#ክብሬን ለሌላ፣ ምስጋናዬንም ለጣዖት አልሰጥም
በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን፣ ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛ አምላክ ቅድስት ሥላሴ፡፡ በዘፍጥረት 18÷1 “እግዚአብሔር በመምሬ ዛፍ ስር ለአብርሐም ተገለጠለት። አብርሐምም ዓይኑን አነሳና ሦስት ሰዎችን አየ” የሚል ቃል አለ፡፡ ይህ ድንቅ ምስጢር እግዚአብሔር በሶስትነቱ በሰዎች አምሳል ለአብርሐም መገለጡን በቁጥር ሶሰት ብሎ ያስረዳል። አንዳንዶች ይህ ሀሳብ ስለሥላሴ አይደለም የሚል ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ መጽሐፉ ግን “እግዚአብሔር ከሶስት ሰዎች ጋር ወይም ከሁለት መላእክት ጋር ተገለጠለት” አይልም። ወይም መላእክትም ሆኑ ሰዎች በዚህ ሥም አይጠሩም፤ በኢሳ 42÷8 “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜም ይህ ነው! ክብሬን ለሌላ፣ ምስጋናዬንም ለጣዖት አልሰጥም።” ይላልና፡፡ በማያወላዳ ሁኔታ ሦስት ሰዎችን አየ” ብሎ ለይቶ ስለተናገረ እግዚአብሔር ሦስትነት ያለው መሆኑን በግልጽ ያስረዳል።
ሥላሴ፣ ሠለሰ ሶስት አደረገ፤ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን፤ ሥላሴ ማለት ሶስትነት ማለት ነው። የምሥጢረ ሥላሴን ትምህርት ስንማር ከሂሳብ ቀመር ሕግ አስተሳሰብ ነጻ መሆን ያሻል። ምክንያቱም መንፈሳዊዉ ጥበብ ሥጋዊዉን ጥበብ ወይም ፍልስፍና ይመረምረዋል እንጅ መንፈሳዊ ጥበብና ምሥጢር በዓለማዊ ዕውቀትና ምርምር ሊደረስበት አይቻልምና። የሃይማኖት ነገር ቁሳዊ ሳይሆን መንፈሳዊና በሃይማኖት ሆኖ በመንፈሳዊነት የሚታወቅና የሚታመን ነው። ለምሣሌ ሰዎች በጸበል ይድናሉ፡፡ አንዱ ጸበል ሁሉን አይነት በሽታ ይፈውሳል፡፡ በዓለም ሕክምና ግን የአንደኛው መድኃኒት ለአንዱ መርዝ ነው፡፡ መንፈሳዊው ሕክምና ጸበል ግን ጤነኛ ቢጠጣው መጠበቂያ፣ ሕሙም ቢጠጣው ፈውስ ነው፡፡ የሥላሴን አኗኗር በስጋዊ ስሌት የማንመረምረውም መንፈሳዊ በመሆኑ ነው፡፡
ሥላሴ የሚለው ስም የአንድነትና የሶስትነት ስም ነው፡፡ በስም፣ በግብርና በአካል ሶስት እንላለን፡፡ ለአብ ፣ ለወልድ፣ ለመንፈሰ ቅዱስ ለየራሳቸው ፍፁም ገጽ፣ ፍፁም መልክ፣ ፍፁም አካል፣ አላቸው። አካል በአጠቃላይ ሙሉው የሰውነታችን ክፍል ነው። የፍጡራን አካል የሚታይ፣ የሚዳሰስ፣ የሚመጠን፤ የሚወሰን፣ ሲሆን የሥላሴ አካል ግን፤ የማይታይ ፣ በእጅ የማይዳሰስ፣ በቦታ የማይወሰን፣ በሁሉም ምሉዕ ነው። በመዝሙር 138÷7 እንደተጻፈው በሁሉ የመላ ነውና፡፡ “ከመንፈስህ ወዴት እሔዳለሁ፤ ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ አለህ፤ ወደ ውቅያኖስም ጥልቅ ብወርድም በዚያ ትገኛለህ፤ እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ ከአጽናፍ አጽናፍ ብበርም እጅህ በዚያ ትመራኛለች ቀኝህም ትይዘኛለች” ይላል፡፡
የቅድስት ሥላሴ ስማቸው ከአካላቸው፣ አካላቸው ከስማቸው ሳይቀድም ከዓለም በፊት የነበረ ስም ነው እንጂ ኋላ የተገኘ አይደለም፡፡ ቅድምናቸው ዘመኑን ቢወስነው እንጂ ዘመኑ ቅድምናቸውን አይወስነውምና፡፡ የእግዚአብሔርን አንድነት በባህርይ፣ በህልውና፣ በፈቃድ፣ በሥልጣን፣ በመፍጠር በመሳሰሉት፡፡ የሰው ነፍስ የቅድስት ሥላሴ ምሳሌ ናት፡፡ ይኸውም አብ በልብ፣ ወልድ በቃል፣ መንፈስ ቅዱስ በእስትፋስ ይመሰላሉ፡፡ በእግዚአብሔርነቱ፤ ልብ፣ ቃል፣ ሕይወት አለ። ነፍስ ሶስት ባህርያት ቢኖሯትም አንድ እንደምትባል እግዚአብሔርም ሶስት ስም፤ ሶስት ግብር፤ ሶስት አካል፤ ቢኖረውም አንድ አምላክ እንጅ ሶስት አማልክት አይባልም፡፡ የቅድስት ሥላሴ ምሕረትና ቸርነት አይለየን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