ወደ አዲስ ኪዳናዊ የመመለስ ተሐድሶ ያስፈልገናል!
ከዚህ ቀደም የጻፍኹትን ልጥቀስ፣
“ተሐድሶ፣ “ሐደሰ” ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን፣ ትርጕሙ “አዲስ አደረገ” የሚለውን ትርጕም ታሳቢ ያደርጋል። በተገብሮ (Passive) “ተሐድሰ” ከሚለው ቃል ደግሞ፣ “ተሐድሶ” የወጣ ሲኾን፣ ትርጕሙ “አዲስ ኾነ” ማለት ነው። ስለዚህም ስያሜው ድርጊትን እንጂ ተቋማዊነትን ወይም አደረጃጀትን ፈጽሞ አያመለክትም።” [1]
ወደ ርዕሳችን ስንመለስ፣ ወደ አዲስ ኪዳናዊ የመመለስ ተሐድሶ ማለት፣ በጌታችንና በቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ተሰጡት ትምህርቶች፣ ወደ ተኖሩ ልምምዶችና ትውፊቶች በመመለስና ብሎም አሠረ ፍኖታቸውን በመከተል እውነተኛ የሕይወትና የኑሮ ተሐድሶ ማምጣት የሚል ፅንሰ ዐሳብ በውስጡ የያዘ ነው። ይህ የሚኾንበት ዋነኛ ምክንያቱ፣ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ዘመናት፤ በተለያዩ ታሪኮችና በተለያዩ ኹኔታዎች ውስጥ በማለፍዋ ምክንያት፣ ለተለያዩ እንግዳ ትምህርቶችና ልምምዶች ልትጋለጥ ትችላለች ወይም ተጋልጣ ታይታለች።
በአዲስ ኪዳን ምንባባት ውስጥ ጌታችን ኢየሱስ፣
“ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ” (ማቴ. 16፥6)፣ “ምን ወይም እንዴት እንድትሰሙ ተጠበቁ።” (ማር. 4፥24፤ ሉቃ. 8፥18)
እንዲሁም ቅዱስ ጳውሎስ፣
“በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።” (ሐ.ሥ. 20፥28-30)
ብለው ሲናገሩ፣ ቤተ ክርስቲያን ባለመጠንቀቅዋ ምክንያት ለተለያዩ እንግዳና ልዩ ልዩ ትምህርቶች ልትጋለጥ እንደምትችል አመልካች ናቸው።
ለዚህም ነው ለተለያዩ እንግዳና ልዩ ልዩ ትምህርቶች ከተጋለጡት አብያተ ክርስቲያናት መካከል ገላትያን እንዲህ በማለት ቅዱስ ጳውሎስ የሚናገረው፤
“በክርስቶስ ጸጋ የጠራችሁን እርሱን ትታችሁ፣ ወደ ተለየ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ መዞራችሁ ደንቆኛል፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ሌላ ወንጌል የለም። የሚያደነጋግሯችሁና የክርስቶስን ወንጌል ለማጣመም ጥረት የሚያደርጉ አንዳንድ ሰዎች አሉ።” (ገላ. 1፥6-7 ዐመት)።
በዚህ ክፍል ላይ የገላትያ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ባለ ውድቀት ውስጥ መግባትዋን እናስተውላለን። ብዙዎች እንዲህ ስንናገር፣ “ቤተ ክርስቲያን አትሳሳትም፤ ሰዎች እንጂ” የሚል አቋም ያንጸባርቃሉ። ይህን በሌላ ርዕስ እመለስበታለሁ።
ወደ አዲስ ኪዳናዊ የመመለስ ተሐድሶ፣ እውነት ኾኖ በብዙዎች ልብ ያለ ቢኾንም፣ ነገር ግን ለመቀበልና ለመተግበር ብዙዎች ፈቃደኞች የኾኑ አይመስሉም። እንዲያውም፣ ተሐድሶ ሲባል በብዙዎች ልብ ያለው፣ “ኦርቶዶክስን ወደ ወንጌላውያን የመውሰድ ወይም ፕሮቴስታንት የማድረግ ዝንባሌ” እንደ ኾነ ተደርጐ ሲወሰድ ይስተዋላል፤ በርግጥ ይህ ስህተት አልተፈጸመም ማለት አይቻልም። ነገር ግን እውነተኛውና ወደ አዲስ ኪዳናዊ ወይም ወደ ቅዱሳት መጻሕፍት የመመለስ ተሐድሶ፣ ተቋም የመለወጥ አልያም ስፍራ የማቀያየር ተግባር ነው ማለት አንደፍርም።
የዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን፣ ባለፉት ኹለት ሺህ አመታት አልፋ በመጣችባቸው ልዩ ልዩ ጎዳናዎች፣ ወድቃም፤ ተሳስታም አሳስታም ኖራ፣ ነገር ግን በጌታ ምሕረትና ጥበቃ፤ በትድግናውና በሉዓላዊ መግቦቱ ግን እስከ አኹን አለች። ስለዚህ ባለፉት ዘመናት በውስጧ የገቡና የሰረጉ፤ በዘመን ርዝመት እውነት የመሰሉ አያሌ ስህተቶችና እንከኖችን አስወግዳ፣ ስትመሠረት በነበረችውና ለመሲሑ ቃልና ሕይወት፤ ትምህርትና ልምምድ በመገዛት በቄሣርና በአላውያን ነገሥታት ፊት ተፈርታና ታፍራ እንደ ነበረችው ቤተ ክርስቲያን ትኾን ዘንድ መመለስ ያስፈልጋታል ብለን እናምናለን። ስለዚህም ደፍረን በዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የክርስቶስ የኾነው ኹሉ ይንጸባረቅ ዘንድ እንመለስ እንላለን!
በአጭር ቃል፣ የክርስቶስ ሕይወት ሕይወታችን፤ ኑሮው ኑሮአችን፤ ትምህርቱ ትምህርታችን፤ ልምምዱ ልምምዳችን፤ ሥራው ሥራችን ኾኖልን፤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚሉን በመመለስና ርሱን በመከተል ሕይወት በመኖር የመንፈሳዊ እውነተኛ የሕይወት ተሐድሶ እናመጣ ዘንድ ወደ አዲስ ኪዳናዊ የመመለስ ተሐድሶን በእውነት እንድርግ እንላለን!
[1] http://abenezerteklu.blogspot.com/2021/09/blog-post_29.html
My blog link - http://abenezerteklu.blogspot.com/2025/01/blog-post_31.html