EBS - NEWS


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


Official EBS news channel

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: ታማኝ ዜና
የሁለቱ ወንድማማቾች አውሮፕላን !

በኦሮሚያ ምስራቅ ወለጋ ከነቀምቴ ቅርብ ርቀት በምትገኘው የሲቡ ሲሬ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወንድማማቾች ለሊሳ ዳንኤል እና ቢቂላ ዳንኤል ከሰሞኑ የሰሯትን 'አውሮፕላን' ለማብረር ጥረት ማድረጋቸው የበርካቶች መነጋገሪያ ሆነዋል።

ወጣቶቹ "ኦሮሚያ" ሲሉ የሰየሟትን 'አውሮፕላናቸውን' ለማብረር ሙከራ ማድረጋቸው የአከባቢ ሰዎች በታሪክ መዝገብ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለ ሞተር አውሮፕላን ካበረሩት አሜሪካውያን ወንድማማቾች ኦርቪል እና ዊልበር ራይት ጋር አነጻጽረዋቸዋል።

ወንድማማቾቹ የሰሯትን 'አውሮፕላን' ለማብረር ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።

@tamagnzena @tamagnzena


የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳቹ ቴክኒክና ሙያ መማር ለምትፈልጉ የመግቢያ ነጥብ በምስሉ ላይ ተያይዟል::

ከሰኞ ግንቦት 09,2013 ጀምሮ በሬጅስትራር ጽ/ቤት አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃ ይዞ በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

@ebs_official @ebs_official


#Advertisement

ስለሶፍትዌር ለመማር እና የሶፍትዌር እውቀት ለማሳደግ ለምትፈልጉ ብቻ 👇👇
https://t.me/joinchat/am-9NdPcMeo1ZmU0


በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ አዳማ ከተማ ሀዋሳ ከተማን 2 ለ 1 አሸነፈ፡፡

የአዳማ ከተማን ሁለት ግቦች አብዲሳ ጀማል በመጀመሪያው አጋማሽ ሲያስቆጥር የሀዋሳ ከተማን ብቸኛ ግብ መስፍን ታፈሰ በ36ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

አዳማ ከተማ ከፕሪምየር ሊጉ መውረዱ የሚታወስ ነው፡፡

ረፋድ ላይ በተካሄደው ጨዋታ ባህርዳር ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና 2 ለ 2 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

@ebs_official @ebs_official


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1442 ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሰን ፣ አደረሳችሁ።

@ebs_official @ebs_official


መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ እና 3ኛ ዓመት የመደበኛ መርሃ ግብር ተማሪዎቹ ከመጪው ምርጫ አንድ ሳምንት በፊት ዩኒቨርሲቲውን በመልቀቅ ወደቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ አሳስቧል።

የመማር ማስተማር ሂደቱ ግንቦት 10/2013 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ሲሆን የማጠቃለያ ፈተና ከግንቦት 11/2013 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል።

ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚመለሱበት ቀን ወደፊት ከምርጫ በኋላ በመገናኛ ብዙሃን ይገለፃል ብሏል።

ውሳኔው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጋር ያደረገውን ስብሰባ መሰረት በማድረግ የተደረሰ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@ebs_official @ebs_official


እስራኤል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች፡፡

በእስራኤል ሃይሎችና በዓረብ እስራዔላዊያን መካከል ግጭቱ እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ ነው አዋጁ መታወጁን ቢቢቢ ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መረጃ ገልጿል፡፡ሰሞኑን የፍሊስጤም ሃይሎች በእስራኤል ማእከላዊ ከተማዎች ላይ በሮኬት የታገዙ ጥቃቶችን ሲያደርሱ መሰንበታቸውን መረጃው አስታውቋል፡፡

እስራኤልም በአጸፋው በፍሊስጤም የጋዛ ሰርጥ ላይ በወሰደችው የአየር ላይ ጥቃት ህንጻወችን ከማውደሟም ባለፈ፤ በርካታ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን የቢቢሲ መረጃ አስታውሷል፡፡የእስራኤል ጥቃት ያነጣጠረው በፍሊስጤም ጋዛ ውስጥ የሚገኙ ተፋላሚ ሃይሎች ላይ ሲሆን የፍሊስጤም ሃይሎች ደግሞ የእስራኤልን ከተማ ቴላአቪቭ መሆኑን መረጃው አመላክቷል፡፡

