቀረቡት

ከሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊህ አልዑሰይሚን ረሂመሁሏህ
እና
ከለጅነቱ አድዳኢማ ሊልቡሁሲ አልዒልሚየቲ ወልኢቅናእ ቢልመምለከቲ አልዓረቢየቲ አስ`ሱዑዲያ

ትርጉም:‐ አቡ ዓብዲልዓዚዝ/ዩሱፍ አህመድ ሃፊዞሁሏህ

በቻልነው ሁሉ ለሌሎች እንዲደርስ የበኩላችንን እናበርክት

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

كن على بصيرة

https://t.me/alateriqilhaq


ﻛَﺎﻥَ ﻋُﻤَﺮُ ﺑْﻦُ ﺍﻟﺨَﻄَّﺎﺏِ  ﺇِﺫﺍ ﺃَﺗَﻰ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﺃَﻣْﺪَﺍﺩُ ﺃَﻫْﻞِ ﺍﻟْﻴَﻤﻦِ
ﺳﺄَﻟَﻬُﻢْ : " ﺃَﻓِﻴﻜُﻢْ ﺃُﻭَﻳْﺲُ ﺑْﻦُ ﻋَﺎﻣِﺮٍ؟ " ﺣﺘَّﻰ ﺃَﺗَﻰ ﻋَﻠَﻰ ﺃُﻭَﻳْﺲٍ
 ، ﻓَﻘَﺎﻝَ ﻟَﻪُ: " ﺃَﻧْﺖَ ﺃُﻭَﻳْﺲ ﺑْﻦُ ﻋﺎﻣِﺮٍ؟ " ﻗَﺎﻝَ : ﻧَﻌَﻢْ، ﻗَﺎﻝَ: "ﻣِﻦْ
ﻣُﺮَﺍﺩٍ، ﺛُﻢَّ ﻣِﻦْ ﻗَﺮَﻥٍ؟ " ﻗَﺎﻝَ: ﻧﻌَﻢْ، ﻗَﺎﻝَ : " ﻓﻜَﺎﻥَ ﺑِﻚَ ﺑَﺮَﺹٌ
ﻓَﺒَﺮِﺋْﺖَ ﻣِﻨْﻪُ ﺇِﻟَّﺎ ﻣَﻮْﺿِﻊَ ﺩِﺭْﻫَﻢٍ؟ " ﻗَﺎﻝَ : ﻧَﻌَﻢْ، ﻗَﺎﻝَ: "ﻟَﻚَ ﻭﺍﻟِﺪَﺓٌ؟"
ﻗَﺎﻝَ : ﻧَﻌَﻢْ، ﻗَﺎﻝَ : "ﺳَﻤِﻌْﺖُ ﺭَﺳُﻮﻝَ ﺍﻟﻠَّﻪ ﷺ ﻳﻘﻮﻝ: ‏« ﻳَﺄْﺗِﻲ
ﻋﻠَﻴْﻜُﻢْ ﺃُﻭَﻳْﺲُ ﺑْﻦُ ﻋَﺎﻣِﺮٍ ﻣَﻊَ ﺃَﻣْﺪَﺍﺩِ ﺃَﻫْﻞِ ﺍﻟْﻴَﻤَﻦِ، ﻣِﻦْ ﻣُﺮَﺍﺩٍ، ﺛُﻢَّ
ﻣِﻦْ ﻗَﺮَﻥٍ، ﻛَﺎﻥَ ﺑِﻪِ ﺑَﺮَﺹٌ ﻓَﺒَﺮَﺃَ ﻣِﻨْﻪُ ﺇِﻟَّﺎ ﻣَﻮْﺿِﻊَ ﺩِﺭْﻫَﻢٍ، ﻟَﻪُ ﻭَﺍﻟِﺪَﺓٌ
ﻫُﻮ ﺑِﻬﺎ ﺑَﺮٌّ، ﻟَﻮْ ﺃَﻗْﺴَﻢَ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪ ﻷَﺑَﺮَّﻩُ، ﻓَﺈِﻥِ ﺍﺳْﺘَﻄَﻌْﺖَ ﺃَﻥْ
ﻳَﺴْﺘَﻐْﻔِﺮَ ﻟَﻚَ ﻓَﺎﻓْﻌَﻞْ ‏» ، ﻓَﺎﺳْﺘَﻐْﻔِﺮْ ﻟﻲ " ، ﻓَﺎﺳْﺘَﻐْﻔَﺮَ ﻟَﻪُ، ﻓَﻘَﺎﻝَ ﻟَﻪُ
ﻋُﻤَﺮُ : " ﺃَﻳْﻦَ ﺗُﺮِﻳﺪُ؟" ﻗَﺎﻝَ: ﺍﻟْﻜُﻮﻓَﺔَ، ﻗَﺎﻝَ: " ﺃَﻻ ﺃَﻛْﺘُﺐُ ﻟَﻚَ ﺇِﻟﻰ
