በ1.6 ቢሊዮን ብር የተገነባው የቦሌ አራብሳ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ተመረቀ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቦሌ አራብሳ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያን ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻን በዘመናዊ መንገድ ለማስወገድና መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚረዳው የቦሌ አራብሳ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ በ1.6 ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባ መሆኑ ገልጸዋል።
በቀን 30 ሺህ ሜትሪክ ኪዩብ ፍሳሽ የማጣራት አቅም ያለው እና 240 ሺህ ነዋሪዎችን የስርዓቱ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑንም ተናግረዋል።
በነዋሪው የሚነሳው የውሃ አቅርቦት ለማሻሻልም የፍሳሽ ማስወገጃ ውሃን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል እንደሚያግዝ ተገልጿል።
የፍሳሽ ማጣሪያ ግንባታ ስራው በቻይናው ኩባንያው CGCOC Group የተከናወነ ሲሆን የግንባታ ቁጥጥር ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ማከናወኑ ተገልጿል።
በአዲስ አበባ ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻን በዘመናዊ መንገድ ለማስወገድና ለማገናኘት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ዛሬ ተመርቆ ወደ አገልግሎት የገባው የቦሌ አራብሳ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያም የስራው አካል ሆኖ ይቀርባል።ማጣሪያ ጣቢያው ከህብረተሰቡ የሚሰበሰበውን ፍሳሽ ሦስት የማጣራት ሂደት የሚያልፍ ነው።
በመጀመሪያ ደረጃ ቆሻሻን መቀበል፣ የፍሳሽ መጠን መለካት፣ ፕላስቲክ መሰል ቆሻሻን መለየት ያካትታል።
በሁለተኛ ደረጃም ከመጀመሪያ ምዕርፍ ያለፉ ቆሻሻን የማጣርት ሂደት የሚከናወንበት ሲሆን በሶስተኛው ምዕራፍ ደግሞ ካሎሪን በመጠቀም ውሃ ይጣራል። በስተመጨረሻ የተጣራው ፍሳሽ ለተለያዩ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚለው ይሆናል።
በመርሃ ግብሩ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ ተገኝተዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ ፣ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይና ሌሎች የከተማ አስተዳድሩ ከፈተኛ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።