ማቹሪቲ ሌቭል ሶስት ለማሳካት ሁሉም ሠራተኛ የበኩሉን ሚና መወጣት አንዳለበት ተገለጻ፡፡
ጥር 26/2017 አ/አ፡ ባለስልጣኑ ለሰራተኞቹ ማቹሪቲ ሌቭል ሶስት ለማሳካት እየተካሄደ ያለውን የኦዲትዝግጅት እና የተሰሩ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ ለሠራተኞቹ ግንዛቤ ሰጥቷል፡፡
በግንዛቤ መድረኩ መክፋቻው ላይ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ደይሬክተር ወሪ/ት ሄራን ገርባ እንደተናገሩት ማቹሪት ሌቭል ሶስት በአለም ጤና ድርጅት ቤንች ማርኪንግ መሰረት በዓለም ዓቀፍ በተዘጋጁ የዎዲት መስፈርቶች መሰረት በመመዘን የሀገራት የመድኃኒት ጥራት ቁጥጥር ኦዲት በማድረግ የተቆጣጣሪዎችን የቁጥጥር ደረጃ የሚበየንበት መሆኑን በመግለጽ እንዚህን ደረጃዎች በማሟላት መቻል እንደ ሀገር ለጤና ግብዓት ቁጥጥር ዘርፍም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የላቀ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ እንደተናገሩት እንደዜጋ ሀገራችንና ህዝባችንን ለማገልገል የተሰጠን ዕድል በመጠቀም የሀገራችን የመድኃኒት ቁጥጥር ዘርፍ ማቹሪቲ ሌቭል ሶስት ኦዲትን በማሳካት የውጭ ሀገራት ምርቶች እየተቀበልን የምንኖርበት ዘመን እንዲያበቃና በሀገሪቱ የሚገኙ የመድኃኒት አምራቾችን ቁጥር ለመጨመር ለሌሎች ሀገራትም የሚሆኑ የመድኃኒት ምርቶች ለማምረት በር ከፋች በመሆኑ የአለም የጤና ድርጅት ማቹሪቲ ደረጃ ሶስት ኦዲትን በስኬት ማጠናቀቅ እንደሚገባ ገልፀዋል። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ለኦዲቱ ብቁ ለማድረግ የህግ ማሻሻያዎች መደረጉን ጭምር አስታውቀዋል።
እስከ አሁን በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ለሰራተኞቹ ማብራሪያ የሰጡት የጥራት ስራ አማራር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አወት ገ/እግዚአብሄር ግምገማውን በስኬት ለማጠናቀቅ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የገለፁ ሲሆን የባለስልጣኑ ሰራተኞች ከመደበኛ የስራ ሰዓት ውጪ ተጨማሪ ስራዎችን ለመስራት ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።