#FactCheck "የድሮ ፎቶ" እንዲመስል በቅንብር የተሰራ ምስል
'አበበ ቶላ ፈይሳ' የተባለ ፌስቡክ ላይ ከ158 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ግለሰብ "የድሮ ፎቶ እያወጣህ እንደ አዲስ የምትለጥፍ ከሆነ..." በሚል ያሰራጨው ምስል እንዳለ ተመልክተናል።
ግለሰቡ በዚህ ልጥፉ ላይ ከትናንት ጀምሮ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲንሸራሸር የነበረው የፋኖ ሀይሎች አመራር የሆነው የዘመነ ካሴ ምስል "ዓመት የሞላው" መሆኑን ገልጿል።
ይህን ያሳያሉ ያላቸውን እና የፋኖ አመራሩን ፎቶ አምና፣ ማለትም እአአ በ2023 የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች አጋርተውት ነበር ያላቸውን ምስሎች አያይዟል።
ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ማጣራት እንዲያደርግ ጥያቄ የቀረበለት ሲሆን እኛም በዚህ ዙርያ ፍተሻ አርገናል።
በዚህ ዙርያ ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ የድሮ እንዲመስሉ '2023' የሚል ዓመት በፎቶሾፕ ቅንብር እንደገባባቸው ተመልክተናል። ቅንብሩ ሲሰራም የፌስቡክን ዲዛይን በማይመስል መልኩ ተጣሞ እና ከዲዛይን ውጪ ክፍተት ኖሮበት ሆኖ እንደተሰራ መመልከት ይቻላል።
ከዚህም በተጨማሪ መረጃውን አጋርተዋል ወደተባሉት የፌስቡክ ገፆች እና አካውንቶች በመሄድ ምርመራ ያደረግን ሲሆን "የአርበኛ ዘመነ ካሴ የዕለቱ መልዕክት" ከሚለው ፅሁፍ ጋር ተጋርቶ የነበረው ሌላ የፋኖ አመራሩ ምስል መሆኑን ለማየት ችለናል።
በዚህም ምክንያት 'አበበ ቶላ ፈይሳ' በተባለው ግለሰብ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ እና በቅንብር የቀረበ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።
ከአውድ ውጪ ከሚቀርቡ፣ በቅንብር ከሚሰሩ እና ተጋነው ከሚሰራጩ መረጃዎች ራሳችንን በማራቅ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።
ኢትዮጵያ ቼክ
@EthiopiaCheck