የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም የምሽት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች፡_
🌐👉በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የርዕድ መሬት አደጋ እያስተናገደ ባለው አዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ዛሬ እኩለ ቀን ላይ በማግኒቲውድ 5 የተመዘገበ ርዕድ መሬት መከሰቱን የጀርመን የጂኦሎጂካል ምርምር ተቋም አስታወቀ፡፡
❇️🔽የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ባለፉት ስድስት ወራት በፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች ላይ ከ300 በላይ ክሶችና ቅሬታዎች መቅረባቸውን አስታወቀ፡፡
👉👉የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሽግግር ፍትህ ፖለሲ ላይ በተቀመጠው መሰረት የልዩ ችሎት ማቋቋሚያ በረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱና ለውይይት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ፡፡ በተያያዘ በዚሁ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ተጎጂዎች በሚገኙባቸው አምስት ክልሎች ምክክር ለማድረግ መታቀዱን ተነግሯል፡፡
🇪🇹👉በኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2030 2.5 ሚሊዮን የሚገመቱ ልጃገረድ ሴቶች ለግርዛት ችግሮች ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ የመንግስታቱ ድርጅት አዲስ ባወጣው ሪፖርቱ አስታወቀ፡፡
🌐👉የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂዬቫ በነገው እለት አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
✅✅ልዩ መለያ ኮድ ወይም ኪው አር ኮድ የተካተተበት የልዩ ደረሰኝ ህትመት ጥያቄ የማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓመተ ምህረት ድረስ እንዲራዘም መወሰኑ ተነግሯል።
ዜና አዲስ ነገር ነው! አዲስ ነገርም ዜና ነው!"
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews