የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ጎበኙ።
ጥር 13/2017 አዲስ አበባ፡ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በመገኘት የባለስልጣኑን የስራ እንቅስቃሴ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት በኢትዮጵያ ውስጥ ጥራት ያለው፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ የሆነ የምግብና የጤና ግብዓት ምርቶች እንዲደርሱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው ምርቶች ወደ ገበያ ከመግባታቸው በፊት ጥራታቸውን በጥብቅ በመፈተሽና በመቆጣጠር ዙሪያ እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናከሮ እንዲቀጥል በመግለጽ በቀጣይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
በጉብኝታቸው ወቅት የመድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ላብራቶሪ እንዲሁም የተለያዩ የስራ ክፍሎች እየሰሩ ያሉትን ስራዎች በአካል ተገኝተው የተመለከቱ ሲሆን በወቅቱ ከነበሩ ደንበኞች ጋርም ስለባለስልጣን መስሪያ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ አስተያየቶችን የጠየቁ ሲሆን በቀጣይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለስልጣኑ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንዲያስቀጥል በሚያስችልበት ሁኔታ ላይ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