ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ስለሆነችው ብርቱካን ተመስገን ከበደ ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ ማብራሪያ
ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ስለሆነችው ብርቱካን ተመስገን ከበደ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ግንኙነት ስላለው ማብራሪያ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
በስም ተጠቃሽ በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪ የነበረች ቢሆንም የብሄራዊ ፈተናው በወቅቱ በተፈጠረው ዓለም ዓቀፍ የኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 02/2013 ዓ.ም እንዲሰጥ መደረጉ ይታወሳል። ተማሪዋም በዚሁ ጊዜ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በምስራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ መሰናዶ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፈተና ወስዳ 392 ውጤት በማምጣት በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ምደባ ተደርጎላታል፡፡ ሆኖም ግን ወደተመደበችበት ዩኒቨርሲቲ ያልሄደችና ያልተመዘገበች ሲሆን ወደ ሀዋሳ ከተማ በማቅናት በተከታታይ የትምህርት ኘሮግራም (ኤክስቴንሽን) ተመዝግባ “በአካውንቲንግና ፋይናንስ” የትምህርት ክፍል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ኘሮግራም ከግቢ ውጭ ሆና ትምህርቷን ስትከታተል የነበረችና ትምህርቷንም ሳትጨርስ ያቋረጠች መሆኑን ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተገኘ መረጃ ያረጋግጣል፡፡
በተቃራኒው በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ስርጭት በተላለፈው ፕሮግራም ግለሰቧ በሀሮማያ ዩኒቨርስቲ ተመድባ ወደ ሀሮማያ በመጓዝ ላይ ሳለች አውቶቡስ ውስጥ ባገኘቻት ደምቢደሎ ዩኒቨርስቲ ተመድባ በመጓዝ ላይ ካለች ሌላ ተማሪ ጋር በመነጋገር ሀሮማያ ዩኒቨርስቲ የነበራትን ጉዞ በመሰረዝ ወደ ደምቢደሎ ዩኒቨርስቲ ሄዳ ለመማር ተመዝግቢያለሁ ማለቷ ከእውነታውና ከአሰራር ውጭ የሆነና በፍጹም ወደ ደምቢደሎ ዩኒቨርስቲ ያልሄደችና ምዝገባም ያላደረገች መሆኑ የዩኒቨርስቲው መረጃ ያስረዳል። በዚህ አጋጣሚ ማንኛውም አይነት የአዲስ ተማሪዎች ምደባ የሚከናወነው በትምህርት ሚኒስቴር ብቻ እንጂ በዩኒቨርስቲዎች ደረጃ የማይፈቀድ መሆኑም ለማሳዎቅ እንወዳለን። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BuHUumVUJ/