“በኅልውና አንድ በኾነ በማይለወጥና በማይጨመርበት፣ በአንድነት በሚሰገድለት በአንድነትም በሚመሰገን የነፋስን ኃይል እየነፈሰ የፀሐይም ነበልባል እየተርገበገበ የፀሐይን ክበብ በነፋሳት ሠረገላ በሚከምር፣ በሰማይ መስኮቶችም በሚያወጣው ለጨረቃም ዐውደ ቀመር ፈጽሞ እስኪመላ ድረስ በብርሃን ቀን በየጠዋቱ ብርሃንን በሚስልበት፣ የመብረቆች ብልጭታ ሲያበራ የነጐድጓድም ድምጽ ሲጮህ የዝናብ ጠብታዎችን ከደመናዎች ማኅፀን በሚቀዳ በሥሉስ ቅዱስ ስም ለፍጥረታት ሁሉ ገዥ ለእርሱ ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።”
(ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)
(ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)