"፭ኛ ኮርስ "ነገረ ማርያም"
#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
፪.፪, #ክብረ_ድንግል
፪.፪.፩, #የአምለክ_እናት_መሆኗ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት መሆኗ በቅዱሳት መጻሕፍት የተመሰከረ ነው። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ በትንቢቱ እንዲህ ብሎ ተናግሯል። “ሕፃን ተወልዶልናልና፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶልናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘለዓለም አባት፣ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ኢሳ 9፥6 ይህም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ” ተብሎ የተነገረለት የባህርይ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
እርሱን የወለደች ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት በሌላም ሥፍራ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ብሏል “ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ተብሎ ይጠራል” ኢሳ 7፥14 “አማኑኤል” ማለትም የእግዚአብሔር መላአክ እንደተረጎመው እግዚአብሔር ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስ ነስቶ ሰው ሆነ ማለት ነው ይህም የባህርይ አምላክ ነው በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደችው ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ስለዚህ የአምላክ እናት መባል ይገባታል። (ማቴ 1፥23)
ቅድስት ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተመልታ ድንግል ማርያም የአምላክ እናት መሆኗን ስትመሰክር "የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?" ብላለች። (ሉቃ 1፥43)
ድንግል ማርያም በቅድምና ለነበረው አካላዊ ቃል ለእግዚአብሔር ወልድ እናቱ ናት። (ዮሐ 1፥1-14) ከእርሷ የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው። (የሐዋ. ሥራ 20፥80) ስለዚህም ነው የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ የምንላት በዘመኑ ፍጻሜ የሌለው ከእርሷ የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር የባህርይ ልጅ አምላክ ወልድ አምላክ ነው። (ገላ 4፥4 / ሮሜ 1፥3-4) ስለዚህም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ትባላለች።
በብሉይ ኪዳን ነቢያት “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” እያሉ የተናገሩት ትንቢት በኢየሱስ ክርስቶስ መፈፀሙ የኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔርነት የባህርይ አምላክነት የሚያረጋግጥ ነው። ኢዮ 2፥32 / የሐዋ 2፥21-38 / ሮሜ 10፥9-13 / ኢሳ 40፥3 / ማር 1፥1-3 እነዚህን ማመሳከሩ ብቻ በቂ ነው።
ይህንን ሁሉ ይዘን ድንግል ማርያም ለአምላክ እናትነት ብቻ የተፈጠረች የእግዚአብሔር እናት ናት እንላለን። በተጨማሪም የእስክንድሪያው ሊቀ ጳጳስ አባታችን ቅዱስ ቄርሎስ “አማኑኤል የባሕርይ አምላክ እንደሆነ ንጽሕት ድንግልም አምላክን የወለደች እንደሆነች ሰው የሆነ የእግዚአብሔርንም ቃል እንደወለደች የማያምን ሰው ቢኖር የተወገዘ ይሁን” በማለት ካወገዘ በኋላ "ዳግመኛ በኋላ ዘመን ቅድስት ድንግል እርሱን በሥጋ ወለደችው ስለ እኛ ሰው የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ወለደችው ስለዚህም ቅድስት ድንግልን ወላዲተ አምላክ እንላታለን።" በማለት (ሃ.አበው ገጽ 277-305) እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ መባል እንደሚገባት አስረግጦ ተናግሯል።
፪.፪, #ክብረ_ድንግል
፪.፪.፪, #ቅድስናዋ
እመቤታችን ከሁሉ ይልቅ ወላዲተ አምላክ በመሆኗ ከፍጥረታት ሁሉ የከበረች ናት። ይህ ከእግዚአብሔር የተሰጣት ስለሆነችም ቅድስተ ቅዱሳን ከተለዩ የተለየች ትባላለች።
አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ። (ዘሌ 19፥2)ብሎ እንደተናገረው በፈጣሪው አርአያና አምሳል ለተፈጠረው የሰው ልጅም በቅድስና የፈጣሪውን አርአያ መከተል ሃይማኖታዊ ግዴታው ነው።
ይህንን ግዴታ ለመፈጸም በቀና እምነትና በበጎ ምግባር ለብፅዕና ለቅድስና የበቁ የብሉይና የሐዲስ ምእመናን ቁጥር በፈጣሪ እንጂ በፍጡር አዕምሮ ተደምሮና ተባዝቶ የሚደረስበት አይደለም።
ሆኖም ከዚህ ዓለም ቅዱሳን እና ቅዱሳት መካከል እንደ እመቤታችን ያለ በእርስዋ መጠን ፀጋን የተመላ በንጽሕናና በቅድስና የተዋበ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነና በልዑል ኃይልም የተጠበቀ ሰውነት ያለው የለም። (ሉቃ 1፥28-36)
ይኸውም እመቤታችን ለአምላክ እናትነት የተመረጠች ድንግል በመሆኗ እና የአምላክ እናት እንደመሆኗ መጠን በሐልዮ በማሰብ፣ በነቢብ በመናገር፣ በገቢር በመከወን ንፅሐ ጠባይ ያላደፈባት ቅድስትና ቡርክት በመሆኗ ነው።
ስለዚህ ራስዋ ወላዲተ አምላክ አስቀድማ በወንጌል ቃል እንደተናገረችው ትውልድ ሁሉ “ቅድስት ወብፅዕት” እያሉ ሲያመሰገኗት ይኖራሉ። (ሉቃ 1፥48)...