ﻋَﺎﻣِﻠﻬَﺎ؟" ﻗَﺎﻝَ: ﺃَﻛُﻮﻥُ ﻓﻲ ﻏَﺒْﺮﺍﺀِ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﺃَﺣﺐُّ ﺇِﻟَﻲَّ , ﻓَﻠَﻤَّﺎ ﻛَﺎﻥَ
ﻣِﻦَ ﺍﻟﻌَﺎﻡِ ﺍﻟﻤُﻘﺒﻞ ﺣﺞَّ ﺭﺟﻞٌ ﻣﻦ ﺃﺷﺮﺍﻓﻬﻢ، ﻓﻮﺍﻓﻰ ﻋُﻤَﺮَ ,
ﻓَﺴَﺄﻟَﻪُ ﻋَﻦْ ﺃُﻭَﻳْﺲٍ , ﻓَﻘَﺎﻝَ: ﺗَﺮَﻛْﺘُﻪُ ﺭَﺙَّ ﺍﻟﺒﻴﺖ، ﻗﻠﻴﻞ ﺍﻟﻤﺘﺎﻉ ,
ﻗﺎﻝَ : "ﺳَﻤِﻌﺖُ ﺭَﺳُﻮﻝَ ﺍﻟﻠﻪِ ﷺ ﻳﻘﻮﻝ: ‏« ﻳَﺄْﺗِﻲ ﻋَﻠَﻴْﻜُﻢْ ﺃُﻭَﻳْﺲُ
ﺑْﻦُ ﻋَﺎﻣِﺮٍ ﻣَﻊَ ﺃَﻣْﺪَﺍﺩٍ ﻣِﻦْ ﺃﻫْﻞِ ﺍﻟﻴَﻤَﻦِ، ﻣِﻦْ ﻣُﺮَﺍﺩٍ , ﺛُﻢَّ ﻣِﻦْ ﻗَﺮَﻥٍ ,
ﻛَﺎﻥَ ﺑِﻪِ ﺑَﺮَﺹٌ ﻓَﺒَﺮَﺃَ ﻣِﻨْﻪُ ﺇﻟَّﺎ ﻣَﻮْﺿِﻊَ ﺩِﺭْﻫَﻢٍ , ﻟَﻪُ ﻭَﺍﻟِﺪﺓٌ ﻫُﻮَ ﺑِﻬَﺎ ﺑَﺮٌّ،
ﻟَﻮْ ﺃﻗْﺴَﻢَ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻷَﺑَﺮَّﻩُ , ﻓَﺈﻥِ ﺍﺳْﺘَﻄَﻌْﺖَ ﺃَﻥْ ﻳَﺴْﺘَﻐْﻔِﺮَ ﻟَﻚَ
ﻓَﺎﻓْﻌَﻞْ ‏»" ، ﻓَﺄﺗَﻰ ﺃُﻭَﻳْﺴًﺎ ﻓَﻘَﺎﻝَ: ﺍﺳْﺘَﻐْﻔِﺮْ ﻟِﻲ , ﻗَﺎﻝَ: ﺃﻧْﺖَ ﺃَﺣْﺪَﺙُ
ﻋَﻬْﺪًﺍ ﺑﺴَﻔَﺮٍ ﺻَﺎﻟِﺢٍ ﻓَﺎﺳْﺘَﻐْﻔِﺮْ ﻟﻲ , ﻗَﺎﻝَ: ﻟَﻘِﻴﺖَ ﻋُﻤَﺮَ؟ ﻗَﺎﻝَ: ﻧَﻌَﻢْ،
ﻓﺎﺳْﺘَﻐْﻔَﺮَ ﻟَﻪُ , ﻓَﻔَﻄِﻦَ ﻟَﻪُ ﺍﻟﻨَّﺎﺱُ , ﻓَﺎﻧْﻄَﻠَﻖَ ﻋَﻠَﻰ ﻭَﺟْﻬِﻪِ . ﺭﻭﺍﻩ
ﻣﺴﻠﻢ
➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️
የየመን ነጋዴዎች በመጡ ጊዜ ኡመር ረዲየሏሁ አንሁ ሁሌም ይጠይቅ ነበር፦ከእናንተ ዉስጥ ኡወይስ የሚባል ሰዉ አለ በማለት?
ታደረ ከለታት አንድ ቀንም ሰዎችን በጠየቀ ጊዜ አዎ አለ ይሉትና እንደዛ ሲፈልገዉ የነበረዉን ኡወይስን ያገኘዋል

ከዛም ኡመር ጠየቀዉ፦
አንተ ኡወይስ ኢብኑ ኣሚር ነህ?
ኡወይስም፦
አዎ
ኡመርም፦
ሙራድ ከተሰኘዉ ህዝብ ከዛም ከቀረን ነህ?
ኡወይስም፦
አዎ
ኡመርም፦
ባንተ ላይ መልጥ ነበረብህ ከዛም አንዲት ዲርሃም የምታክል ቦታ ሲቀር ዳንክ?
ኡወይስ፦
አዎ
ኡመር፦
እናት አላችህ?
ኡወይስ፦
አዎ
ኡመርም እንዲህ አሉ ፦
እኔ ረሱላችን እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦

