#FactCheck ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ያለፉ ተማሪዎች በግል እንዲማሩ መወሰኑን የሚገልጽ ‘ደብዳቤ’ ሀሰተኛ ነው
ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ያለፉ ተማሪዎች በግል እንዲማሩ እንደተወሰነ የሚገልጽ ደብዳቤ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋራ ይገኛል።
በቀን 18/2/2017 እንደተጻፈ ተደርጎ እየተጋራ የሚገኘው ይህ ደብዳቤ የትምህርት ሚኒስቴር አርማ እና የሚንስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) “ፊርማ” አርፎበታል።
ደብዳቤው በመንግስት ይሰጥ የነበረው አቅም ማሻሻያ ፕሮግራም በበጀት እጥረት ምክንያት መቋረጡን እና ለፕሮግራሙ ያለፉ ተማሪዎች በግል እንዲማሩና የመንግስት ከፍተኛ ት/ት ተቋም መግቢያ ነጥብ ሲያመጡ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ያትታል።
ኢትዮጵያ ቼክ የዚህን ደብዳቤ ትክክለኛነት እንዲያጣራ ከተከታዮቹ ጥቆማዎች የደረሱት ሲሆን ጉዳዩን በተመለከተ መረጃ አግኝቷል።
በዚሁ መሰረት የትምህርት ሚኒስቴር እና የሚንስትሩን ስም እና “ፊርማ” ይዞ እየተሰራጨ የሚገኘው ደብዳቤ ሀሰተኛ መሆኑን ከት/ት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የትምህርት ሚንስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) “ሀሰተኛ መረጃ ነው” በማለት ደብዳቤው ትክክለኛ አለመሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል።
በተጨማሪም በደብዳቤው ላይ አጠራጣሪ የሆኑ የአፃፃፍ ሁኔታዎችን የተመለከትን ሲሆን በፎቶፎረንሲክስ መስል መመርመሪያ መሳሪያ ባደረግነው ማጣራትም ደብዳቤው ተመሳስሎ የተሰራ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶችን ተመልክተናል።
ተመሳስለው የሚሰሩ ሀሰተኛ ደብዳቤዎች ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ የመጣ ሲሆን ታማኝ ባልሆኑ ምንጮች የሚሰራጩ መሰል ደብዳቤዎችን አምነን ከመቀበላችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።
ኢትዮጵያ ቼክ
@EthiopiaCheck