"የአእላፋት ዝማሬ"ን የተወሰነውን ተመልክቻለኹ፤ ለኦርቶዶክስ "ቀላል ያልኾነ" መነቃቃት ሊያመጣ እንደሚችል አምናለኹ፤ ምክንያቱም ጌታ ኢየሱስን የመጠማትን ብርታት፤ መንፈስ ቅዱስን የመፈለግ ሐሰሳ አለበትና። ቅዱስ ጳውሎስ ለአይሁድ ዘመዶቹ እንዳለው፣ እኔም ለኦርቶዶክስ ዘመዶቼ እንዲህ እላለኹ፤
"ወንድሞች ሆይ፥ የልቤ በጎ ፈቃድና ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ልመናዬ እንዲድኑ ነው። በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ እመሰክርላቸዋለሁና። የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም። የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።" (ሮሜ 10፥1-4) እንዳለው፣ በክርስቶስ የተገለጠው እግዚአብሔር ኹለንተናቸውን እንዲወርስ እመኛለኹ።
ደግሞም፣ አንድ ቀን "የአእላፋት ዝማሬ" ለታረደው፤ ክብርን ኹሉ ከፍጥረታት ጠቅልሎ ለወረሰውና ለሥላሴ ፍጥረትን ለማረከው ለመሲሑ ክርስቶስ ብቻ ዝማሬያቸው እንደሚኾን ተስፋ አደርጋለኹ። ከተዘመሩት "ዝማሬዎች" እኒህ ሐረጋት ደምቀው በልቤ አሉ።
"ጌታ ሆይ በስምህ ግዞቱ አበቃ ...!
የጠፋ በግ አዳም ታደሰ በጌታ ...!
ሥጋዋን አንጽቶ በማርያም አደረ ...!" የሚሉት።
ተሐድሶ በቅዱስ ቃሉ ለወደቀው ፍጥረት ዘወትር እንዲኾን እንማልዳለን።
የቴሌግራም አድራሻ - https://t.me/ebenezertek