🌷በእናንተ ላይ ኡወይስ ኢብኑ ኣሚር የሚባል(ከታብእዮች)የሆነ ከየመን ነጋዴዎች ጋር ይመጣል በሱም ላይ ለምጥ ነበረበት ከዛም የዲርሃም ያክል ቦታ ሲቀር ዳነ ለሱ እናት አለችዉ እሱም ጥሩን የዋለላት (ሃቋን የጠበቀላት ) ነች
ታዳ እሱ በአላህ ላይ እንኳን ቢምል ያጠራዋል
ምናልባት እስቲግፋር እንዲያደርግልህ መጠየቅ ከቻል ጠይቀዉ እስቲግፋር ያድርግልህ (ማህርታን ይጠይቅልህ)🌷ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ
ከዛም ኡመር እንዲህ አለዉ፦
እስቲግፋር አድርግልኝ (ማህርታን ጠይቅልኝ)?
ኡዎይስም ለዚህ ትልቅ ሶሃብይ ለኡመር እስቲግፋር አደረገለት...

ይህ ሰዉ ኡወይስ ምን ያክል ትልቅ ሰዉ ቢሆነዉ? ምንስ ቢሰራ ነዉ ይሄንን ያክል ረሱላችን ሳያዩት ያወደሱት?ኡመር እሱን ለማግኘት እንደዚህ የጓጉለት ታብዕይ ምን ጥሩ ስራ ቢኖረዉ ነዉ?

መልሱ በጣም ቀላልና አጭር ነዉ📌📌
እሱም፦
የእናቱን ሃቅ ስለጠበቀ ነዉ የእናቱን ሃቅ በመጠበቁ ምክኒያት ይህንን ደረጃ አግኝቷል!

አሏህ የወላጆቻችንን ሃቅ በመጠበቅ ላይ ያግዘን ፡፡
🎤ሙስሊም ዘግበዉታል

~አብዱ ሽኩር አቡ ፈዉዛን

የቴሌግራም ቻናላችን👇👇👇
https://t.me/abu_fewzan_abdu_shikur


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በቅርብ ቀን ኢንሻአላህ
~
http://t.me/IbnuMunewor


. አዲስ ሙሓደራ .

የሶላት አንገብጋቢነትበተመለከተ
በ አብዱ ሽኩር አቡ ፈዉዛን

https://t.me/abu_fewzan_abdu_shikur


አሰላሙዓለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካትሁ

#ማሳሰቢያ
በመጀመሪያ ሌሎችም ይሳተፉና ያውቁ ዘንድ እባችሁ ሼር አድርጉት። እንዲሁም የቴሌግራም ጓደኞቻችሁን ወደቻናሉ አድ አድርጓቸው።

ከክፍል አንድ ደርስ ላይ የወጡ ጥያቄዎች

#ኮፒ ማድረግ አይቻልም። መልስ ብቻ ወደ ግሩፖ ከገቡ በኋላ ይላኩ።
@ibnuteymiyayesunamedresagurep

እውነት ወይም ውሸት በማለት መልሱ።

1, الحمدلله
ማለት ምስጋና ለአላህ ይገባው ማለት ነው።

2, ሱሐባ የሚባለው ነብያችንን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን በህይወት የተገናኘ ከሆነ ነው።

3, የተቀጠፈ ሀዲስ ይዘው ማሊኪያዎችና ከፊል ሐናቢላዎች የወሩን ስም ሸህሩ ረመዷን አይባልም ይላሉ።

4, ረመዷን ማለት አቃጣይ ማለት ነው።

5, አንድ ካፊር ሰው የረመዷን ቀን ላይ ከሰለመ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ማታ ድረስ መፆም አለበት የዛን ቀን ቀደዋ ግን ማውጣት አለበት።

6, ለረመዳን ወር ለሁሉም ቀን የመጀመሪያ ዕለት ብቻ ንያ ማድረግ ይችላል።

7, እብድ የሆነ ሰው የረመዳን ቀን ላይ ቢድን የዛን ግማሽ ቀን መፆም ይወጅብበታል።

8, አንዳንዴ ንያን በምላስ መናገር ይቻላል።

9, የረመዳን ፆምና የሱና ፆም ንያው አንድ አይነት ነው።

አጭር መልስ አስቀምጡ።

1, ኪታቡ በማን ተዘጋጀ? ኩኒያቸው ማነው?

2, የኪታቡ አዘጋጅ መቼ ሞቱ?

3, የረመዳን ወር መስፈርቶችን ስንት ናቸው? ለስንት ይከፈላሉ? በደርሱ ውስጥ የተዳሰሱትን ዘርዝሩ።

4, ኡሱልዮች ዘንድ ሸርጥ ማለት ምን ማለት ነው።

5, ኒያ ማለት ከሸሪዓ አንፃር ምን ማለት ነው?

