#FactCheck በጅማ አየር ማረፊያ ፎቶ የተነሳው እቃ ጫኝ አውሮፕላን ለዓለም የምግብ ፕሮግራም አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ነው
ከ22,000 በላይ ተከታዮች ያሉትና ‘Amhara News Service’ የሚል ስያሜ የሚጠቀም የትዊተር አካውንት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ከትናት ወዲያ በስህተት መቶ የጣለው ኢሉሽን እቃ ጫኝ አውሮፕላን ከዚህ ቀደም በጅማ አየር ማረፊያ ታይቶ ነበር የሚል መረጃ ማጋራቱን ተመልክተናል።
ከመረጃው ጋርም ሁለት ፎቶዎችን ያያየዘ ሲሆን በአንዱ በጅማ አየር ማረፊያ የቆመ ኢሉሽን አውሮፕላን ይታያል። ይህንንም ከድንበር ዘለል የመሳሪያ ዝውውር ጋር አገናኝቶታል።
ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ በፎቶው ላይ ባደረገው ማጋጣራት በጅማ አየር ማረፊያ ቆሞ የሚታየው አውሮፕላን ለዓለም የምግብ ፕሮግራም አገልግሎት (World Food Program) ይሰጥ የነበር መሆኑን አረጋግጧል።
ፎቶግራፉ የተጋራውም የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ከመጀመሩ ከዓመታት በፊት እአአ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ሲሆን በአውሮፕላኑ ጎን ላይ ውሃ ሠማያዊ ቀለም ያለው የአለም ምግብ ፕሮግራም አርማ ይታይበታል።
ይህንንም ማስፈንጠሪያውን በመከተል መመልከት ይቻላል: https://www.instagram.com/p/BjKG3XrjizQ/?igsh=YzljYTk1ODg3Zg==
ፎቶውን ያነሳውና በኢንስታግራም ገጹ ያጋራው ሰው የአለም ምግብ ፕሮግራም አርማ የሚታይበትን አውሮፕላን የሚያስዩ ፎቶዎችን ከጅማ በተጨማሪ በጋምቤላ አየር ማረፊያ በማንሳት በኢንስታግራም ገጹ ያጋራ ነበር (https://www.instagram.com/p/B7Lf_AbpKOL/?igsh=YzljYTk1ODg3Zg%3D%3D) ።
የጅማ እና የጋምቤላ አየር ማረፊያዎችን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በደቡብ ሱዳን ለሚያደርገው የምግብ እደላ ለዓመታት ይጠቀምባቸው እንደነበር ይታወቃል።
ለምሳሌ በፎቶዎቹ ላይ ከሚታዩትና የመለያ ቁጥሩ EW-355TH የሆነውን አውሮፕላን እአአ በ2014 ዓ.ም ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ (UNICEF Ethiopia) በፍሊከር ገጹ አጋርቶት ነበር።
አውሮፕላኑ በደቡብ ሱዳን ለሚገኙ ተረጅዎች ከአየር ላይ የሚጣል ምግብ ከጋምቤላ አየር ማረፊያ እየጫነ መሆኑም ፍሊከር ላይ ይነበብ ነበር: https://www.flickr.com/photos/unicefethiopia/15898594070
በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የምንመለከታቸውን መልዕክቶች ከማመናችን እና ከማጋራታችን በፊት ትክክለኛ መሆናቸውን እንመርምር።
@EthiopiaCheck