ጆዜ ሞሪኒሆ ተቀጡ
በቱርክ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ ከጋላታሳራይ በነበራቸው ጨዋታ ያልተገባ ድርጊት የፈጸሙት አሰልጣኙ የ3 ጨዋታ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
ፌነርባቼ 2 ለ 1 በተሸነፈበት ጨዋታ ፖርቹጋላዊው ጆዜ ሞሪኒሆ የጋላታሳራይ አሰልጣኝ የሆነውን ኦካን ቡሩክ አፍንጫ ይዘው በመጎተታቸው ነው ቅጣቱ የተጣለባቸው።
የቀድሞው የቼልሲ እና ማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ በተጨማሪም የ5 ሺህ 955 ፓውንድ የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
ሁሌም ብጥብጥ በማያጣው የኢስታምቡል ደርቢ ፌነርባቼ 2 ለ 1 ተሸንፎ ከውድድር መሰናበቱ የሚታወስ ነው::
በዚህ ጨዋታ ላይ ሁለት የጋላታሳራይ እና አንድ የፌነርባቼ ተጫዋች ቀይ ካርድ መመልከታቸውም አይዘነጋም።