6, ረመዳንን ለመፆም መቼ ነው ንያ ማድረግ ያለበት? የተሰነዘሩ የተለያዩ አቋሞችን ጥቀሱ።

የቴሌግራም ግሩፑ ሊንክ
https://t.me/ibnuteymiyayesunamedresagurep
https://t.me/ibnuteymiyayesunamedresagurep


በራሱ ወጥመድ አጥምደው!
አይሁዶችና ምእራባውያን ሰዎችን የክህደትና የዋልጌነት መናኸሪያ ለማድረግ ሌት ተቀን ሳይታክታቸው ይደክማሉ ።
ይህንን የከረፋ አላማ ለማሳካትና ለማሰራጨት ኢንተርኔትን ትልቅ መሳሪያ አድርገው ይጠቀማሉ ። ከባድ ወጥመዳቸው ሆናል ።
ኢንተርኔትን ዲንህን ለመማርና መልካምን ለማሰራጨት ተጠቀምበት ።
ከሃዲያን የተንኮላቸው ምርኮኛ አያድርጉህ ።
ተውሒድን በመማርና በማሰተማር፣ ቁጥብነትን በመስበክና በመተግበር ክህደታቸውንና ብልግናቸውን ተዋጋበት — ኢንተርኔትን ።
የማይሹትን በጎ በማንበብና በማስራት በወጥመዳቸው አጥምዳቸው ‼ በመሳሪያቸው ውጋቸው ‼
በርታ ወንድሜ!
በርቺ እህቴ!

https://t.me/Muhammedsirage


✅💢ሶላት ከማሰላመታችን በፊት የሚባል ዱዓ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
« اللَّهُمَّ إِنِّي ظَلَمتُ نَفْسِي ظُلْمًا كَثِيرًا، وَلاَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلاَّ أنْت َ، فَاغْفِرْ لي مَغْفِرَةً مِنْ عِنْدِكَ ، وارْحَمْنِي، إنَّكَ أنْتَ الغَفُورُ الرَّحِيمُ»

✅ጌታዬ አሏህ ሆይ!ነፍሴን ብዙ መበደልን በድያለሁ፣ ከአንተ በስተቀር ወንጀሎችን የሚምር ማንም የለም፣ ካንተ ዘንድ የሆነ እዝነትህን ለግሰኝ፣ እዘንልኝም፣ አንተ መሀሪና አዛኝ ነህና!!!


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ጀናባን የሚመለከቱ ህግና ደንቦች
~
የቃላት መፍቻ፡-

1. መኒይ (የዘር ፈሳሽ)፡-

- በስሜት ተስፈንጥሮ ከእርካታ ጋር የሚወጣ ፈሳሽ ነው፡፡
- ለወንድ ወፍራምና (ወደ ቢጫነት የሚያደላ) ነጭ ፈሳሽ ሲሆን ለሴት ደግሞ ቀጭንና ቢጫ ነው፡፡ [ሙስሊም፡ 311] ሽታው ወደሊጥ ሽታ የቀረበ ነው፡፡ በሆነ ምክንያት እነዚህ መታወቂያዎች ሊቀየሩ ይችላሉ፡፡
- ከወጣ በኋላ የሰውነት መቀዝቀዝ (ፉቱር) ይከተላል፡፡
- ፈሳሹ ጦሀራ እንጂ ነጃሳ አይደለም፡፡ ይህን የሚደግፉ ሶሒሕ ማስረጃዎች መጥተዋል፡፡ [ሙስሊም፡ 694] [አልኢርዋእ፡ 1/197]
- በውንም ይሁን በህልም ከወጣ ገላን መታጠብ ግዴታ ነው፡፡

2. መዚይ፡-

- ግንኙነትን ሲታሰብ ወይም ሲፈለግ የሚወጣ ያዝ የሚያደርግ (የሚያጣብቅ)፣ ቀለም አልባ ቀጭን ፈሳሽ ነው፡፡
- አወጣጡ ከእርካታ ጋር አይደለም፡፡ ተስፈንጥሮ ስለማይወጣ መውጣቱ ላይስተዋል ይችላል፡፡
- ነጃሳ ስለሆነ የነካውን አካል ማጠብ ይገባል፡፡ ልብስን ከነካ ወይ ማጠብ ካልሆነ ቦታው ላይ ውሃ በመርጨት መብቃቃት ይቻላል፡፡
- የነካውን ቦታ እንጂ ገላን መታጠብ ግዴታ አይደለም፡፡
- ውዱእን ያፈርሳል፡፡

3. ወዲይ፡-

- ከሽንት በኋላ የሚወጣ ነጭ ሽታ አልባ ፈሳሽ ነው፡፡
- የሚያጣብቅ አይደለም፡፡
- ብይኑ ከሽንት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

