Book Recommendation
መልክአ ስብሐት
ስብሐትና ሚቶሎጂ (በቴዎድሮስ ገብሬ )
እስካሁን ስንመለከት እንደቆየነው ስብሐት-ልማዱ ማለቴ ነው በይነ ዲስፕሊናዊ ነው በሚቶሎጂ አማካኝነት ደግሞ ይህ ልማድ ወደ በይነ ባህላዊነት (Intercultural/ነት) እና በይነ- ቴክስታዊነት/ድርሰታዊነት (Intertextual/ነት) ይሸጋገራል በግልባጩም ይህንኑ ዓይነት ንባብ በይነ-ዲሲፒሊናዊ፣ በይነ -ባሕላዊና በይነ-ቴክስታዊ ንባብ-ከተደራሲው ይማጸናል ሚት እና ሪችዋል (አምልኮታዊና መንፈሳዊ ሥርዓት) በስብሐት ድርሰቶች ውስጥ ትልቅ ሥፍራ አላቸው ሚት ለእነዚህ ሥራዎች በቋንቋ አጠቃቀም ረገድ ዓብይ የዘይቤ ፣ የትእምርትና የምስል መፍጠሪያ ስልት ነው፡፡ ሚት ከቴክኒክና ከስልት ባላነሰ የጭብጥና የርእዮተ ዓለም ጣጣም ነው፡፡ በብሉይ ምሥልነት (በአርኪታይፕነት ) በአንድ በኩል ለረቂቁ ግለሰባዊ መልክአ ልቡና ማደሪያነት ይውላል በሌላ በኩል ለማኅበሩ የወል ርዕዮትና የጋራ ንጽረተ ዓለም መከሰቻነት ያገለግላል፡፡
inbox me at https://t.me/yosefdibaba for the PDF file