ካሳለፍነው ሰኞ ጀምሮ በፍሊስጤም ታጣቂ ሃይሎች ወደ እስራኤል ማእከላዊ ከተማዎች ከ1 ሺህ የሚበልጡ ሮኬቶች መተኮሳቸውን እንዲሁም እስራኤል ደግሞ 200 ሚሳኤሎችን መተኮሷ ተነግሯል፡፡

በፍሊስጤም የጋዛ ሃይሎችና በሀገሪቷ ሃይሎች መካከል ያለው ግጭት እየተባባሰ በመምጣቱ፤ በዚህም የንጹኃን ዜጎች ሞት እየጨመረ በመሆኑ እስራኤል ሎድ በተባለችዋ ከተማና ሌሎች ግጭቱ በተቀሰቀሰባቸዉ አካባቢዎች ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጇን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

@ebs_official @ebs_official


አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የሚስዮኑ ኃላፊ ጋር ተወያዩ
************************

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የሚስዮን ኃላፊ የሆኑትን ፊሊፕ ቦቨርዲን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

አቶ ደመቀ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ድርጅት በኢትዮጵያ በሚፈጠሩ ሰው ሰራሽ ግጭቶች እንዲሁም እንደ ድርቅና ወረርሽን የመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎች በሚያጋጥሙበት ወቅት ግንባር ቀደም በመሆን እያበረከተ ስላለው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

የሚስዮኑ ኃላፊ፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ሌሎች ተያያዥ መስሪያ ቤቶች ድርጅታቸው ኃላፊነቱን ለመወጣት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ወቅት ላደረጉላቸው ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የስራ ኃላፊው ቀይ መስቀል እስካሁን በትግራይ ክልል ባከናወናቸው ተግባራት ደስተኛ መሆናቸው ጠቅሰው፤ ያጋጠሟቸውን ችግሮችንም አንስተዋል።

አቶ ደመቀ በትግራይ ክልል የሰብአዊ ዕርዳታ ተደራሽ እንዲሆን መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር ለ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ መደረጉንም ጠቅሰዋል።

የፀጥታ ስጋት ባሉባቸው ውስን ቦታዎች ጭምር መከላከያ ከሲቪል ጋር በመቀናጀት ድጋፍ እየተሰጠ ነው ሲሉ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

(FBC)
@ebs_official @ebs_official


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የመድረክ ቴአትሮችን ለተመልካች ማቅረብ ሊጀምር ነው!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የኮቪድ-19 መከላከል መመሪያን ተግባራዊ ባደረገ መልኩ በሚቀጥለው ሳምንት የመድረክ ቴአትሮችን ለተመልካች ማቅረብ ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል።

ቴአትር ቤቱ በአንድ ጊዜ 1 ሺህ 200 ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ቢኖረውም አሁን ላይ በአንድ ጊዜ 300 ተመልካቾች ብቻ ይስተናገዳሉ ሲሉ የቴአትር ቤቱ የቴአትር ክፍል ዳይሬክተር ደስታ አስረስ ገልጸዋል።

“ተመልካቾች ወደ ቴአትር ቤት ሲመጡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በማድረግ፣ ሳኒታይዘር በመጠቀም እና ተራርቆ በመቀመጥ እንዲመለከቱ ይገደዳሉ” ብለዋል።

ከታህሣሥ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ቴአትር ቤቱ ለተመልካች ክፍት ሆኖ በሳምንት ሶስት ቴአትሮችን ለማሳየት ዝግጅት መደረጉንም ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል። (ENA)
@ebs_official @ebs_official


የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ከመጭው ሀገራዊ ምርጫ በፊት አባሎቹ እንዲፈቱ ጠየቀ!

ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በሀገሪቱ ዶሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ የበኩሉን ሲያበረክትና በተለያዩ ምርጫዎች ሲሳተፍ መቆየቱን አመለክቷል።ኦፌኮ ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫን ለማካሄድ በምርጫ ቦርድ በኩል እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ገልጾ፤ በመጭው ዓመት 2013 በሚካሄደው ምርጫም ለመሳተፍ እንደሚፈልግ አመልክቷል።ይሁን እንጅ ምርጫው በታቀደለት ጊዜ ተዓማኒነት ባለውና በዲሞክራሲያዊ መንገድ እንዲካሄድ ከተፈለገ፤መንግስት ከምርጫው በፊት የታሰሩ አመራሮች እንዲፈቱ፣በመንግስት ሀይሎች የተዘጉ ፅ/ቤቶች እንዲከፈቱና በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት እንዲከበርና የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ ጠይቋል።

