EBSTV NEWS


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.
https://t.me/ebstvworldwide
Inbox - @EbswhatsnewBot

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


👉 በሀገራችን የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችን ለማስቆም የኃይማኖት ተቋማት የሚገባቸዉን ሚና እንዳልተወጡ ዑስታዝ አቡበከር ገልፀዋል።

👉 የኃይማኖት ተቋማቶች አማኞቻቸው በትክክል ከዕምነቱ ጋር መቆራኘት ስለመቻላቸው ሊፈትሹ እንደሚገባ የገለፁት የእስልምና ዕምነት አስተምሮት መምህር ዑስታዝ አቡበክር አህመድ አሁን ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችን ለማስቆም የኃይማኖት ተቋማት ቀዳሚዉን ድርሻ መውሰድ አለባቸው ነው ያሉት።

👉 አማኙ እና ዕምነቱ ተለያይተዋል ያሉት መምህሩ ሰው ለዕምነቱ አባል ነው እንጂ ዕምነቱን የተላበሰ እንዳልሆነ አስረድተዋል።

👉 ቤተ ዕምነቶች ነፃ የሥነ-ምግባር ትምህርት በመስጠት ማህበረሰቡን በመለወጥ እና በማስተማር ትክክለኛ የዕምነቱ አካል እንዲሆኑ ለማድረግ የተሰራው ሥራ ዝቅተኛ ነው ብዬ አምናለሁ ያሉት የኃይማኖት ምሁሩ ተቋማቱ በደፈናው የቡድን ተከታይ ከማፍራት ያለፈ ሥራ በመሥራት አማኞች በትክክል ዕምነቱ ዉስጥ ስለምኖራቸው መፈተሽ እንደሚገባቸው መክረዋል።

🔸የዚህን ዜና ዝርዝር በምሽት የዜና ሰዓት እወጃችን ይዘን የምንቀርብ ይሆናል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


የህዳር 24/2017 አበይት የዓለም ዜናዎች

🇮🇱🇱🇧 በእስራኤል በተፈፀመ የአየር ጥቃት 9 ሰዎች መገደላቸውን ሊባኖስ አስታወቀች።

🇺🇸🇦🇴 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሥልጣን ዘመናቸው የመጀመሪያ በሆነው የአፍሪካ ጉብኝታቸው በአንጎላ ጉብኝት እያደረጉ ነው።

🇺🇦 ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት "ኔቶ" ሙሉ አባል ስሆን ብቻ ነው ደህንነቴ የተረጋገጠ የሚሆነው ስትል አስታወቀች።

🇺🇸🇵🇸🇮🇱 ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የፍልስጤሙ ሃማስ አግቶ የያዛቸውን የእስራኤል ዜጐች በአስቸኳይ ካልለቀቀ ዋጋ ይከፍላል ሲሉ አስጠነቀቁ።

🇵🇸 የፍልስጤሙ ፋታህ የፖለቲካ ፓርቲ እና ሃማስ ከጦርነት በኃላ ጋዛን በጋራ ለማስተዳደር መስማማታቸው ተነገረ።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


💠 የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ወጣት ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ላይ እንደማይሳተፈ ተረጋግጧል።

💠 በዑጋንዳ አስተናጋጅነት ከ12 ቀናት በኃላ በሚካሄደው የታዳጊዎች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ኢትዮጵያ ተካፋይ እንደምትሆን ሲገለፅ ቢቆይም በመጨረሻ ሀገሪቱ ራሷን ከውድድሩ ማግለሏን ሴካፋ አሳውቋል።

💠 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በገጠመው የገንዘብ ችግር ምክንያት ኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ የማትሳተፍ ይሆናል።

💠 ባሳለፍነው ሐሙስ በወጣው የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ኢትዮጵያ ከዑጋንዳ፣ ታንዛንያ እና ብሩንዲ ጋር ብትደለደለም ባሳለፍነው ሰኞ በመድረኩ እንደማትታደም ለካፍ ማስታወቋ ተነግሯል።

