"፭ኛ ኮርስ "ነገረ ማርያም"
#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌷🌹🌺
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
፪.፩.፫, #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም
#ከጌታ_ጽንሰት_እስከ_ቀራኒዮ_ያደረገችው_አገልግሎት
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በእግዚአብሔር ተመርጣ እናት እንደምትሆነው በነቢያት በተነገረው ትንቢት መሠረት አምላክ ዓለሙን ለማዳን የቀጠሮው ጊዜ ሲደርስ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ እመቤታችን ላከው እርሷም ሀርና ወርቅ እያስማማች ስትፈትል ልብሱን እየታጠቀ እየፈታ ለእርሷ የሚገባውን ክብር ሰጥቶ እያመሰገናት ለእግዚአብሔር እናት እንድትሆነው መመረጧን ነገራት እርሷም እኔ ወንድ ስላማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? ብላ ጠየቀችው እርሱም “ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም” አላት። እመቤታችንም እኔ የእግዚአብሔር አገልጋይ (ገረድ) ነኝ እንደ ቃልህ ይደረግልኝ አለችው።
በዚህ ጊዜ አካላዊ ቃል ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በተለየ አካሉ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፈስ ነስቶ የዕለት ፅንስ ሆኗል። (ሉቃ 1፥26)
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አገልግሎት ከዚህ ይጀምራል። እግዚአብሔር ዓለሙን ለማዳን በወደደ ጊዜ እሺ ብላ እመቤታችን ፍቃደኛ በመሆኗ ከእርሷ ሰው ሆኗልና አባቶቻችን በነገረ ማርያም እንደሚያስተምሩት እመቤታችን በቤተ መቅደስ ሳለች መጽሐፈ ኢሳይያስ ስትመለከት ከትንቢተ ኢሳይያስም 7፥14 ላይ ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል። የሚለውን ስታነብ ከዚች ድንግል ከዘመኗ ደርሼ እንጨት ሰብሬላት ውሃ ቀድቸላት ገረድ ሆኜ ባገለገልኳት ብላ ተመኝታ ነበር።
አምላካችን ልዑል እግዚአብሔርም ትህትናዋን ተመልክቶ ለበለጠው አገልግሎት ለእናትነት መረጣት እርሷም በህቱም ድንግልና ፀንሳው በህቱም ድንግልና ወለዳዋለች።
መላእኩ ለአረጋዊ ዮውሴፍ ሕፃኑን ከእናቱ ጋር ይዞ ወደ ግብጽ እንዲሰደድ ከነገረው አስነስቶ ንጉሥ ሄሮድስ ሙቶ እስኪመለሱ ድረስ እመቤታችን ብዙ ችግሮችን አይታለች/ተንከራታለች።....
#ከጌታ_ጽንሰት_እስከ_ቀራኒዮ_ያደረገችው_አገልግሎት
...እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማስተማር ዘመኑም ከጌታችን አልተለየችም በቅዱስ ወንጌል “የመጀመሪያው ተአምር” ተብሎም የተመዘገበው ተአምር የተከወነው በእመቤታችን ምልጃ ነው። ይኸውም የውሃው ወደ ወይንነት መለወጥ ነው። (ዮሐ 2፥1-11)
በስተመጨረሻም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለድኅነተ ዓለም በመልዕልተ መስቀል በተሰቀለ ጊዜ ከመስቀል ሥር ነበረ። ልብን በሚያቃጥል እንባ እያለቀሰች ታዝን ነበር። ከእርሷ ጋር እነ ሰሎሜ፣ እነ ማርያም መግደላዊት ሌሎችም ሴቶች ከደቀ መዝሙርቱም ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ቁመው አብረው ያለቅሱ ነበር።
ጌታችንም ለድንግል ማርያም ዮሐንስን እነሆ ልጅሽ አላት ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስን ደግሞ ድንግል ማርያምን “እናትህ እነኋት” አለው። ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ወደ ቤቱ ወሰዳት። (ዮሐ 19፥26)
ለጊዜው በዮሐንስ አማካኝነት እመቤታችን ለሐዋርያት በእናትነት መሰጠቷን፤ እርሷም እነርሱን በፀጋ ልጅነት መቀበሏን ያሳያል። ለፍጻሜው ግን እኛን ሁላችንን በፀጋ ልጅነት ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም መስጠቱን እና ለእኛ ለሁላችን ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በፀጋ እናት አማላጅ አድርጎ መስጠቱን የሚያመለክት ኃይለ ቃል ነው።
ለዋርያትም ከጌታችን ሞት እና ትንሣኤ እንዲሁም በ40ኛው ቀን ማረግ በኋላ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋውን እንደሰሙ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል በማርቆስ እናት ቤት ዘግተው ደጅ ሲፀኑ (ሲፀልዩ) በመካከላቸው እመቤታችን አብራ እንደነበረች ቅዱስ ሉቃስ በግብረ ሐዋርያት መጽሐፍ ምስክር ሁኗል። (ዮሐ ሥራ 1፥14)
“እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር” እንዲል። ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ለስብከት በየአህጉሩ ሲፋጠኑ እመቤታችን አልተለየቻቸውም ነበር። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታት ድርሰቱ“ ሞገሰ ስብከቶሙ ለሐዋርያት” ብሎታል። ትርጉም የሐዋርያት የስብከታቸው ሞገስ አንቺ ነሽ ማለት ነው።
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን አገልግሎት ለመግቢያ ያህል ጠቀስን እንጅ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አገልግሎት ከነቢያት ከሐዋርያት ከቅደሳን ሁሉ የበለጠ በፍፁም እምነት ከእናተነት ፍቅር ጋር ልዑል እግዚአብሔርን ያገለገለች እናት ናት።
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
#ቀጣይ_ትምህርታችን-->የእመቤታችን ልደት በነገረ ድኅነት
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