ጉዳዩን ለማስተባበል የተሄደበት ርቀት እንደ ሀገር የገባንበትን ዝቅጠት ያሳያል!
ማስተባበያው ወጣቷ የዩኒቨርስቲው ተማሪ አልነበረችም አይለንም፣ ብቻ "ዩኒቨርሲቲው የፋርማሲ ትምህርት ሲሰጥ በ2013 የሁለተኛ ዓመት ተማሪ እንዳልነበረው ይገልጻል" ብሎ ለጭብጡ አላስፈላጊ የሆነ ነገር መዞ ክስ ለመመስረት ይዝታል። ለመሆኑ እንደ ተቋም ተማሪዎቹ ሲታገቱ ምን አደረገ?
ኢቢኤስ ላይ የተደረገውን ማስፈራራት ሳይ ትዝ ያለኝ ይህን ዜና በወቅቱ ለ Associated Press ስፅፍ የደረሰብኝ ወከባ ነበር: https://apnews.com/general-news-ab7fd681148f0b7317beaa3b19c9ad1a
አንዴ የታገተ ተማሪ የለም፣ ሌላ ግዜ በሙሉ ተለቀዋል፣ ቆይተው ደግሞ ስድት ብቻ ነው የቀሩት እያሉ ጉዳዩን ሲያምታቱ የነበሩት የመንግስት ባለስልጣናት ነበሩ፣ እኛንም ቢሯቸው እየጠሩ ዜና መስራት እንድናቆም ሲጠይቁ ነበር። አሁን ጉዳዩ ቆይቶ ለህዝብ ሲደርስ ደግሞ ሌላ ማስፈራርያ።
በዚህ አካሄዳቸው ልጅቱንም ሊያስፈራሩ ይችላሉ፣ ስለዚህ በቅርብ እንከታተላለን። ልጅቱን ለማገዝም እንቅስቃሴ እናደርጋለን፣ እስካሁን በስልኳ ለማግኘት ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም።
በነገራችን ላይ፣ የእገታ ዜና ሰልችቶን ዜና ሳይመስለን የምናልፍበት እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ተፈጠረ እንጂ በየሳምንቱ የሚታገቱትም እጣ ፈንታቸው ይሄው የልጅቷ ነው። ባለፈው ሳምንት ብቻ ሁለት ሙሉ አውቶቡስ ህዝብ ታግቷል፣ የሁለት አመት ህፃን ልጅን ጨምሮ።
በቃችሁ ይበለን።
@EliasMeseret