#EthiopiaCheck የሰኞ መልዕክት
የማህበራዊ ትስስር ሚዲያ ድርጅቶች በጥላቻ ንግግር እና በሃሰተኛ መረጃ መቆጣጠር ላይ ያላቸው ሚና ምን መምሰል አለበት?
የጥላቻ ንግግር እና የሃሰተኛ መረጃዎች ስርጭት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየበዛ መቷል፡፡ ነገር ግን እነዚህ መረጃዎች የሚወጡባቸው የማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች በቂ የሚባል የመቆጣጠር (moderating) ስራ በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሰሩ አይታዩም።
እነዚህ ድርጅቶች በመጀመሪያ የተመሰረቱ ጊዜ በሚዲያቸው ላይ ለሚወጡ ጽሁፎችም ሆነ ማንኛውም አይነት ነገሮች ተጠያቂነታቸውን ከራሳቸው ላይ አንስተው ነበር፡፡ ሆኖም ግን በተለይ ከቅርብ አመታት ወዲህ ሰዎች ማንኛውንም አይነት መረጃዎችንም ሆነ ዜና የሚያገኙት በነዚህ የማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች ላይ ብቻ እየሆነ መቷል፡፡ ስለሆነም እነዚህ ድርጅቶችም ከብዙ ጫናዎች በኋላ በተወሰነ መልኩ በሚዲያዎቻቸው ላይ የሚወጡትን መረጃዎች አርተፊሻል ኢንተለጀንስን እና የሰው ሀይልን በመጠቀም መቆጣጠር ጀምረዋል፡፡
ሆኖም ግን የሃሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮች የመብዛታቸውን ያክል እነዚህ ድርጅቶች ሃላፊነት ወስደው ሲሰሩ አይታዩም፣ በተለይ የፖለቲካ ይዘት ባላቸው ጽሁፎች ላይ፡፡ የሚያንማር መንግስት በሮህንጊያ ሙስሊሞች ላይ ያሰራጨው የሃሰተኛ መረጃ ያስነሳውን ከፍተኛ እልቂት እንደ ምሳሌነት መመልከት እንችላለን፡፡
በሃገራችንም ደግሞ በተለይ ከ2015 አ.ም ጀምሮ በሚታዩት የተለያዩ አለመግባባቶች እና ግጭቶች ጀርባ በማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች ላይ የሚወጡት የሃሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮች ግጭቶቹን ከሚያባብሱት ውስጥ ናቸው።
የእነዚህ ሚዲያዎችን ቸልተኝነትን አስከትሎ በአለማችን ላይ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት መንግስታት በማህበራዊ ድህረ ገጽ ላይ የሚወጡትን መረጃዎች በተለይም የፖለቲካ ይዘት ያላቸውን መረጃዎች የሚቆጣጠሩበት መመሪያዎችን አውጥተዋል። እነዚህ መመሪያዎችን ካወጡ ሃገራት መካከል አውስትራሊያ እና ሲንጋፖር ይገኙበታል።
ኢትዮጵያም በቅርቡ ያጸደቀችው የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ውስጥ ለተቋማትና አገልግሎት ሰጪዎች ኃላፊነቶችን አስቀምጣለች።
ህጉ “ማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቆጣጠርና ለመግታት ጥረት ማድረግ አለበት። ድርጅቱ የጥላቻ ንግግርን ወይም የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን የተመለከተ ጥቆማ ሲደርሰው በሀያ አራት ሰዓት ውስጥ ይህን መሰል መልዕክቶችን ወይም ንግግሮችን ከአግልግሎት አውታሩ ሊያስወግድ ይገባል” ይላል።
ነገር ግን መንግስት እንደዚህ አይነት ህጎችን/መመሪያዎችን አውጥቶ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሚወጡትን መረጃዎች በሚቆጣጠሩበት ጊዜ የሰዎችን የመናገር መብትን ሲጋፉ እናያለን።
እንደ መፍትሄ ልናያቸው ከሚገቡ አስተያየቶች መካከል:
1. በእነዚህ ድርጅቶች ድህረ ገጽ ላይ የሚወጡትን እያንዳንዱን መረጃዎች የሚከታተሉ ሰዎች (content moderators) በብዛት መቅጠር ያስፈልጋቸዋል። አሁን ከሚጠቀሟቸው ከነሱ ውጪ ያሉ ድርጅቶች (outsourced companies) ይልቅ በየሃገሩ ሰዎችን መቅጠር አለባችው። እነዚህም የሚቀጠሩት ሰዎች የሃገሩን ባህል እና የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሰዎች መሆን ይኖርባቸዋል። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ከ7 ሚሊየን ሰዎች በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚ ባለባት ሀገር እና በብዙ ቋንቋዎች በሚጻፍባት ሃገር ላይ በብዛት መረጃዎችን የሚከታተሉ ሰዎች (content moderators) መቀጠር አለባቸው።
2. እነዚህ የማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች ደግሞ ቢያንስ በመረጃ የተረጋገጡ ሃሰተኛ መረጃዎችን ከአውታራቸው ማውረድ ይኖርባቸዋል።
3. እንዲሁም ትክክለኛ ገፆችን ማረጋገጥ (verify ማድረግ) እና ተመሳስለው የተከፈቱ ገፆችን የመዝጋት ሀላፊነታቸውንም ሊወጡ ይገባል።
ኢትዮጵያ ቼክ
@EthiopiaCheck