የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት አሻራ መስጫ ቀን ያለፈባቸውን ደንበኞች የቅጣት ክፍያ በማስቀረት በአዲስ ምዝገባ 5 ሺጭ ብር እና 6 ወር ቀጠሮ መጠበቅ ግዴታ እንዲኾን ማድረጉን አስታውቋል።
ቀደም ባለው አሠራር፣ የአሻራ መስጫ ቀን ያለፈባቸው ቅዳሜ ቀን በመሄድና 1 ሺሕ ብር የቅጣት ክፍያ በመክፈል ይስተናገዱ ነበር።
ቀጠሮ ያለፈባቸው ደንበኞች በአዲስ ምዝገባ ማለትም 5 ሺሕ ብር ከመክፈልና 6 ወር ከመጠበቅ በቅጣት 1 ሺሕ ብር መክፈል ይሻላል በማለት ወደ ውስጥ ለመግባት እየተጠባበቁ መኾኑን ለዋዜማ ተናግረዋል።
የፓስፖርት አሻራ መስጫ ቀጠሮ ያለፈባቸው ደንበኞች የመጨረሻ ቀን ባለፈው ቅዳሜ በመኾኑ፣ እጅግ በርከታ ሰዎች ከተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ሲስተናገዱ ዋዜማ ተመልክታለች።
ተቋሙ፣ ገንዘብ ሚንስቴርን ሳያስፈቅድ በግለሰብ ስም አካውንት በመክፈት ከ1 ሺሕ እስከ 1 ሺሕ 500 ብር ቅጣት ሲያስከፍል እንደነበርና በዚኹ አካውንት 17 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ገደማ ገቢ ስለመደረጉ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኦዲት ሪፖርት መረጋገጡ ይታወሳል።
https://t.me/ethio_mereja_news