በስጋት ተኮር የድህረ ገበያ ጥናት ላይ በተገኙ ውጤቶች ዙሪያ አውደ ጥናት ተካሄደ
የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን በፋርማኮቪጂላንስ እና ክሊኒካዊ ሙከራዎች ዙሪያ በአውሮፓውያኑ 2024 ዓ.ም ያካሄዳቸውን እንቅስቃሴዎች ለመገምገምና ለመወያየት አውደ ጥናት አካሂዷል። የአውደ ጥናቱ ዋና ትኩረት በስጋት ተኮር የድህረ ገበያ ጥናት የናሙና መሰብሰብ መርሆዎች፣ ቁጥጥር እርምጃዎች እና የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤቶች ላይ ነበር።
አውደ ጥናቱን በይፋ የከፈቱት የባለስልጣኑ የመድኃኒት ደህንነት ክትትል እና የህክምና ሙከራ መሪ ስራ አስፈጻሚ አስናቀች አለሙ ሲሆኑ በኢትዮጵያ የመድኃኒት ጥራትና ደህንነትን ለማረጋገጥ ስጋት ተኮር የድህረ ገበያ ጥናት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት አስረደረድተዋል ።
ከ2016 ሁለተኛ ግማሽ ዓመት ጀምሮ እስከ 2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ስጋት ተኮር መሰረት ባደረገ መልኩ የተሰሩ የድህረ ገበያ ጥናት በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን የተሰበሰቡ ናሙናዎች ላይ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ከባለስልጣኑና ከክልሎች ተወክለው በተገኙ ውይይት ተደርጓል፡፡