የማይንቀሳቀስ ንብረት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ
በማቅረብ ብቻ የሚረጋገጥ አይደለም የሰ/መ/ቁ.
229608
በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 33(2) መሰረት ከሳሽ ባቀረበው ክስ ላይ
መብትና ጥቅም የለውም ተብሎ የሚወሰነው ክስ ባቀረበበት
ጉዳይ ላይ መብት ያለው ስለመሆኑ ማስረጃ ሳያቀርብ ሲቀር ነው፡፡አመልካች በስር ፍ/ቤት ክስ ባቀረበበት ንብረት ላይ መብትና ጥቅም ያለው ስለመሆኑ የተለያዩማስረጃዎችን (በሰበር አቤቱታው ላይ የተዘረዘሩ) ከክሱ ጋር አያይዞ አቅርቦ ሳለ የስር ፍ/ቤቱ አመልካች ክሱን ለማቅረብ መብትና ጥቅም የለውም በማለት ክሱን ውድቅ በማድረግ የሰጠው ብይን እና ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው፡፡ የስር ፍ/ቤት መብትና ጥቅም የማይንቀሳቀስ ንብረት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በማቅረብ ብቻ እንደሚረጋገጥ አድርጎ ብይን የሰጠ ሲሆን ይህም የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 36320(ቅጽ 9) በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ክስ ለማቅረብ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ማቅረብ ግዴታ አለመሆኑን እና ባለይዞታነት በሌላ መንገድ ሊረጋገጥ እንደሚችል ከሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ውጪ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው።👇👇.
https://t.me/ethiolawtips