4. ከሴቶች ብልት የሚወጣ እርጥበት፡-

- ከማህፀን የሚወጣ ቀጭን ፈሳሽ ነው፡፡ መጠኑ ከሴት ሴት ይለያያል፡፡
- ሴቷ መውጣቱንም ላታስተውለው ትችላለች፡፡
- አካልንም ልብስንም ቢነካ አይነጅስም፣ ጦሃራ ነው፡፡
- ውዱእን ግን ያፈርሳል፡፡ ከሁለቱም መፀዳጃዎች በኩል የሚወጣ ነገር ውዱእ ያፈርሳልና፡፡ አወጣጡ ቋሚ ከሆነ ግን ለያንዳንዱ ሶላት ወቅቱ ከገባ በኋላ ውዱእ እያደረገች መስገድ ይገባል፡፡ ውዱእ ካደረገች በኋላ ቢወጣ ቦታም አይሰጠውም፡፡

ገላን መታጠብ ግዴታ የሚሆነው መቼ ነው?
~ ~ ~ ~ ~ ~~
1. በውኑ ግንኙነት ከተፈፀመ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) #ቢፈስም_ባይፈስም ትጥበት ግዴታ ነው፡፡
2. በቀጥታ ግንኙነት #ባይፈፀምም የዘር ፈሳሽ (መኒይ) #ከእርካታ ጋር ከወጣ ትጥበት ግዴታ ነው፡፡
3. በህልሙ ግንኙነት እንደፈፀመ አይቶ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካገኘ መታጠብ ግዴታ ነው፡፡
4. በህልሙ ግንኙነት እንደፈፀመ አይቶ ነገር ግን ሲነቃ ምንም አይነት የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካላገኘ መታጠብ አይጠበቅበትም፡፡ ኡሙ ሱለይም ረዲየላሁ ዐንሃ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንዲት ሴት ኢሕቲላም ከሆነች (በህልሟ ግንኙነትን ካየች) የመታጠብ ግዴታ አለባትን?” ብላ ስትጠይቅ “ፈሳሽ ካየች አዎ” ሲሉ መልሰውላታል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
5. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካገኘ የመታጠብ ግዴታ አለበት፡፡
6. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ ፈሳሽ አገኘ፡፡ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) እንዳልሆነ እርግጠኛ ከሆነ የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ የነካውን ግን ሊያጥብ ይገባል፡፡ ብይኑ የሽንት ብይን ነውና፡፡
7. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ይሁን አይሁን #መለየት_ያልቻለው ፈሳሽ ካገኘ በሽታ ወይም በቻለው መንገድ ለመለየት ይሞክርና ጥርጣሬው መኒይ ወደመሆኑ ካደላ ይታጠብ፡፡ ጥርጣሬው መዚይ ወደመሆኑ ካደላ ግን በተለይም ከመተኛቱ በፊት ስለ ግንኙነት አስቦ ከነበር እንደ መዚይ ይቁጠረውና የነካውን ቦታ ብቻ ይጠብ፡፡ ገላውን የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ ቢታጠብ ከጥንቃቄ አንፃር የተሻለ ነው፡፡
8. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ይሁን አይሁን #መለየት_ያልቻለው ፈሳሽ ካገኘና ግምቱ ወደየትኛውም ካላደላ፣ ከመተኛቱ በፊት ስለ ግንኙነት #ያላሰበ ከሆነ ጉዳዩ አወዛጋቢ ቢሆንም ትክክለኛው ትጥበት የለበትም የሚል ነው፡፡ ቢታጠብ ከጥንቃቄ አንፃር የተሻለ ነው፡፡ [ፈታዋ ኢብኑ ዑሠይሚን፡ 11/161]

የጀናባ አስተጣጠብ ሁለት አይነት ነው፡፡

1. የሚያብቃቃ ማለትም ግዴታውን ለማውረድ የሚጠበቅ ሲሆን እሱም ሙሉ አካልን በውሃ ማዳረስ ነው፡፡ ባይሆን መጉመጥመጥና በአፍንጫ ውሃ መሳብ (ኢስቲንሻቅ) እንዳይረሳ፡፡ ለትጥበት ኒያ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ ጀናባ የማውረድ ኒያ ማለት ነው። አንድ ሰው ጀናባ ማውረድን ሳያስብ እንዲሁ ውሃ ውስጥ ዋኝቶ ቢወጣ መላ አካላቱ ውሃ መንካቱ ብቻ ጀናባው ለመውረዱ በቂ አይሆንም፡፡ ይስተዋል! ይህን ትጥበት ካደረጉ በኋላ ውዱእም ባያደርጉም መስገድ ይቻላል፡፡ ባይሆን ከትጥበቱ መሀል ውዱእ የሚያፈርስ ነገር መፈፀም የለበትም፡፡
2. ሌላኛውና በላጩ ግን በቅድሚያ ሁለት እጆችን መታጠብ፡፡ ከዚያም ኢስቲንጃእ ማድረግ፡፡ ከዚያም ውዱእ ማድረግ፡፡ ከዚያም ከእራስ ጀምሮ ቀሪ አካላትን ውሃ ማዳረስ፡፡ እግርን ከውዱእ ጋር ማጠብም ይቻላል፤ መጨረሻ ላይ ማጠብም ይቻላል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]

