#CapitalNews የሪል እስቴት አልሚዎች ያልተገነባ ቤት በመሸጥ የሚሰበስቡትን ገንዘብ በዝግ አካዉንት እንዲያስቀምጡ የሚያስገድደዉ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ
ሪል ስቴት አልሚዎች ግንባታ ከማከናወናቸው አስቀድመው ቤት እንዳይሸጡ እና ከደንበኞቻቸው የሚሰበስቡትን ገንዘብ ደግሞ በዝግ የባንክ አካውንት እንዲያስቀምጡ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ፀድቋል።
በዚህ አዋጅ የይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፍቃድ ያላገኙ አልሚዎች ደንበኞችን መመዝገብ እና ክፍያ መቀበል የሚከለክል ሲሆን ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤቶችን ደግሞ ማስረከብ እንዳማይችሉ በዝርዝር አስቀምጧል ።
የማይንቀሳቀስ ንብረት ግመታ ስርዓቱ ዘመናዊና በመረጃ በተደገፈ መልኩ ተገማች ዋጋ እንዲኖረው ማድረግ በማስፈለጉ እና በማይንቀሳቀስ ንብረት ገበያው ግልጽነት መጓደሉ ምክንያት ረቂቅ አዋጅ እንዲወጣ መደረጉ ተገልጿል ነበር።
ይህን ተከትሎ የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ 1357/2017 ሆኖ በሁለት ተቃውሞ እና በአንድ ድምፀ ታቅቦ በአብላጫ ድምፅ መፅደቁ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።