[DW]
@ebs_official @ebs_official


#Tigray

እስከ መጪው እሁድ ድረስ የኤሌክትሪክ ኃይል የተቋረጠባቸው የትግራይ ክልል አካባቢዎች መብራት እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ አሳውቋል።

መቐለን ጨምሮ ሌሎች ማከፋፊያ ጣቢያዎች እና ማስተላለፊያ መስመሮችም ጥገና እየተከናወነላቸው መሆኑን ተገልጿል።
@ebs_official @ebs_official


የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከታህሳስ 1 ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለፀ!

በድሬደዋ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከታህሳስ 1 እስከ 3 መሰጠት እንደሚጀመር የድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ገልጸዋል።

በዚህም 7113 ተማሪዎች የ45 ቀን የክለሳ ትምህርት ተሰቷቸው በ 90 ትምህርት ቤቶች 289 የመፈተኛ ክፍሎች ውስጥ በአንድ ክፍል 40 ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ኃላፊዋ ገልፀዋል፡፡

ፈተናው የ7ኛ ክፍል ሙሉ ይዘት እና የ8ኛ ክፍል የግማሽ አመቱን ይዘት እንደሚያጠቃል የተገለጸ ሲሆን ተማሪዎች በፈተናው ምንም አይነት መረበሽ እንደሌለባቸውም በመጠቆም ወላጆች ልጆቻቸውን ለፈተናው በበቂ ሁኔታ ዝግጁ እንዲሆኑ የስነ-ልቦና ምክር እንዲመክሩም ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

(የድሬደዋ አስተዳደር ኮሚውኒኬሽን ቢሮ)
@ebs_official @ebs_official


የኤርትራ ወታደሮች በትግራዩ ግጭት ተሳትፈዋል ብላ አሜሪካ እንደምታስብ ሮይተርስ ከአንድ የአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣን እና ከ5 የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ዲፕሎማቶች ሰምቻለሁ በማለት ዘግቧል።ኤርትራ ጦሯን ስለማስገባቷ የአሜሪካ መንግሥት ግንዛቤ ያገኘው፣ ከሳተላይት ምስሎች፣ ከተጠለፉ የመልዕክት ልውውጦች እና ከትግራይ ክልል ከሚወጡ ሪፖርቶች እንደሆነ ዘገባው ገልጧል።የአሜሪካ መንግሥት እዚህ ድምዳሜ ላይ ስለመድረሱ ግን፣ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ማረጋገጫ አለመስጠቱን ዘገባው አመልክቷል።የኤርትራ ወታደሮች በዛላንበሳ፣ ራማ እና ባድመ ከተሞች በኩል እንደገቡ ከምንጮች መስማቱን የገለጠው ዜና ወኪሉ፣ የወታደሮቹ ብዛት እና በጦርነቱ ስላላቸው ሚና ግን መረጃ እንዳልተገኘ አክሏል።ብሉምበርግም ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ፣ የኤርትራ ወታደሮች መቀሌ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች መታየታቸውን ዘግቧል።

[Reuters/Wazema]
@ebs_official @ebs_official


Репост из: ታማኝ ዜና
በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሀይደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚገኙ ተማሪዎች በጥሩ ደህንነት ላይ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡

ተማሪዎቹ በአሁን ሰዓት የትምህርት አገልግሎት ቢቋረጥም በሰላማዊ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል።በሀይደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአሁን ሰዓት የህክምናና ተመራቂ የጤና ሳይንስ ተማረዎች ይገኛሉ፡፡

ከዚህ ባሻገር በተለያዩ የትምርህት ዘርፍ ስፔሻላይዝድ ለማድረግ የገቡ የህክምና ተማሪዎች የሚገኙ ሲሆን÷ በአሁን ሰዓት ሁሉም በሆስፒታሉ ቅጥር ጊቢ እንዳሉ ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ከጊቢው ውጪ ይኖሩ የነበሩ የስፔሻሊቲና ሰብ ስፔሻሊቲ ተማሪዎች ወደ ጊቢ ገብተው የመኝታ ክፍል አግኝተው በጥሩ ደህንነት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡በዩኒቨርሲቲው በቂ የውሃና የመብራት አቅርቦት እንደሌለም ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

(FBC)
@tamagn_zena @tamagn_zena


#Grade8

ትምህርት ሚኒስቴር የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እስከ ታህሳስ 30 ተሰጥቶ ይጠናቀቃል አለ!

የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው የግዜ ሰሌዳ መሰረት የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በሁሉም ክልሎች እስከ ታህሳስ 30 ተሰጥቶ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።ይህንንም ተከትሎ የክልል ትምህርት ቢሮዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየትና አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ፈተናውን በተያዘለት የግዜ ገደብ ለመስጠት የራሳቸውን የግዜ ሰሌዳ እያወጡ ይገኛሉ።

በዚህም መሰረት የሀረሪ ክልል ከ ታህሳስ 7-9፣ የአማራ ክልል ከታህሳስ 12-14 ፈተናውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

ሌሎች ክልሎችም በቀጣይ ቀናት ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ይፋ የሚያደርጉ ይሆናል።በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከትላንት ጀምሮ መሰጠት መጀመሩ ይታወሳል።

(MoE)
@ebs_official
@ebs_official


ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ የሚገነባው የአትክልት ተራ የገበያ ማዕከል በ 2 ሳምንታት ይጠናቀቃል ተባለ!

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ እየተገነባ ያለው የአትክልት ተራ የገበያ ማዕከል የግንባታ ሥራ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ፡፡የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ወደ አንድ ቢሊዮን ብር በሚጠጋ የኮንትራት ዋጋ እየገነባ የሚገኘውን ተለዋጭ የአትክልት ተራ የገበያ ማዕከል በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚያጠናቅቅ አስታውቋል፡፡

የገበያ ማዕከሉን በሁለት ምዕራፍ ከፋፍሎ እየገነባ የሚገኝ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ 14 የገበያ ሼዶች፣ በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ የፓርኪንግና የአረንጓዴ ቦታዎች፣ መጋዘኖች፣ የአስተዳደር ህንጻዎች እና ሌሎች የግንባታ ስራዎች ይከናወናሉ።የገበያ ማዕከሉ 80 ሺ ካሬ ሜትር ቦታ ሲሸፍን፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ የሚገነቡት 14 ሼዶች ውስጥ 588 የመገበያያ ሱቆች እንዳሏቸው የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመለክታል፡፡
@ebs_official
@ebs_official


የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ መሰጠት ተጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ዛሬ እና ነገ ይሰጣል።
በወጣው መርሐ ግብር መሠረት የዛሬው ፈተና ተማሪዎች በየተመደቡባቸው ትምህርት ቤቶች መሰጠት ተጀምሯል።
(አስማረ ብርሃኑ)
@ebs_official
@ebs_official


#HPR

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው!

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነው እያካሄደ የሚገኘው፡፡በስብሰባው የምክር ቤቱን 6ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ  እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡ከዚህ ባለፈም በተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚመክርም ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@ebs_official
@ebs_official


Репост из: ታማኝ ዜና
በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት ከነገ ኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያበቃል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም በህዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ከነገ ጀምሮ በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት አይቻልም።

የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታኅሣሥ 6 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወቅቱ መግለጹ ይታወሳል።

ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አሮጌ የብር ኖቶች በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየሩ መሆኑ ይታወቃል።

@tamagn_zena @tamagn_zena


#ሀሰተኛ_መረጃ

"ሱዳን ፖስት" የተባለ ድረ-ገጽ ደቡብ ሱዳን በሀገሯ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለማባረሯ እና ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ በሚገኙ የደቡብ ሱዳን ዲፕሎማቶች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ስለመውሰዷ በትናንትናው እለት አስነብቧል።

ሱዳን ፖስት ያሰራጨው መረጃ "ውሸት" መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኢትዮጵያ ቼክ ዛሬ ጠዋት አረጋግጠዋል።

የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ ተመሳሳይ ማረጋገጫ የሰጠ ሲሆን "ይህ ፍፁም ውሸት ነው፣ እንዲህ አይነት ነገር አልነበረም፣ ሆን ተብሎ ሀገራቱን ለማጋጨት የሚደረግ ሴራ ነው" ብሏል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ቼክ

Показано 20 последних публикаций.

5 070

подписчиков
Статистика канала