ዶ/ር ደብረፂዮን የህወሃት ምሥረታ 50ኛ ዓመት በዓል ላይ ምን አሉ?!
ዛሬ ጠዋት በመቐለ በሚገኘው ትግራይ ስታድየም በነበረ ስነስርዓት በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሠራዊት አዛዦች፣ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት በተለያዩ ፕሮግራሞች በዓሉ ተከብሯል።
በዚሁ መርኀግብር የህወሓት አንዱ ክንፍ ከፍተኛ አመራሮች፣ የትግራይ ሐይሎች ወታደራዊ አዛዦች፣ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች እና ሌሎች የታደሙ ሲሆን በዚሁ መድረክ ንግግር ያደረጉት የህወሓት መሪ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፥ 50ኛ ዓመት በዓሉን እየተከበረ ያለው ከጦርነት መልስ ፤ ጦርነቱን ያስቆመው የፕሪቶርያ ውል ሳይፈፀም ነው ብለዋል።
ደብረፅዮን «ወራሪዎች ከሕገመንግሥታዊ ሉአላዊ የትግራይ ግዛት አልወጡም። በሕዝባችን ላይ ለተፈፀመው «ጀኖሳይድ» ተጠያቂነት የሚያረጋግጥ ሂደት አልተጀመረም። በህወሓት እና የኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ፖለቲካዊ ንግግርም ቢሆን ገና አልተጀመረም። የዳግም ግንባታ ሥራዎችም በአግባቡ አልተጀመሩም። ከዚህ አልፎ ደግሞ የፕሪቶርያ ውል ፈራሚ እና ተደራዳሪ የሆነው ህወሓት የተሰረዘ ሕጋዊ ሰውነቱን መመለስ ያልቻለ ሲሆን ወደማያስፈልግ ውዝግብ የሚያስገቡ ውሳኔዎች እየተላለፉ የፕሪቶርያው ስምምነትን ወደ አደጋ የሚያስገባ ተግባር እየታየ ነው» ብለዋል።
በዛሬ የትግራይ ስታድዮም መድረክ ላይ የተናገሩት ዶክተር ደብረፅዮን የኢትዮጵያ መንግሥት የሰላም ስምምነቱን ይተግብር ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥትም ቢሆን የትግራይ ጉዳይ በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ብቻ እንደሚፈታ አምኖ ለፖለቲካዊ ንግግር ዝግጁ ሆኖ የፈረመውን ስምምነት በታማኝነት እንዲፈፅም ጥሪ እናቀርባለን» ሲሉ አክለዋል።
@ethio_mereja_news