Book Recommendation
ልጅነት ከሰለሞን ደሬሳ
የግጥም ቅርፅ ቃላትን ለክቶ ከመደርደር ብቻ አይወለድም፡፡ የኑሮ አላማ እንደ ክብሪት ዋጋ ቁርጡ ባይገለጥልንም አላማ ለመኖሩ የፍጡሩ ከእለት ወደ እለት መፍጨርጨር በቂ ጠቋሚ ነው፡፡ የግጥም ፈንታ ይህን ግላዊ መፍጨርጨር (የትንኝ መፍጨርጨርም ቢሆን ) ከዚህ ዓለም ችላ ባይነት ጋር አያይዞ ማብላላት ይመስለኛል ፡፡ ማብላላት ማፋጨት እያፋጩም ተቃራኒዎችን ማጣመድ ተመሳሳዮችን መለያየት፡፡ ከግጭታቸው ላንዳፍታ እንደ በራሪ ኮከብ የሚታይ ግልጥ መፍትሔን ማዋለድ፡፡ መለስ ብለው ተዳኘኝ ቢሉት ምፍትሔው እየተለዋወጠ ቢያስቸግርም ጉድለት መስሎ አይታየኝም፡፡ አለዚያማ ቁልጭ ያለች ተነጣጥራ የተወረወረች የጋዜጣ ርዕሰ አንቀፅ ትሻል የለ? ለሁሉም በአንዴ የምትገባ ማንም ተመልሶ የማያነባት ፡፡ በዶማ ግንድ እንደማይፈለጥ በመጥረቢያ አትክልት አይኮተኮትምና ፡፡
የግር ጣት
የረጋ ደመና ሲያንዣብብ
ተኮራመት አታሸቅብ
ወርጭቶ ጠጠር ሲጥል
ቀና አትበል
ብርጭቆ ቤት አትጠለል
አያፍርም ይፈነዳል
ላይን አይሆን ጥርስ ይሸርፋል
ሰዎች ሁሉ አቆልቁሉ
የግር ጣት ቁጠሩ
በሙሉ ጥርስ እንድታምሩ
inbox me at https://t.me/yosefdibaba for the PDF file.