ንጉሡና የእሱ ተከታዮች የሚሰግዱለት ጣዖትም ምንም ምን ማድረግ የማይችል ደካማ ፍጡር መሆኑን በሚገባ ከአስረዳ በኋላ ሰማይና ምድርን፣ የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ የፈጠረውን እውነተኛውን አምላክ እንዲያመልኩና ለእሱም እንዲሰግዱ እያስተማረ የንጉሡን ሚስት ንግሥቲቱን ሳይቀር ሕዝቡን ሁሉ በማሳመን የሰማዕትነት ተግባሩን ቀጠለ፡፡ ከሐዲውና ጣዖት አምላኪው ዱድያኖስ በአምልኮ ጣዖት የፀና፣ እውነተኛውን አምላክ እግዚአብሔርንም የካደ ከመሆኑ የተነሣ እሱ ቃሉን ሰምቶ በእውነተኛው አምላክ ማመን ሲገባው በተቃራኒው ቅዱስ ጊዮርጊስ እሱ ለሚያመልከው ጣዖት ቢሰግድና በእሱም ጣዖት ቢያመልክ ከአባቱ የበለጠ ሹመትና ክብር እንደሚሰጠውና ከእሱም ቀጥሎ ባለው የመንግሥት ሥልጣን ላይ እንደሚያስቀምጠው ደጋግሞ ቃል በመግባት ያባብለው እንደነበር ስለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋድሎ በተጻፈው መጽሐፈ ገድል በሰፊው ተጽፎ ይገኛሉ፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን የእግዚአብሔርን እውነተኛ አምላክነት፣ ከሀላፊነቱንና ኃያልነቱን በሚገባ ያወቀ ከመሆኑም በላይ የዚህን ዓለም ከንቱነት ከልብ የተረዳ ስለሆነ የንጉሡ የዱድያኖስ ቃል አለታለለውም፣ ጊዜያዊ ሹመትና ሽልማትም አልማረከውም፡፡ እንዲያውም ሰባት ዓመት ሙሉ ተጋድሎውን በመቀጠል እጅግ አሰቃቂና ዘግናኝ የሆኑ ፀዋትወ መከራዎችን በመቀበል የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ምስከር ሆኖአል፡፡ ብዙ አስደናቂ ተአምራትንም በማድረግ ብዙ አሕዛብን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ አድርጓል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስም በዱድያኖስና በሰባ ነገሥታት ፊት በቆመ ጊዜ በዚያም የተቀመጡባቸው የዕንጨት ወንበሮች ነበሩ፡፡ ቅዱሱንም እሊህን የተቀመጥንባቸውን ወንበሮች እንዲበቅሉ እንዲአብቡና እንዲአፈሩ ታደርጋቸው ዘንድ ከአንተ እንሻለን አሉት፡፡ በዚያን ጊዜ ጸለየ፤ እንዳሉትም አደረጋቸው፤ ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው በርካቶች በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ፡፡ ከሃዲው ንጉሥ ዱድያኖስ ግንድ አምጥተው ቅዱስ ጊዮርጊስን በግንዱ ላይ እንዲቸነክሩት አዘዘ፤ በላዩም ላይ ሰም አፍስሰው እሳት እንዲያነዱበት አደረገ፡፡ ከዚያም ቅዱሱን ወስደው በጐድጓዳ ብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት፡፡ አቃጥለው፣ አሳርረው ሥጋውንና አጥንቱን ፈጩት፤ አንጀቱ ሁሉ ወጥቶ ከምድር ላይ እስኪዘረገፍ ድረስ አሰቃዩት፡፡ በዚህም ነፍሱ ከሥጋው ተለየች፡፡ የሰማዕቱን ሥጋ አቃጥለው ፈጩት አመዱንም በቀፎ አድርገው ይድራስ ወደሚባል ተራራ ላይ በተኑት “ደብረ ይድራስ” ማለት ምድረ በዳ የሆነ ቦታ ነው፡፡ ጌታችንም የሰማዕቱን ነፍሱን ወደ ሥጋው መልሷት ደግሞ አስነሣው፡፡ ወደ ነገሥታቱም ተመልሶ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከ፡፡ በርካታ አሕዛብም ይህንን ታላቅ ተአምራት አይተው አምነዋል፡፡ በኋላም በሰማዕትነት አልፈዋል፡፡ ይህ የሆነው ጥር ፲፰ ቀን ነው ይህንንም ቀን “ዝርዎተ አጽሙ” ስትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰማዕቱን አዘክራ ትውላለች፡፡ በስሙ በታነጹለት አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ታቦተ ሕጉ ውጥቶ በደማቅ ሥነ ሥርዐት ተከብሮ ይውላል፡፡
የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፡፡ አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ዋቤ መጻሕፍት፡-
✍️ መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ
✍️ መጽሐፈ ሰዓታት
✍️ መጽሐፈ ስንክሳር