መረጃ‼️
የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር፣ ለከተማዋ የኮሪደር ልማት ከመደበው 15 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ውስጥ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚኾነውን ከከተማው ነዋሪዎች ለመሰብሰብ ማቀዱ ገልጿል።
የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አስሜ ብርሌ፣ የከተማ አስተዳደሩ ለኮሪደር ልማቱ ከትልልቅ ባለሃብቶች፣ ነጋዴዎች፣ ነዋሪዎችና ከመኖሪያ ቤትና የንግድ ድርጅቶች አከራዮች በደረሰኝ ገቢ እየሰበሰበ መኾኑንና በተያዘው ዓመት 1 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን ተናግረዋል።
የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋይ ነጋዴዎች 30 ሺሕ ብር፣ የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች 15 ሺሕ ብር፣ የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋይ ነጋዴዎች 10 ሺሕ ብር፣ የመኖሪያ ቤት አከራዮች 2 ሺሕ ብር እና ነዋሪዎች 1 ሺሕ ብር እና ከዚያ በላይ እንዲከፍሉ እየተደረገ መኾኑን ዋዜማ ተረድታለች።
በኮሪደር ልማቱ ቀጥታ ተጠቃሚ የኾኑ ወይም መንገድ ዳር የሚገኙ መንግሥታዊ ተቋማት፣ የግል ድርጅቶችና ባለሃብቶች ለብቻ ተመን እንደወጣላቸው ምክትል ከንቲባው ገልጸዋል።