፪.፪, #ክብረ_ድንግል
፪.፪.፪, #ቅድስናዋ
...በብሉይና በሐዲስ ኪዳን ማረጋገጥ እንደሚቻለው ለሕይወተ ዓለም እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነው ረድኤተ እግዚአብሔር በዘመነ ፍዳና በዘመነ ኩነኔ ከዓለም ሊርቅና ሊነሳ የቻለው በዓመፅና በክፋት ብዛት ነበር። የሰው ልጅ ያን ጊዜ በበረከተ ሥጋ እና በበረከተ ነፍስ እጦት ይሰቃይ የነበረውም በዚሁ ምክንያት ሲሆን ያጣውን ሁሉ አግኝቶ እንደገና ለመክበር የበቃውም ዳግም በፍፁም ተስፋ ይጠበቅ የነበረው የዓለም መሢሕ ከእመቤታችን ከተወለደ ወዲህ ነው።
ስለሆነም የሰው ልጅ ንጽሕ ጠባዩን በድቀተ ኃጢአት ምክንያት ከማደፉ በፊት የነበረው የተፈጥሮ ንጽሐ ሥጋ፣ ንጽሐ ነፍስ፣ ንጽሐ ልቦና ወይም የሐልዮ፣ የነቢብ እና የገቢር ንጽሕና የቱን ያህል እንደ ነበር ማረጋገጥ የተቻለውም በእመቤታችን ንጽሕና፣ ቅድስና ነው።
ይኸውም እመቤታችን ከፈጣሪዋ በተሰጣት ምሉዕ ፀጋ መሠረት በውስጥ በአፍአ የነበራት ንጽሕናና ቅድስና ሁሉ ፍፁም ስለሆነ ነው። እኛም አሁን ከእመቤታችን ረድኤትና በረከት እንዲከፈለን ወደ ልጅዋ የምንማፀነው በእርስዋ ከተሰጠው የንጽሕናና የቅድስና በረከት እንድናገኝ ነው።
አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኃጢአት (ጥንተ አብሶ) ያላገኛት መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት ገና ከመወለዷ አስቀድሞ በአምላክ ሕሊና ታስባ ትኖር የነበረች በሰው ልማድና ጠባይ ከሚደርሰው ሥጋዊ አሳብና ፍቃድ የተጠበቀች፣ ከተለዩት የተለየች፣ ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን ናት። (መኃ 4፥7)
“ምልዕተ ጸጋ፣ ምልዕተ ክብር ሆይ ደስ ይበልሽ” ተብላ በቅዱሳን መላእክት አንደበት በቅድስናዋ ተመስግናለች። (ሉቃ 1፥28)
እመቤታችን በውስጥ በአፍአ በነፍስ በሥጋ ቅድስት ስለሆነች እግዚአብሔር ለልጁ ማደሪያ መርጦታል። ማህደረ መለኮት እንድትሆን አድርጓታል። አምላክን ለመውለድ ያስመረጣትና ያበቃት ንጽሕናዋ ቅድስናዋ ነው።
አባ ሕርያቆስም በቅዳሴው “እግዚአብሔር አብ በሰማይ ሆኖ ምሥራቁን እና ምዕራቡን ሰሜኑን
እና ደቡቡን ዳርቻዎችን ሁሉ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አልተገኘም ያንቺን ንጽሕና
ወደደ፤ ደም ግባትሽን ወደደ፤ የሚወደውን ልጁን ወደ አንቺ ሰደደ።” ብሏል
የእመቤታችን ንጽሕና እና ቅድስና በመወደዱ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ በተዋህዶ ሰው መሆኑን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለአምላክ እናትነት መመረጧን የሚያሳይ ነው። ቅዱስ ዳዊትም በመዝ 131፥13 “እግዚአብሔር ፅዮንን መርጧታል ማደሪያው እንድትሆን አስጊጧታል።” ብሏል