👉የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የአሜሪካው የተራድዖ ድርጅት ዩ.ኤስ.ኤይድ ፕሮግራሞችን የመከለስ ስራ መጠናቀቁን ጠቁመው 83 በመቶ የሚሆኑት የኤጀንሲው የቀድሞ ፕሮግራሞች ከዚህ በኋላ እንደማይቀጥሉ ገልጸዋል፡፡
👉ኤጀንሲው ከነበሩት 6 ሺህ 200 ፕሮግራሞች መካከል 5 ሺህ 200 የሚሆኑት ፕሮግራሞች ሙሉ በሙሉ በይፋ መሰረዛቸው ነው የተገለጸው፡፡
👉የትራምፕ አስተዳደር በዚህ 60 ዓመት በሞላው ኤጄንሲ ፕሮግራሞች ላይ 6 ሳምንታት የፈጀ ግምገማ ማካሄዱን የጠቆሙት ሩቢዮ በግምገማው 18 በመቶ የኤጀንሲው ፕሮግራሞች እንዲቀጥሉ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡
👉እነዚህ 18 በመቶ የሚሆኑት የእርዳታ እና የልማት ፕሮግራሞችም የሚቀጥሉት በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስር ብቻ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
👉ሩቢዮ በኤክስ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በለጠፉት መልዕክት ኤሎን መስክ የሚመሩት የዶጅ ቢሮ ሰራተኞች ለረጅም ሰዓታት የኤጀንሲውን ፕሮግራሞች በመገምገም ለዚህ ታሪካዊ ለውጥ ስላበቁዋቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews