ወራሽነት ማረጋገጫ የያዘ ሰው በማናቸውም ጊዜ ንብረት መካፈል ይችላል የሚለው ውሳኔ ተሽሯል።
የፌደራል የሰበር ሰሚ ችሎት ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት የወራሽነት የምስክር ወረቀት የያዘ ሰው በማንኛውም ጊዜ የውርስ ንብረት ጥያቄ ማንሳት ይችላል ተብሎ ከዚህ ቀደም በሰበር በመ/ቁ 205248፣ መ/ቁ 44237፣ 38533 የተሰጡ ውሳኔዎችን አሻሽሏል። በሌላ ልዩ ሕግ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የወራሽነት ጥያቄ በፍ/ሕ/ቁ 1000 በተመለከተው የጊዜ ገደብ በይርጋ ይታገዳል። የውርስ ማጣራት ተጠናቆ ንብረቱ የጋራ ባልሆነበት ሁኔታ የወራሽነት ምስክር ወረቀት በመያዝ ብቻ የፍ/ሕ/ቁ 1062 መሠረት በማድረግ ያለጊዜ ገደብ የክፍፍል ጥያቄ ሊነሳ አይችለም የሚል የሕግ ትርጉም ተሰጥቷል።
የውሳኔውን ይዘት ከዚህ ይመልከቱ
https://www.abyssinialaw.com/know-your-rights/case243973-inheritance-claim-timing-revoked
Join👇👇
https://t.me/ethiolawtips