የኮሪደር ልማት የፍራስራሽ ግምትን ለግል ጥቅማቸው ለማዋል የሞከሩ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያካሄደው ባለው የኮሪደር ልማት ሥራ ከተማዋን የሚመጥኑ ሰፋፊ የመንገድ መሠረት ልማቶችን እና ግዙፍ ተሻጋሪ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ላይ መሆኑን ባወጣው መግለጫ አንስቷል።
በተለይ በየካ ክፍለ ከተማ በካዛንችስ የኮሪደር ልማት ሥራ መንግሥትና ህዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ከልማቱ ፍራስራ ላይ ለግል ጥቅማቸው ሊያውሉ የነበሩ የወረዳ 06 አመራሮች አስተዳደሩ በዘረጋው የህዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ በትናንትናው ዕለት በፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር በማዋል ሌብነት የልማቱ እንቅፋት እንዳይሆን ተገቢውን እርምጃ መውሰዱን አስተዳደሩ አስታውቋል።
በዚሁ መሠረት በየካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ራሄል ኃ/ኢየሱስ፣ የወረዳው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደበበ ጉልማ፣ የወረዳው የፋይናስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ ግዛቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል ብሏል መግለጫው።
ግለሰቦቹ የኮሪደር ልማትን መነሻ አድርገው የፍራስራሽ ግምትን ለግል ጥቅማቸው ለማዋል በመሞከር ላይ እያሉ የከተማዋ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እስከ ክፍለ ከተማ ያለውን መዋቅሩን በመጠቀምና ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን ገልጿል።
የወንጀል ማጣራት ሥራው በሚመለከተው አካል እየተካሄደ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፥ ሌብነትን እና ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት የሚደረገው ትግል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁሞ፤ ህብረተሰቡም ጥቆማ በመስጠት የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።
https://t.me/ethio_mereja_news