የንግድ ስራ ገቢ ግብር ምጣኔ
የካቲት 20/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
የንግድ ስራ ገቢ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡-
👉 ግብር ከፋዩ ዕቃዎችን በማስተላለፍ እና አገልግሎቶችን በመስጠት የሚያገኘውን የገንዘብ መጠን ጨምሮ በግብር ዓመቱ ከንግድ ስራ ያገኘው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን፣
👉 የንግድ ስራ ሃብትን በማስተላለፍ የሚገኝ የገንዘብ መጠን (ከመዝገብ ዋጋ በላይ ያለው ዋጋ)፣
👉 በዚህ አዋጅ መሠረት የግብር ከፋዩ ገቢ ተደርገው የተወሰዱ ሌሎች ማናቸውም ገቢዎች፣
👉 የካፒታል ንብረት የሆነን የንግድ ስራ ሃብት በማስተላለፍ በሚገኘው ጥቅም ላይ ሁለት ግብሮች ሊወሰኑ ይችላሉ፡፡
- የንግድ ትርፍ ግብር
- የካፒታል ዋጋ ዕድገት ግብር
👉ለንግድ ስራው ሃብት የተደረገው ወጪ ከንግድ ስራው ሀብት የተጣራ የመዝገብ ዋጋ የሚበልጠው የገንዘብ መጠን በንግድ ስራ ገቢ ውስጥ የሚካተት ሲሆን ከወጪው በላይ የሚገኘው ጥቅም ደግሞ የካፒታል ዋጋ ዕድገት ግብር ይከፈልበታል፡፡
👉
t.me/tebekasamuel👉
t.me/tebekasamuel ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ
📞 0911190299
#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #samuelgirma
@SAMUELGIRMA