ማሳሰቢያ፡-
~~~~
ሴቷ ለትጥበት ስትል የፀጉር ጉንጉኗን የመፍታት ግዴታ የለባትም፡፡ ነብዩ (ﷺ): ኡሙ ሰለማህ ለጀናባ ወይም ለሐይድ ትጥበት ፀጉሯን “ልፍታው ወይ?” ብላ ስትጠይቃቸው “አይ! የሚበቃሽ ከእራስሽ ላይ ሶስት ጊዜ ውሃ ማፍሰስ ብቻ ነው” ብለዋታል፡፡ [ሙስሊም የዘገቡት ነው።] ስለዚህ ፀጉር ሳይፈታ ውሃ መድረስ ከተቻለ መፍታት አይጠበቅም ማለት ነው፡፡
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር 8/2008)
https://t.me/IbnuMunewor


▪️ቢሽር ቢን አልሀሪስ አላህ ይዘንለትና እንዲህ አሉ።

✅ ሰዎች ዘንድ እንድትወሳ ብለህ ምንም አትስራ። መጥፎ ስራህን (ሰዎች እንዳያውቁብህ) እንደምትደብቀው ሁሉ መልካም ስራህንም ደብቅ።

📚 [ سير اعلام النبلاء ]




Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ቀልብ የፅድቅም የጥፋትም የእዝ ማዕከል
~~~~ ~ ~ ~~~~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~~
ጀነት ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተከባለች፤ ጀሀነም ደግሞ ነፍስ በምትወዳቸው ሸይጧን በሚያስውባቸው አማላይ ነገሮች፡፡ በብዙ ሁኔታዎቻችን ከአረሕማን ይልቅ ለሸይጧን የቀረብን ነን፡፡ ዐይኖቻችን፣ ጆሮዎቻችን፣ እጆቻችን፣ እግሮቻችን፣ እንዲሁም ምላሳችን ለሸይጧናዊ ተልእኮ የሰሉ ናቸው፡፡ ቀላሉን አምላካዊ ክልከላ መታገስ አቅቶን ከባባድ ሸይጧናዊ ልፋት ላይ እንተጋለን፡፡ ሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች ለጥፋት ሲተባበሩ፣ አንዳቸው ብቻ ለሚበቁት ኸይር ግን ተባብረውም ይዝላሉ፡፡ ይሄ ሁሉ የሚሆነው እንግዲህ ማዕከሉን “ዋግ” ሲመታው ነው፡፡ ቀልብ በሺርክ፣ በቢድዐ፣ በስሜት፣ ለሙስሊሞች በምታረግዘው ክፋት፣ … ከተበከለች ታማ፣ ታውካ፣ አመርቅዛ ትሞታለች። ታዲያ ቀልብ ስትሞት ሞቷ ለኸይሩ እንጂ ለሸሩማ ኢንኩቤተር ትሆናለች - ክፉ የሸር መፈልፈያ። ብቻ ሂወቷ በኢማን ካልኩሌተር ሲሰላ ያለ ኢማን ሂወት የለምና ሞታለች - የምር ሞት! ከዚያስ? ከዚያማ ቀልብ ተበላሽታ ሌላው ሰውነት ምን ጤና ሊኖረው? የአካል እንቅስቃሴ በሙሉ ደመ-ነፍሳዊ ይሆናል። ተንቀሳቃሽ ሙት!!! ግድግዳ የተጠጋ እንጨት ሆኖ ሂወት እንዳለው ያስባል፡፡
ከዚህ በኋላ ዐይንም ዐይን ጆሮም ጆሮ አልሆነም፡፡ የሰማያትና የምድር አፈጣጠር፤ የሌሊትና የቀን መተካካት ለሱ ከታክሲዎች መተላፍ፣ ሽንት ቤት ደርሶ ከመመለስ ብዙም ልዩነት የለውም፡፡ ችግሩ ከማዕከሉ ነዋ!

(أَفَلَمۡ یَسِیرُوا۟ فِی ٱلۡأَرۡضِ فَتَكُونَ لَهُمۡ قُلُوبࣱ یَعۡقِلُونَ بِهَاۤ أَوۡ ءَاذَانࣱ یَسۡمَعُونَ بِهَاۖ فَإِنَّهَا لَا تَعۡمَى ٱلۡأَبۡصَـٰرُ وَلَـٰكِن تَعۡمَى ٱلۡقُلُوبُ ٱلَّتِی فِی ٱلصُّدُورِ)
((ለነርሱም በነርሱ የሚያውቁባቸው ልቦች ወይም በነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች ይኖሩዋቸው ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን እነሆ ዐይኖች አይታወሩም። ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ይታወራሉ፡፡)) (አልሐጅ፡ 46)

