⚽️የእንግሊዝ ኤፍ ኤካፕ ሶስተኛ ዙር ጨዋታ ዛሬ ምሽት በኤሜሬትስ ስቴዲየም ሲቀጥል የውድድሩ ባለታሪኮች አርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
⚽️በታሪክ 16ኛ ጊዜ በውድድሩ የሚገናኙት ክለቦቹ ከኤቨርተን እና ሊቨርፑል የ19 ጊዜ የእርስ በእርስ ጨዋታ መልስ ለበርካታ ጊዜ በመድረኩ የተገናኙ ቡድኖች ሆነዋል፡፡
⚽️አርሰናል ካለፉት ሶስት የውድድር አመታት ከኤፍ ኤካፕ 3ኛ ዙር ውድድሮች በሁለቱ ከውድድር ውጭ የሆነ ሲሆን በ2019/2020 ግን ቼልሲን በመርታት ውድድሩን ማሸነፍ ችሏል፡፡
⚽️ማንችስተር ዩናይትድ አርሰናልን በኤፍ ኤካፕ በቅርብ ጊዚያት በገጠመባቸው ካለፉት ሶስት ጨዋታዎች ሶስቱን ያሸነፈ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ በተገናኙበት የ2018/2019 ጨዋታም 3-1 መርታቱ ይታወሳል፡፡
⚽️ማንችስተር ዩናይትድ አርሰናልን ስምንት ጊዜ ከኤፍ ኤካፕ ውድድር ውጭ ያደረገ ሲሆን አርሰናል በበኩሉ ማንችስተር ዩናይትድን ለ7 ያህል ጊዜ ከመድረኩ ሸኝቷል፡፡
⚽️ሁለቱ ክለቦች በውድድሩ ታሪክ ለበርካታ ጊዜ ዋንጫውን ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን አርሰናል 14 ጊዜ የመድረኩን አሸናፊነት ክብርን ሲያገኝ ማንችስተር ዩናይትድ ደግሞ 13 ጊዚ ውድድሩን ማሸነፍ ችሏል፡፡
⚽️ሁለቱ ክለቦች ከዚህ ቀደም በኤፍ ኤካፕ ካደረጓቸው ጨዋታዎች መሀል በ1999 የተከናወነው እና በማንችስተር ዩናይትድ አሸናፊነት የተጠናቀቀው ጨዋታ ተጠቃሽ ሲሆን በ2005 በመድረኩ ፍጻሜ የተገናኙበት ጨዋታም የሚታወስ ነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews