ከባህር ዳር ከተማ ተነስተው ወደ ጎንደር ያቀኑን ወታደራዊ ኮንቮዮች ያሳያል ተብሎ የተጋራው ፎቶ ከሌላ ቦታ የተወሰደ ነው
ከ15,700 በላይ ተከታዮች ያሉትና ‘Demekech’ የሚል ስያሜ የሚጠቀም የኤክስ/ትዊተር አካውንት ብዛት ያላቸው ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን የሚያሳይ ፎቶ ማጋራቱን ተመልክተናል።
በፎቶው ላይ የሚታዩት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችም ከባህር ዳር ከተማ ተነስተው ወደ ጎንደር ያቀኑ መሆናቸውን ገልጿል።
ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ የጎግል ሪቨርስ ኢሜጅ ሰርች መገልገያን በመጠቀም ባደረገው ማጣራት ከላይ የተጠቀሰው ፎቶ ከሩዋንዳ የተወሰደ መሆኑን አረጋግጧል።
በፎቶው ላይ የሚታዩት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ንብረትነታቸው የሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት ሲሆን እአአ በታህሳስ ወር 2021 ዓ.ም በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተፈጠረን ውጥረት ተከትሎ ሩዋንዳውያንና ዩጋንዳውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በስፋት ሲያጋሩት ነበር።
ይህንንም የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች በመከተል መመልከት ይቻላል:
https://web.facebook.com/share/p/15VXLLitQP/
https://web.facebook.com/share/p/15m5CFiBCd/
በተጨማሪም በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚነበበውን የሰሌዳ ቁጥር ያነጻጸርን ሲሆን የሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት የሚጠቀምበት መሆኑን አይተናል።
ከአውድ ውጭ ተወስደው የሚጋሩ ፎቶዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጥራት እናድርግ።
ኢትዮጵያ ቼክ
@EthiopiaCheck