በሌላ በኩል ልብ ከተስተካከለች፣ በኢማን ከተዋበች፣ በተቅዋ ካሸበረቀች መላ ሰውነት ጤና ይኖረዋል፡፡ ፊትም ኑር ይላበሳል፡፡ ዐይኖች በሐራም አይገግሙም፡፡ ጆሮዎች ለሙዚቃ አይቆሙም፡፡ ምላስም የሀሜት ማሽን አትሆንም፡፡ ከውጭ ሙስሊም ያልሆነ ገፅታ እየተስተዋለ ምላስ “ዋናው ልብ ነው” እያለች አታሽቃብጥም፡፡ ማዕከሉ ነቅቶባታላ!
ልብ ስትስተካከል እውነተኛ ማንነት ይገኛል፡፡ ከውስጥም ሙስሊም፣ ከውጭም ሙስሊም! በሐያእ የለሰለሰ፣ በውጭ ገፅታው ያልተኮፈሰ፣ በልቡ የመጠቀ፣ ከእንቶ ፈንቶ የራቀ ልዩ ስብእና!!! አቡበክር አሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሁ ከሌሎች የመጠቁት በሶላትና በፆማቸው ብዛት አልነበረም፡፡ ይልቁንም ልባቸው ውስጥ በፀደቀ ነገር ነበር። ኢማን! የቀልብ ልዩ ክብር!!!
ባጭሩ ጥፋታችንም ልማታችንም ከልብ ጋር የተሳሰረ ነው ማለት ነው፡፡ ታዲያ እኔና እርሶ የቱጋ ነን? ሰገነት ወይስ ጫማ ተራ? ነው ወይስ መሀል ሰፋሪ? በሌላ አነጋገር ልባችን ጤነኛ ነው? በሽተኛ ነው? ወይስ ሙት ነው?
ለካ ይህንንም ለማወቅ ልብ ያስፈልጋል፡፡ ((ባለ ልቦናዎቹ እንጂ አይገነዘቡም)) አይደል ያለው ኻሊቁ?
አንተ ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው ጌታችን ሆይ! ልቦቻችንን ወደ ትእዛዝህ አዙርልን። በዲንህም ላይ አፅናን፡፡ አላሁመ ኣሚን፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ 2001)
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: ኢብኑ ተይሚያ የተውሂድ የሱና ቻናል
◾️ሶላቴ ከወንጀል የማያቅበኝ ለምንድ ነው⁉️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🌐ለታላቁ አሊም ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦

➡️ ጥያቄ⁉️
〰〰〰〰
♦️ሶላት እሰግዳለሁ። ነገር ግን የተወሰኑ ወንጀሎችን እፈፅማለሁ። በዚህ ላይ ምን ትመከወሩኛላችሁ? ለምንድ ነው ሶላቴ ከመጥፎ ነገር እንድታቀብ ያላደረገኝ?

➡️ መልስ‼️
〰〰〰〰
🔶መጀመርያ የምመክርህ ወደ አላህ እንድትመለስ ነው። እውነተኛ በሆነ መልኩ ወደ አላህ ዙር። እያመፅከው ያለውን ጌታ ትልቅነት አስተውል። ትእዛዙን ለሚጥሱ ሰዎች ያዘጋጀውንም ከባድ ቅጣት አስታውስ። ይህንን የአላህ ቃል አንብብ {{ባሮቼን እኔ መሓሪው አዛኙ እኔው ብቻ መኾኔንና ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መኾኑን ንገራቸው።}} (ሱረቱ አል-ሒጅር 49 - 50) አላህን መሀርታና ይቅርታውን ጠይቅ። ከቅጣቱንም ፍራ።

ያማ እየሰገድክ ነገር ግን ሶላትህ ከወንጀል ያልከለከለህ፦ ሶላትህ ላይ ጉድለት ስላለ ነው። ምክንያቱም ያቺ ወንጀልና ከአፀያፊ ነገር ትከለክላለች የተባለችዋ ሶላት ሙሉ የሆነችዋ ሶላት ናትና። እሷም ነብዩ ያሳዩት ከሆነው ጋር በተስማማ መልኩ የተሰገደቿ ሶላት ናት። ቀልብ ሶላት ላይ በማድረግና ሌሎችም ሶላት ውስጥ የሚሰሩ ስራዎች ሱና ላይ በመጣበት መልኩ ሲሆን ነው። እንጂማ የተሰገደ ሶላት ሁሉ ከወንጀልና ከፀያፍ ተግባር ይከለክላል ማለት አይደለም። አላህ እንዲህ ብሏል {{ከመጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ፡፡ ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፡፡}} (ሱረቱ አል-ዐንከቡት - 45) ይህ ማለት የሚከለክለው በትክክለኛው መልኩ የተሰገደ ሶላት ነው ማለት ነው።

