የኦሬንታል አብያተ ክርስቲያናት የጋራ ጉባኤ እና ሥርዓተ ቅዳሴ መርሐ ግብር (Oriental Orthodox Concelebration) የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ቋሚ ጉባኤ (SCOOCH) አሰናጅነት ቅዳሜ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 19 ቀን 2024 በሰሜን አሜሪካ ኒውጀርሲ የማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን (Old Tappan) እንደሚካሄድ አብያተክርስቲያናቱ አሳውቀዋል።
በዚህም ሥነ ሥርዓት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ጨምሮ የአርሜንያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ;የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ; የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ; የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት ይሳተፉበታል።
የዝግጅቱ አሰናጅ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ቋሚ ጉባኤ The Standing Conference of Oriental Orthodox Churches in America እኤአ 1973 ዓ.ም የተመሠረተ ሲሆን
የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በጋራ ጉዳዮች ላይ ምክክር የሚያደርጉበት ጉባኤ ሲሆን ; ባለፉት ዓመታት በርካታ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች በየቤተ ክርስቲያኖቻቸው የጉባኤው አባል ሆነው በመወከል ለድርጅቱ እድገትና መስፋፋት ትልቅ አስተዋፅዖ አድርገዋል። በጉባኤው በርካታ የሥነ መለኮት ጉዳዮች ላይ ምክክር ሲያደርግ ቆይቷል።
በመ/ር አቤል አሰፋ