በ72 ከተሞች የኤሌክትሪክ መስመሮችን ማሻሻል የሚያስችል ፕሮጀክት ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው
በ11 ክልሎች በሚገኙ 72 ከተሞች ላይ የኤሌክትሪክ መስመሮችን ለማሻሻልና ዓቅም ለማሳደግ የሚያስችል የኢነርጂ ዘርፍ ሪፎርም ኢንቨስትመንት እና ዘመናዊነት በኢትዮጵያ (ፕራይም-1) የተሰኘ ፕሮጀክት ለመተግበር ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡
ፕራይም-1 ፕሮጀክት በዋናነት የኃይል አቅርቦት ጥራትን ለማሻሻል፣ የከተሞችን ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማሳደግ፣ የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል እና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን አስትማማኝ ለማድረግ ያለመ ነው።
ፕሮጀክቱ በ72 ከተሞች የሚገኙትን የመካከለኛና ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ መስመሮችን የሚያሻሻል እና የሚያዘመን ሲሆን፤ በዚህም የትራንስፎርመሮችን አቅም ማሻሻል፣ የኃይል ብክነት መቀነስ፣ የቮልቴጅ መዋዠቅ ማስተካከልና በኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን የጥራት ጉድለት መቀነስ እንዲሁም አስተማማኝነትን ለመጨመር ያስችላል…..ሙሉውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡- http://www.eeu.gov.et/contents/press-release?lang=am