🇺🇸👨⚖የዩ ኤስ ኤይድ ሰራተኞች የግዳጅ ዕረፍት እንዲወጡ ያስተላለፉት ትዕዛዝ በፍርድ ቤት ታገደ፡፡
🇺🇸👨⚖ትራምፕ 2 ሺህ 200 የዩ ኤስ ኤይድ ሰራተኞች የግዳጅ ዕረፍት እንዲወጡ ያስተላለፉት ትዕዛዝ ሊተገበር ሰዓታት ሲቀሩት ነው ካርል ኒኮላስ የተሰኙ አንድ ዳኛ ትዕዛዙ እንዳይፈጸም እገዳ ያስተላለፉት፡፡
🇺🇸👨⚖እገዳው ለአንድ ሳምንት እንደሚቆይ የተነገረ ሲሆን ዳኛው ከዚህ እርምጃ ላይ የደረሱትም ሁለት የዩ ኤስ ኤይድ ሰራተኞች ማህበራት በፍርድ ቤት ክስ መመስረታቸውን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል፡፡
🇺🇸👨⚖ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካው አለለመምአቀፍ የተረድኦ ድርጅት ወይም ዩ ኤስ ኤይድ ካሉት 10 ሺህ ሰራተኞች መካከል 611 ብቻ ቀርተው ሌሎቹ በሙሉ ከስራ እንዲሰናበቱ ማቀዳቸውን ሲናገሩ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡
🇺🇸👨⚖ፕሬዝዳንቱ ዩ ኤስ ኤይድ አሜሪካ ቅድሚያ ከሚለው የአስተዳደራቸው አቋም ጋር የማይሄድ መሆኑን ደጋግመው ሲገልጹ የቆዩ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ግን የትራምፕ አስተዳደር የሀገሪቱን ህገ መንግስት እየጣሰ ነው ብሏል፡፡
🇺🇸👨⚖ታዲያ ዳኛው ባስተላለፉት ውሳኔ በቀጣይ ተጨማሪ ውሳኔዎች እስከተላለፉ ድረስ ሁሉም የድርጅቱ ሰራተኞች ክፍያ እንዲያገኙ እና ወደ ስራቸው እንዲመለሱ እንዲሁም ማንም ሰራተኛ የግዳጅ እርፍት እንዳይወጣ እንዲደረግ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ተብሏል፡፡
ዘገባው የዘነበ ኃይሉ ነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews