መላእክት ከጌታ ጋር ነበሩ:: በዲያቢሎስ በተፈተነ ጊዜ “ቀርበው አገለገሉት” (ማቴ. 4:11) ወደ መስቀል ሲሔድ ተጨንቆ ሲጸልይ “የሚያበረታው መልአክ ታየው” (ሉቃ. 22:43) ዕርቃኑን ሲሰቀል አዝነው “በማይታይ ክንፋቸው ጋረዱት” (መጽሐፈ ቅዳሴ) ከሞት ሲነሣ በባዶ መቃብሩ ነጭ ለብሰው ቆሙ:: እንደሞተ አስበው ሽቱ ሊቀቡት ለመጡት ሰዎች “ሕያዉን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል” ብለው መለሱአቸው:: ሲያርግም በእልልታና በመለከት ድምፅ አጀቡት::
መላእክት ለክርስቲያን ሁሉ እንዲህ ናቸው:: በዲያቢሎስ ስትፈተን ቀርበው ይደግፉሃል:: በመከራ ስትጨነቅ ያበረቱሃል:: ዓለም ዕርቃንህን ስትሰቅልህ ከውርደት በክንፋቸው ጥላ ይከልሉሃል:: ከኃጢአት ሞት በንስሓ ስትነሣ እንደ ሰርገኛ ነጭ ይለብሳሉ:: “ሞቶአል ሸትቶአል” ብለው ሽቶ ሊቀቡህ ለሚመጡ ሰዎች “ሕያዉን ከሙታን መካከል ለምን ትፈልጉታላችሁ? ተነሥቶአል!” ብለው ትንሣኤህን ያበሥራሉ:: ከንስሓ በኋላ ከምድር ከፍ ልበል ብለህ ወደ ቅድስና ሥራ ያረግህ እንደሆነ በእልልታ ያጅቡሃል::
#share
▫️@diyakonhenokhaile
https://t.me/diyakonhenokhaile

መላእክት ያላጀቡት ክርስቶስ መላእክት የሌሉበት ክርስትና የለም!
#share
▫️@diyakonhenokhaile
https://t.me/diyakonhenokhaile