ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ ልሂቃን በውስጣቸው ያለውን ልዩነት በመግባባት፣ በሰላም እና የትግራይ ሕዝብን አንድነት በሚያረጋግጥ መንገድ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ለክልሉ ልሂቃን እና ለትግራይ ሕዝብ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ምክረ ሃሳብ ለግሰዋል፡፡
በመልዕክታቸውም÷ የትግራይ ሕዝብ ሀገሩን የሚወድ፣ ሰላም፣ እፎይታና ስራ ወዳድ መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የትግራይ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ የመንግስትን ምንነት በሚገባ የሚያውቅና ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር በመሆን ሀገረ መንግስት የመሰረተ ህዝብ መሆኑን አውስተው፥ ሀገረ መንግስት አደጋ ላይ በሚወድቅበት ጊዜም ቢሆን ከባድ ዋጋ በመክፈል ሀገረ መንግስት ያፀና ነው ሲሉ ጠቅሰዋል።
ለዚህም ድርቡሽ፣ ግብፅ፣ ጣልያን በኋላ ደግሞ በምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ለመጡት ወራሪዎች ለክብሩና ለሀገሩ ሉዓላዊነት ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በመተባበር መታገሉንና መስዋዕት መክፈሉን ለአብነት አንስተዋል። የትግራይ ሕዝብ ትንሽ ሰላም ባገኘበት ወቅት፥ በንግድ፣ እርሻ፣ ስነ ህንፃ፣ ጥበብ እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች የሰራቸው አስደናቂ ተግባራት መኖራቸውንም አስገንዝበዋል።
ከዚህ ባለፈም የትግራይ ሕዝብ በፈተና የማይናወጥ መንፈሰ-ጠንካራ ሕዝብ መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አጽንኦት የሰጡት፡፡ይሁን እንጅ መጥፎ አጋጣሚ ሆኖ በተለይ ባለፉት 100 ዓመታት በተለያዩ አጋጣሚዎችና በተለያዩ ምክንያቶች፣ በተለይ ደግሞ ከማዕከላዊ መንግስት ጋር ባጋጠመ አለመግባባት የትግራይ መሬት የጦርነት አውድ፤ የትግራይ ህዝብ ደግሞ የጦርነት ሰለባ መሆኑን ገልፀዋል። ምክንያቱ የፈለገ ይሁን መነሳት ያለበት ጥያቄ፥“ባለፉት 100 ዓመታት በተደረጉት ጦርነቶች የትግራይ ሕዝብ ያገኘው ማሕበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፀጥታዊ ትርፍ አለ ወይ? ምንስ ከሰረ?” ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው ብለዋል።
በዚህ ወቅት አንድ ልባም ትግራዋይ ልሂቅ፥ “ትግራይና ሕዝቧ ከጦርነት ያገኙት ነው ወይስ ያጡት የሚበዛው?” ብሎ መጠየቅና መልስ ማግኘት እንደሚገባውም መክረዋል። በተጨማሪም የተደረጉ ጦርነቶች ብቸኛ አማራጭ ነበሩ ወይ? ሌላ መፍትሔ አልነበረም ወይ? ከዚህ በኋላስ ጦርነት እንዳይነሳ ምን መደረግ አለበት? የሚሉ ጥያቄዎችን ማቅረብ ተገቢ እንደሆነም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት አፅንኦት ሰጥተዋል።
የትግራይ ህዝብ የትላንት ቁስሉ ሳይሻር፣ ገና አሁንም ሰላምና እፎይታ አግኝቶ ሰርቶ እንዳይገባና እንዳያለማ በፍራቻና ጭንቅ የጦርነት ወሬ እየኖረ መሆኑ አሳዛኝ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡ እንደዚህ አይነት አደጋን እንዴት መፍታት ይቻላል የሚለው በእርጋታ መነጋገር የሚያስፈልገው ጉዳይ እንደሆነም አመላክተዋል።
በመሆኑም በፖለቲካ፣ ንግድ፣ ፀጥታ፣ አካዳሚ፣ ሚዲያና ሌሎች አውዶች ያሉትን የትግራይ ልሂቃንና መላው የትግራይ ሕዝብ እስካሁን የተከፈለው ዋጋ ይበቃል፣ ከጦርነት የሚገኝ ትርፍ የለም በማለት መጀመሪያ በውስጣቸው ያለውን ልዩነት በመግባባት፣ በመደጋገፍ፣ በሰላምና የትግራይ ሕዝብን አንድነት በሚያረጋግጥ የሰለጠነ መንገድ እንዲፈቱ ጠይቀዋል። በተጨማሪም ከፌዴራል መንግስት ይሁን ሌሎች ሃይሎች ጋር ያሉትን ልዩነቶች በኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት እና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በመግባባት ለመፍታት ዝግጁ እንዲሆኑ መክረዋል።
በፌዴራል መንግስት በኩል፥ በሁሉም ጉዳዮች ለመነጋገር እና የሐሳብ ልዩነት እንደ ልዩነት በመውሰድ በሚያግባቡ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በሰላም መስራት የሚያስችሉ ሁኔታዎች እንዳሉ መገንዘብ እንደሚገባም ጠቅሰዋል፡፡
ይህንን በመገንዘብ ልሂቃን ሕዝቡን ከስጋት፤ እናቶችን እንቅልፍ ከማጣት፤ ወጣቶችን ደግሞ ከስደት ለማዳን እንዲሰሩ ከሁሉም በላይ ግን የትግራይ ሕዝብ ወደ ልማቱ እንዲመለስ በጋራ እንስራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