...አንዲት ጠብታ የምትፈጥረው ጢንጥዬ ማዕበል /Vibration/ (ዮሐንስ አድማሱ ለመምቴ የሚላት) ደግሞ የሌላውን ለመምቴ ትነካለች እኒህ የሃሳብ፣ የስሜትና የድርጊት ለመምቴዎች በሌላኛው ተፈጥሮ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አላቸው በበጎም በክፉም ተመልሰው ግን ወደ ምንጫቸው ይመጣሉ በመዋኛ ገንዳ ውስጥ የፈጠርከው የውሃ እርግብግቢት የገንዳውን ግድግዳ ገጭቶ ወዳንተ እንዲመለስ ማለት ነው እንግዲህ ከኔ ቤት ላይ የረጨኸው እሳት ከሆነ ነበልባሉ ያንተን ቤት ይነካል ሽቶ ስትረጨኝ የመዓዛው ቅንጣቶች ለአፍንጫህ ውብ ጠረን ይለግሳል Law of cause and effect እንደሚለው “You reap what you saw” ሰው የዘራውን ያንኑ ደግሞ ያጭዳል ይህን ነገር ምስራቃዊው ነጽሮተ-ዓለም Karma ሲለው ሌሎች ደግሞ Boomerang ይሉታል Boomerang አውስትራሊያኖቹ አቦርጂኒስቶች ከእንጨት የሚሰሩት ደጋን ቅርጽ ያለው የአደን መሳሪያ ሲሆን ወርዋሪው ዘንድ ተመልሶ እንዲመጣ ተደርጎ ዲዛይን የሚደረግ ነው የእኔና ያንተ ቡሜራንግ ምን ይሆን? ምንድነው ለሌሎች እየሰጠን ያለነው? ለሃሳብ፣ ለስሜትና ድርጊትህ መጠንቀቅ የሚኖርብህ ወላፈኑ ‘ለእኔም’፣ ‘ለእርሷም’፣ ‘ለእነርሱም’ እንደሚተርፍ በማሰብ ነው ምክንያቱም …
ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም በአንድ ድንቅ ግጥሙ ላይ እንዲህ ብሏል…
“… ይችላል ይሉሃል ፍልሚያ ማዘጋጀት
ያባት አጥንት ወስዶ ስሎ ጦር ማበጀት
አንተው ጦር ወርውረኽ አንተው ቀድመኽ ወደቅኽ
አካሌ ደረቴ መኾንህን መች አወቅኽ ?” ይቀጥላል.......