ያከበርከኝ
ያከበርከኝ እኔ ማነኝ
ያስከበርከኝ እኔ ማነኝ
ውለታህ በዛ አባቴ ውለታህ በዛ
ሞገስ ከበባት ቅጽሬ ሆንከኝ መዓዛ
ማዕበሉ አለፈ ባንተ ያለኝ አላሳልፍ
ስኬቴን ጻፈው ጣትህ የመኖሬን መጽሐፍ
'ቃልህ ባያዘው ጭንቄን ባያደላድለው
ዓለም ትለኝ ነበር እኔን መድረሻ የሌለው/2/
አዝ_______
ቀን አየች ነፍሴ ባ'ንተ ከመሶብህ በልታ
ከእሳት ማዕበል ነጥቀህ አኖርካት በከፍታ
'ቀን በቀን ቅኔን ይዤ በፊትህ ምንጓደደው
ሚዛንህ ጸጋ ሞልቶት በፍቅርህ ተምሬ ነው/2/
አዝ_______
በወኅኒ ብርሃን ሞላ ሰንሰለቱ ቀለጠ
በድካሜ እየራራ ሞት በሞትህ ተዋጠ
'ስለአንተ ማን አወቀ ጠንቅቆስ ማን ተረዳ
እኔ ግን ቀምሼ ነው የምለው ማራናታ/2/
አዝ_______
መፍረድ የማይሰለቻት ምድሪቱ ከሳሽ ሆና
ሲገርማት ውሎ ያድራል ስሰለፍ ለበገና
'የዘንዶ ጥርሱ ሲፏጭ ጉድጓድ እየተማሰ
በምስጋናዬ ብቻ ኑኖሬዬ ተዳበሰ/2/
አዝ_______
ያህዌን ያለ ሲወድቅ ማን አለ የከሰረ
አያይም አይኔ ጉድለት ይኖራል እየዘመረ
'ኑሃሚን እንዳየች በእንባ ማዕበል ሆና
ማግኘት ይመጣል ፈጥኖ አላዝንም በፈተና/2/
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም
እ_ን__ዘ__ም____ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እ_ን__ዘ__ም____ር
ያከበርከኝ እኔ ማነኝ
ያስከበርከኝ እኔ ማነኝ
ውለታህ በዛ አባቴ ውለታህ በዛ
ሞገስ ከበባት ቅጽሬ ሆንከኝ መዓዛ
ማዕበሉ አለፈ ባንተ ያለኝ አላሳልፍ
ስኬቴን ጻፈው ጣትህ የመኖሬን መጽሐፍ
'ቃልህ ባያዘው ጭንቄን ባያደላድለው
ዓለም ትለኝ ነበር እኔን መድረሻ የሌለው/2/
አዝ_______
ቀን አየች ነፍሴ ባ'ንተ ከመሶብህ በልታ
ከእሳት ማዕበል ነጥቀህ አኖርካት በከፍታ
'ቀን በቀን ቅኔን ይዤ በፊትህ ምንጓደደው
ሚዛንህ ጸጋ ሞልቶት በፍቅርህ ተምሬ ነው/2/
አዝ_______
በወኅኒ ብርሃን ሞላ ሰንሰለቱ ቀለጠ
በድካሜ እየራራ ሞት በሞትህ ተዋጠ
'ስለአንተ ማን አወቀ ጠንቅቆስ ማን ተረዳ
እኔ ግን ቀምሼ ነው የምለው ማራናታ/2/
አዝ_______
መፍረድ የማይሰለቻት ምድሪቱ ከሳሽ ሆና
ሲገርማት ውሎ ያድራል ስሰለፍ ለበገና
'የዘንዶ ጥርሱ ሲፏጭ ጉድጓድ እየተማሰ
በምስጋናዬ ብቻ ኑኖሬዬ ተዳበሰ/2/
አዝ_______
ያህዌን ያለ ሲወድቅ ማን አለ የከሰረ
አያይም አይኔ ጉድለት ይኖራል እየዘመረ
'ኑሃሚን እንዳየች በእንባ ማዕበል ሆና
ማግኘት ይመጣል ፈጥኖ አላዝንም በፈተና/2/
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም
እ_ን__ዘ__ም____ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እ_ን__ዘ__ም____ር