💠 የዘንድሮ የታዳጊዎች የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ከታህሳስ 5 እስከ ታህሳስ 20 የሚከናወን ሲሆን በውድድሩ አንደኛ እና ሁለተኛ የሚወጡ ሀገራት በ2025ቱ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉ ይሆናል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


❕የአዲስ አበባ ፖሊስ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አካባቢ ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ሰዎችን ወደ ውጭ ሀገር እልካለሁ በሚል የማጭበርበር ወንጀል ሲፈፅም የነበረን በህረዲን ጀማል የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡

❕ተጠርጣሪ ግለሰቡ ወደ ውጭ ሀገር የመላክ ምንም ዓይነት ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖረው የግል ተበዳይን “ሁሉንም ነገር እኔ አስጨርሼ ወደ ዱባይ እልክሃለሁ” በማለት ከ297 ሺህ ብር በላይ በመቀበል ከተጠርጣሪው የጉዞ ሰነድ የተሰጠው የግል ተበዳይ ወደ ዱባይ ለመሄድ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተገኘበት ወቅት ሰነዱ ሀሰተኛ መሆኑ እንደተገለፀለትና ከአየር መንገዱ እንደተመለሰ ፖሊስ መምሪያው አስታውቋል።

❕የግል ተበዳይን አቤቱታ የተቀበለው የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልፆ በተጠርጣሪው ተመሳሳይ የማታለል ወንጀል ተፈፅሞብናል የሚሉ ግለሰቦች ወደ ክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ቀርበው ተጨማሪ መረጃ መስጠት እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመለክታል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


🔸በትግራይ ክልል በ2016 ብቻ 783 ሴቶች ላይ በተፈፀመ ፆታዊ ጥቃት 44 ሴቶች መገደላቸውን የክልሉ ሴቶች ማህበር አስታውቋል።

🔸በክልሉ ሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች ተባብሰው መቀጠላቸውን የገለፀው ማህበሩ በግፍ ከተገደሉ 44 ሴቶች መካከል ደግሞ 24ቱ በባሎቻቸው የተገደሉ ናቸው ብሏል።

🔸የትግራይ ሴቶች ማህበር ሥራ አስከያጅ ወ/ሮ አበባ ኃይለሥላሴ በግፍ ከተገደሉ 44 ሴቶች መካከል ፍትህ ያገኙት ስድስቱ ብቻ መሆናቸውን ለኢቢኤስ አዲስ ነገር የገለፁ ሲሆን በክልሉ ከፍተኛ የሆነ የህግ ማስከበር ዘመቻ ያስፈልጋል ብለዋል።

🔸በትግራይ ክልል በሴቶች መብት ዙርያ የሚሰሩ ተቋማት እና የተጎጂ ቤተሰቦች በክልሉ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች በተለየ ፍርድ ቤት እንዲታዩ ጥሪ ማቅረባቸው ሲታወቅ በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት በሴቶች ላይ ከደረሰው ፆታዊ ጥቃት ባሻገር አሁንም በክልሉ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ አስገድዶ መደፈር፤ እገታና ድብደባ መቀጠሉ ተነግሯል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


🔸የሦስተኛ ዙር የእንግሊዝ ኤፌኤካፕ ተጋጣሚዎች ተለይተው የታወቁ ሲሆን አርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድን የሚያደርጉት ፍልሚያ እጅግ ተጠባባቂ ሆኗል። 

🔸በግዙፉ ኦልትራፎርድ ስቴዲየም ሰኞ ምሽት ይፋ በሆነው ድልድልም ታላላቆቹ የሊጉ ክለቦች ወደ አራተኛው ዙር ለመሻገር የሚገጥሟቸውን ቡድኖች ለይተዉ አዉቀዎል።

🔸በዚህም የአምናው የውድድሩ አሸናፊ ማንችስተር ዩናይትድ አርሰናልን በኤሜሬትስ ሲገጥም የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከአግሪንግተን ስታንሌይ በአንፊልድ የሚፋለሙ ይሆናል።

🔸የውጤት ማጣት ቀውስ ላይ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ ደግሞ ሳልፎርድ ሲቲን እንዲሁም በተሻለ የድል ጉዞ ላይ ያለው ቼልሲ ደግሞ ሞሬካምቤን በስታምፎርድ ብሪጅ የሚያስተናግድ ይሆናል።

🔸የሦስተኛ ዙር የኤፍኤካፕ ጨዋታዎቹም ከጥር 2 እስከ ጥር 5 ባሉት ቀናቶች በተለያዩ ስቴዲየሞች የሚካሄዱ ይሆናል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


💠 አርጀንቲናዊው የቀድሞ ተጫዋች ሀቨዬር ማሻራኖ ታታ ማርቲኖን በመተካት አዲሱ የኢንተር ማያሚ ዋና አሰልጣኝ በመሆን በይፋ ተዋውቀዋል።

💠 ከመጪው 2025 ጀምሮ ከጓደኛው እና ከቀድሞ የቡድን አጋሩ ሊዮ ሜሲ ጋር አብሮ የመስራት ዕድል ያገኘው ማሻራኖ በሊዮ ጠቋሚነት እንደተቀጠረ ዘ ኢንዲፔንደንት አስነብቧል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስረኛ ሳምንት መርኃግብር ከዛሬ ጀምሮ ይደረጋል።

⚽️⚽️

10:00 ድሬደዋ ከተማ ከሲዳማ ቡና
01:00 መቻል ከቅዱስ ጊዮርጊስ

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


🔹በኤፍኤካፕ 3ኛ ዙር ኤቨርተን ከፒተርቦሮው ጋር መደልደሉን ተከትሎ አሽሊ ያንግ የ18 ዓመት የበኩር ልጁን በተቃራኒነት ይገጥማል።

🔹አሽሊ ያንግ ከድልድሉ በኋላ በመህበራዊ ትስስር ገፁ ህልሜ ዕውን ሆነ ብሎ በመፃፍ ሃሳቡን አጋርቷል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews










🔸ባሳለፍነው ሳምንት በአሜሪካዋ ኒውዮርክ ከተማ ለጨረታ የቀረበ አንድ ሙዝ በ750 ሚሊዮን ብር መሸጡ በርካቶችን አስደንቋል።

🔸ሙዙን በግድግዳ ላይ በፕላስተር በመለጠፍ ለጨረታ ያቀረበው ማውሪዚዮ ካቴላን የተባለ ጣሊያናዊ ለሙዙ ኮሜዲያን የሚል ስያሜ መስጠቱ ጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጓል ነው የተባለው።

🔸ለብዙዎች ስሜት የማይሰጥ ነው የተባለው "ኮሜዲያን" የሚል ስያሜ የተሰጠው የጥበብ ሥራ ለጨረታ ቀርቦ ከተጠበቀው በላይ በአራት እጥፍ የላቀ ዋጋ ማውጣቱ ተነግሯል።

🔸ይህንኑ የሙዝ ጨረታ አሸንፎ የገዛው ቻይናዊው የክሪፕቶከረንሲ ነጋዴ ጀስቲን ሰን ጨረታውን በ6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር መግዛቱ ጉድ ሲያሰኝ ስድስት ተጫራቾችን አሸንፎ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያፈሰሰበትን ሙዝ ከፕላስተሩ አላቆ እራሱ ተመግቦታል።

🔸ሙዙ በዓለማችን ውድ ዋጋ ያወጣ ፍራፍሬ ለመሆን ሲበቃ የጥበብ ሥራነቱ ምኑ ጋር ነው በሚል በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ መነጋገሪያ መሆኑን ኒዮርክ ታይምስ ዘግቦታል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


👉 ከሴቶች ጥቃት ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ክልል የተከሰቱና ህግን ተላልፈው የተገኙ የወንጀል ድርጊቶችን በመከታተል የህግ ውሳኔ መሰጠቱን የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል።

👉 በዚሁ መሰረት በአዳማ ከተማ ለፍቅር ግንኙነት አሰባትን ሴት በምትሰራበት ሆቴል ውስጥ በሥራ ላይ እያለች በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ መፈፀሙ በፍርድ ቤት የተረጋገጠበት ግለሰብ የዕድሜ ልክ ቅጣት እንደተወሰነበት ሲገለፅ በቦረና ዞን ደግሞ ከህብረተሰቡ ባህል እና እሴት ባፈነገጠ መልኩ የ3 ልጆች ሚስቱን ዋጨሌ ገበያ ላይ አስሮ በአሰቃቂ ሁኔታ ያስገረፈ እና በድርጊቱ መሳተፋቸው የተረጋገጠባቸው ሌሎች 3 ግለሰቦች እያንዳንዳቸው ከ4 እስከ 7 ዓመት የሚደርስ የእስር እና የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለባቸው ቢሮው ጨምሮ ገልጿል።

👉 ፆታዊ ጥቃት በሴቶችና ህፃናት ላይ ጥሎት የሚያልፈው ጠበሳ በቀላሉ የሚሽር አይደለም ያለው ቢሮው ጥቃቱን አስቀድሞ ከመከላከል ጎን ለጎን በአጥፊዎች ላይ አስተማሪ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ ገልጿል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews




⚽️ ተጠባቂ የነበረው የሊቨርፑልና ሲቲ ጨዋታ በሊቨርፑል የበላይነት የተጠናቀቀበት፤ የቺልሲ የዝምታ ጉዞና የአርሰናል ከረፍት በፊት የ5 ጎሎች ሪከርድ፤ የሩበን አሞሪም ማንችስተር መነሳሳትን ካስመለከተን አስራሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በኃላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ይህንን ይመስላል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


የዓለም አትሌቲክስ የ2024 የዓለም ምርጥ አትሌቶችን ይፋ ሲያደርግ ከስታዲየም ውጪ የሩጫ ውድድር ምርጫን ታምራት ቶላ አሸናፊ ሲሆን የዓለም የዓመቱ የወደፊት ተስፈኛ አትሌት በመባል ደግሞ ሲምቦ አለማየው ተመርጣለች።

ታምራት ቶላ በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ በወንዶች ማራቶን የውድድሩን ሪከርድ በማሻሻል ጭምር የኦሎምፒያዱ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ሲሆን ወጣቷ አትሌት ሲምቦ አለማየሁ ደግሞ በፓሪስ ኦሎምፒክ የዲፕሎማ ተሸላሚ ስትሆን በፔሩ ሊማ በተካሄደው የዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ3000ሜ መሰናክል የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ነበረች።

ባሳለፍነው ዓመት በተመሳሳይ ተደርጎ በነበረው የዓለም አትሌቶች የዓመቱ ምርጥ ከስታዲየም ውጪ ምርጫን ትዕግስት አሰፋ አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


ዛሬ ጠዋት በስፔን ቫሌንሺያ በተካሄደ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያቷ አትሌት መገርቱ ዓለሙ አሸናፊ ሆናለች።

በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ተሳታፊ የነበረችው አትሌት መገርቱ አለሙ ርቀቱን በቀዳሚነት ስትፈጽም የገባችበት ሰዓት ደግሞ 2:16.49 ሆኖ ተመዝግቧል።

በሴቶች ማራቶን ውድድር ዑጋንዳዊቷ ስቴላ ቼሳንድ ሁለተኛ ሆና ስትፈጽም ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊቷ ጥሩዬ መስፍን ሦስተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በወንዶች ቫሌንሺያ ማራቶን ውድድር  ዴሬሳ ገለታ 2:02.38 በመግባት ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ የብር ሜዳልያ አሸናፊ ሆኗል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሠላም ጥሪ በመቀበል ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ጋር የሠላም ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል።

የሠላም ስምምነቱ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ በክልሉ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ተፈጽሟል።

በመርኃግብሩ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመጡት ምስጋና አቅርበዋል።

መረጃው የኢ ፕ ድ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews

Показано 20 последних публикаций.