የቤተሰብ እና የውርስ ጉዳዮች የሚታዩበት የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 1ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 243973 ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት በሰጠው ውሳኔ ቀደም ሲል በሰ.መ.ቁ 202548: 44237 : 38533 የወራሽነት የምስክር ወረቀት የያዘ ሰው በማንኛውም ጊዜ የውርስ ንብረት ጥያቄ ማንሳት ይችላል በማለት ተሰጥቶ የነበረውን የሕግ ትርጉም በመለወጥ በሌላ ልዩ ሕግ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የወራሽነት ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000 በተመለከተው የጊዜ ገደብ በይርጋ ይታገዳል። የውርስ ማጣራት ተጠናቆ ንብረቱ የጋራ ባልሆነበት ሁኔታ የወራሽነት ምስክር ወረቀት በመያዝ ብቻ የ/ፍ/ሕ/ቁ 1062 መሰረት በማድረግ ያለ ጊዜ ገደብ የክፍፍል ጥያቄ ሊነሳ አይችልም በሚል አዲስ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።
Via Etmet Asamrie ( Judge at Federal Supreme Court)
የፌዴራልጠቅላይፍርድቤት
Via Etmet Asamrie ( Judge at Federal Supreme Court)
የፌዴራልጠቅላይፍርድቤት
JOIN ስለ-ህግ ABOUT-LAW
Telegram- https://telegram.me/ethiolawblog
Facebook- https://m.facebook.com/aboutlawlegalservice
LinkedIn- https://www.linkedin.com/company/aboutethiopian-law
TikTok- https://www.tiktok.com/@aboutethiopianlaw1?_t=8qe3Ip7153m&_r=1