المصدر: سلسلة اللقاء الشهري لشيخنا محمد بن عثيمين رحمه الله > اللقاء الشهري [1]

https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ለመስቀል አምላኪዎች
~~~~~~~
የመሲህ ባሮች ሆይ አንድ ጥያቄ አለን
የተረዳው ካለ መልሱን እንሻለን
ጌታ ግፍ አቅቶት ሰዎች ከገደሉት
አለቀ አከተመ የታል አምላክነት?!
ሰዎች የሰሩትን በሱ ላይ ሲያደርሱ
ጌታ ግብራቸውን ፈቅዶ ነው በራሱ?
እንዲያ ከሆነማ ምንኛ ታደሉ?!
ፍቅሩን ይቸራሉ ፈቃዱን ሲሞሉ::
ባደረሱት ሁሉ አልፎ ከተከፋ
እንግዲህ ምን ይባል?
ሀይሉ ከኮሰሰ ሀይላቸው ከሰፋ?!
ግን እንጠይቃለን ምላሽ አትንፈጉ
ማለባበስ ይቅር ይመለስ በወጉ።
ፈጣሪዋን አጥታ ዐለም ስትዋትት
ሰው ወደ ማን ነበር የሚያስበው ፀሎት?
ፍጡር ፈጣሪውን ካፈር ሲያደባየው
ሰባቱን ሰማያት ማነበር ያቆየው?
ምስማር ተቸንክሮ ሲያሸልብ ፈጣሪ
ዓለም ቀርታ ነበር ያለ አስተናባሪ?
የሰማይ መላእክት ምንኛ ለገሙ?!
እጁ ተቸንክሮ ዋይታውን ሲሰሙ?
እንጨቱም ታምር ነው አቅሙ መቋቋሙ
አምላክ ያክል ነገር ችሎ መሸከሙ
ስለቱስ ጭቃኔው ብረቱ ምስማሩ
አካሉን ሰንጥቆ ስቃይ ማሳደሩ
ጉድ በሉ እሄን ጌታ በአይሁድ የሚረታ
ማጅራቱን ታንቆ ታስሮ የሚመታ
ኋላስ ራሱ ነቃ ከሞት አንሰራራ
ወይስ ጌታ አገኘ ህይወት የሚዘራ?!
ጉድ በሉ ለቀብር ጌታ አቅፎ ለያዘ
የባሰም ሆድ አለ አምላክ ያረገዘ
ዘጠኝ ወር ታሽጎ ሲኖር በጨለማ
ሐይድ እየተጋተ ደም እየተጠማ
ብልት ቀዶ ወጣ አቡሻ ህፃኑ
አፉን ለጡት ከፍቶ አቤት ማሳዘኑ!
አስቡ እሄን አምላክ ሲጠጣ ሲበላ
ከዚያም ያስገባውን ሲያስወጣ በሌላ
ጌታዬ ከፍ አለ ከነሳራ ቅጥፈት
ሁሉም ይጠየቃል ለቀባጠረበት
የመስቀል ባሮች ሆይ ግራ ገባኝ እኔ
ያሽቀነጠረው ሰው ፅድቅ ነው ኩነኔ
ማቃጠል ሰባብሮ ፈቃጁን ጨምሮ
ህሊና ከዚህ ውጭ ይፈርዳል አምሮ?
አምላክ አቅም አንሶት ለተጠፈረበት
ሰብሮ እንደማቃጠል ጭራሹን አምሎኮት?!
እውነትም እርጉም ነው ለምንስ ይዘንጋ
በመሳለም ሳይሆን በእግር ይሰጥ ዋጋ!
ለተዋረደበት ጌታህ ከነነፍሱ
አንተ ካመለከው የሱ ነህ የነሱ?
‘ጌታን ስላዘለ’ ከሆነ አክብሮቲ
አስተዋሽ ቅርፃቅርፅ ቢሆን እንጂ እንጨቱ
መስቀሉ ከጠፋ ሺ ስንት አመታቱ?!
እንዲያ ከሆነማ ሂሳቡ ቀመሩ
ለመስገድ አትቦዝን ለየመቃብሩ
ያስታውሳልና ነገረ ስርኣቱ
ጌታህ ካፈር በታች ለነበረበቱ::
የመሲህ ባሪያ ሆይ ንቃ ተረጋጋ
ይሄ ነው እውነታው ካልፋ እስከ ኦሜጋ፡፡
ንቃ አታንቀለፋ

የኢብኑ ቀይም አልጀውዚያህ “አዑባደል መሲሒ ለና ሱኣሉን” ድንቅ ግጥም ግርድፍ ትርጉም፡፡ ግጥሙን “ኢጋሠቱል ለህፋን ኪታቡ ገፅ 2/290 ላይ ያገኙታል፡፡ የግጥሙን አሪፍ የቪዲዮ ቅንብር ደግሞ ከፍቺው ጋር ከስር ይመልከቱ፡፡
ትርጉም: ኢብኑ ሙነወር

Показано 20 последних публикаций.

89

подписчиков
Статистика канала