+ ከሀዲውን ቃል ሳይናገር የመለሰው ቅዱስ +
በግብፅ ውሰጥ በበረሃ የሚኖር አንድ ቅዱስ ሰው ነበር፡፡ ከእርሱ ርቆ ደግሞ መነናዊ የሆነ (የማኒ እምነት ተከታይ) እነሱ ካህን የሚሉት አንድ ሰው ነበር፡፡
በአንድ ወቅት ይህ ሰው ከመሰሎቹ አንዱን ሊጠይቅ ሲሔድ ኦርቶዶክሳዊው ቅዱስ ከሚኖርበት ቦታ ላይ ሲደርስ መሸበት፡፡ ሆኖም መነናዊ መሆኑ እንደሚታወቅ ስላወቀ ወደዚህ ኦርቶዶክሳዊ አባት ብሔድ አይቀበለኝም በማለት በጣም ተጨነቀ፡፡ ሆኖም ምንም አማራጭ ስላልነበረው ሔደና አንኳኳ፡፡ አረጋዊውም አባት በሩን ከፈተለት፡፡ እርሱም ማንነቱን አወቀው፡፡ ደስ ብሎት በፍቅር ተቀበለው፡፡ ምግብ ከሰጠው በኋላ አስተኛው፡፡
መነናዊውም ሰው ሌሊት ይህን ሁኔታ ሲያሰላስል አደረና ስለ እኔ ምንም ያልጠረጠረው እንዴት ዓይነት ሰው ቢሆን ነው? በእውነት ይህ ሰው የእግዚአብሔር ሰው ነው አለ፡፡ ሲነጋም ከእግሩ ላይ ወድቆ ከአሁን በኋላ እኔ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ አለው፡፡ ከእርሱም ጋር ኖረ።
ዜና አበው
-------------
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

"ሕይወታችን ለሌሎች የሚያበራ ቢሆን ኖሮ ስብከት ባላስፈለገ ነበር:: በምግባራችን መመስከር የምንችል ብንሆን ኖሮ ቃላት ባላስፈለጉ ነበር:: እውነተኛ ክርስቲያኖች ብንሆን ኖሮ አረማውያን ባልበዙ ነበር"
- ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