ባለስልጣኑ የሚያስገነባው የልህቀት ማዕከል ለጤናው ስርዓት ትልቅ ጉልበት እንደሚሆን ተገለፀ፡፡
የካቲት 11/2017 ዓ.ም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚያስገነባው የልህቀት ማዕከል ያለበትን ሁኔታ ለመገምገም የአለም ባንክ፣ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አመራሮች ጉብኝት አድርገዋል፡፡
የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ የአለም ባንክ የሀገሪቱን የጤና ስርዓት ለማዘመን እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው የልህቀት ማዕከሉ ለጤናው ስርዓት ትልቅ ጉልበት እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡
የአለም ባንክ የአፍሪካ ዳይሬክተር ዳንኤል ዱሊዝኪ በበኩላቸው ግንባታው የደረሰበትን ደረጃ አድንቀው ማዕከሉ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጠናው ሀገራትም የስልጠናና የምርምር ማዕከል በመሆን እንደሚያገለግል ያላቸውን ተስፋ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ እንደተናገሩት ማዕከሉ ሲጠናቀቅ 257 የጥራት ምርመራ ክፍሎች የሚኖሩት ሲሆን የልህቀት ማዕከሉ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ ሀገራት የስልጠና ማዕከል በመሆን በአህጉሪቱ የሚታዩትን ዘርፈ ብዙ የጤና ችግሮች ለመቅረፍ ትልቅ አቅም ይሆናል በማለት የልህቀት ማዕከሉ የፋይናንስ ድጋፍ ያደረጉትን የአለም ባንክ እንዲሁም የግንባታ ስራውን እየተቆጣጠረ ያለውን የጤና ሚኒስቴርን አመስግነዋል፡፡