የሩብ ጉዳይ ሀሳቦች
አንዳንዴ ስለ ውስን ጉዳዩች እና ሀሳቦች (On specific Cases and Thoughts) ሳስብ የእኛ ድርሻ እጃችንን ወደ እሳት ውስጥ ከመክተት መከልከል እና መከልከል ብቻ የሆነበት አማራጭ ብቻ ያለበት ሁኔታዎች አሉ በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ መጀመሪያ ማድረግ ያለብን ነገር እጃችንን ከዚህ እኩይ ተግባሩ መከልከል ነው፡፡ እሳት ካሉት ባርያት ውስጥ ማቃጠል አንዱ ባህሪው ነው እሳትን የፈጠረውም ፈጣሪነት የባህሪው ነው ማንም የማይነጥቀው ማንም የማይሰጠው እሳቱን የለኮሰውም ሰው በዚህ ዓለም ላይ ሲኖር ምናልባት ትልቁ የሕይወት ግቡ ያንን እሳት መለኮስ ብቻ ነው ከዚህ የተለየ ግብ የለውም ስለዚህ ስለ እሳቱ ፈጣሪም ስለእሳቱ ባህሪም ስለ እኛ መቃጠልም እሚገደው ነገር የለም እና አንዳንድ ጊዜ የእኛም ድርሻችን እጃችንን መሰብሰብ ብቻ የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡ እሳት ማቃጠሉን ትቶ ብርሃኑን ብቻ እንዲሰጠን መጠበቅ የዋህነት (naïve) መሆን ነው ከተቃጠሉ በኋላ የማይገኝ ተአምራትን ከመጠበቅ ይልቅ በራሳችን እጅ ያለውን ማንም የማይነጥቀንን የመምረጥ ምርጫችንን እንምረጥ፡፡