በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሕገ መንግስት ማሻሻያ ላይ አቤቱታ ያቀረቡ የክልል ምክር ቤት አባል ታሰሩ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) ተመራጭ የሆኑት አቶ ዮሐንስ ተሰማ ዛሬ እሁድ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ተኩል ገደማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ባለቤታቸው እና የፓርቲው ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ። አቶ ዮሐንስ በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው አስቀድሞ፤ “የጉዞ እግድ እንደተጣለባቸው” ተነግሯቸው ከአሶሳ አየር ማረፊያ እንዲመለሱ መደረጋቸውንም ምንጮቹ ተናግረዋል።
አቶ ዮሐንስ ዛሬ ጠዋት በአሶሳ አየር ማረፊያ የተገኙት፤ ጽህፈት ቤቱ በአዲስ አበባ ለሆነው ለፌደራል የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ያስገቡትን አቤቱታ በአካል እንዲያስረዱ በመጠራታቸው እንደሆነ ምንጮቹ አስረድተዋል። ለአጣሪ ጉባኤው የቀረበው አቤቱታ፤ ከአቶ ዮሐንስ በተጨማሪ አቶ አመንቴ ገሺ እና አቶ ተስፋሁን ኪሉ የተባሉ የቦዴፓ የክልል ምክር ቤት ተመራጮችን ስም የያዘ ነው።
አቤቱታው ከሁለት ሳምንት በፊት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ምክር ቤት በአብላጫ ድምጽ የጸደቀውን የክልሉ ህገ መንግስት ማሻሻያ የተመለከተ ነው። የህገ መንግስት ማሻሻያው “የኢፌዲሪን ህገ መንግስት የሚቃረን ነው” ሲሉ በአቤቱታቸው የጠቀሱት፤ ሶስቱ የክልል ምክር ቤት አባላት አጣሪ ጉባኤው የህገ መንግስት ትርጓሜ በመስጠት “ተፈጻሚ እንዳይሆን” እንዲያደርግ ጠይቀው ነበር። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)